የዓለም ምጣኔ ሀብት ዘዋሪዎች ነዳጅ አስመልክቶ አዳዲስ መረጃዎችን እያወጡ ነው።መዕራባውያኑ የሩሲያን ጦርነት ለማስቆም በብዙ እጅ ጥምዘዛ ውስጥ ቢያልፉም ሩሲያ ግን ሁኔታውን አልፋ ጦርነቱ እያካሄደች ነው።የዓለም የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በጋሎን 10 ዶላር ጨምሯል።ይህ ጭማሪ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከሀምሌ 17/2008 በኋላ የመጀመሪያ መሆኑን ብሉምበርግ አስነብበዋል።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት እንዲቆም ሩሲያ ላይ በርከት ያለ የጉዞ እገዳና የሀብት አለማንቀሳቀስ ማዕቀቦች ተጥሏል።ሁሉም የዓለም ሀብት ሩሲያ ጋር ያለ ይመስል በዓለም ገበያ ለሚውደዱ ግብይቶች ሁሉ በምክኒያት እየተቀመጠ ያለው የሁለቱ ሀገራት ጦርነት ነው።
ሞስኮ ነዳጅ መላክ አቁማለች በሚል ሰበብ በ9 እና 10 ዶላር ጭማሪ መከከል ከፍና ዝቅ ሲል የቆየው የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከአስራ አራት ዓመታት በኋላ በበርሜል ከ124 ዶላር በላይ መሸጥ መጀመሩ የዘርፍ ስጋት ሆኖ ቀጥሏል።ይህንን ዜና ዘግይቶ የሰራው BBC የድፍድፍ ነአጅ ዋጋውን 139 ዶላር በበርሚል አድርሶታል።
ከወደ አፍሪካ እየተሰማ ያለው ዜና ደግሞ ዓለም ወደ ባሰ ጭንቅ ውስጥ እንድትገባ ማስፈራሪያ ሆኗል።ባለፈው ሳምንት አውሮፓዊያን የነዳጅ ቋታቸውን ላለማጉደል ወደ አፍሪካ ጎራ ብለዋል።አፍሪካ በቂ የነዳጅ ክምችት ቢኖራትም የመሰረተ ልማቱ የተሳለጠ ባለ መሆኑ ይህንን ችግር ቀርፈን ፍላጎታችንን ከአፍሪካ እናሳካዋለን ሲሉ ቃል ገብተው ነበር።ይሁንና እንቅፋት ብዙ የሆነው የአፍሪካ ልማት በነዳጅ ዘርፉም ገና ካሁኑ እክል እያጋጠመው ነው።
የሊቢያው የብሔራዊ የነዳጅ ኩባኒያ እንዳለው የነዳጅ ዋጋው ከዚህም በላይ ከፍ ሊል ይችላል።ምክኒያቱም በሊቢያ የታጠቁ ቡድኖች ሁለት የነዳጅ ጉድጓዶችን አጋይተዋል።በዚህም ሀገሪቱ የምታመርተውን መርት 330 ሺህ በርሚል እንዲቀንስ አድጎታል።ይህን መሰሉ ድርጊት በሌሎች ነዳጅ ላኪ ሀገራት ላይ የሚደገም ከሆነ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ዓለም አይታው በማታውቀው መጠን ሊጨምርና የሌላውን የገበያ ስርዓት ሊያናጋው እንደሚችል ተሠግቷል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ሀሳባቸውን የሰጡት የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ምክር ቤታቸው ነገሩን ለማስተካከል የሚያግዝ አማራጭ እየፈለገ ነው ብሏል።ሆኖም ከዚህ መቅደም ያለበት ሩሲያን ከዓለም መጣኔ ሀብት ፅር ውስጥማስወጣት ነው ብለዋል።ይህ ካልሆነ ሞስኮ ጦርነት ውስጥ በገባችው ቁጥር የዓለም ምጣኔ ሀብት መዋዠቅ ሊከሰት ነው በማለት በአሜሪካ ድጋፍ ያልሰአቱ ሀገራት በኑሮ ውድነት ተገፍተው ከጎናቸው እንዲሆኑ እያግባቡ ነው።
አሜሪካዊያን የነገሩን ገመድ ወደ ሩሲያ ለመጠምጠም የሚያደጉት ሙከራ ልክ አይደለም ሲሉ የሚሞግቱ አልጠፉም።እነዚህ ተሟጋቾች ለመከራከሪያቸው የሚያነሱት ነጥብ የኒውዮርክ ዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የታየው ጭማሪ ነው።ዋሺግተን ከሞስኮም ሆነ ከሌላ ሀገር የማታስገባቸው፣በሀገሯ ያመረተቻቸው የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ገበያ በኒውዮርክ ግብይት ላይ ባልተለመደ መልኩ ዋጋቸው ንዶ ተገኝቷል።ታዲያ ይህ በምን መልኩ ነው ከሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ጋር ሊገናኝ የሚችለው የሚለው አሜሪካ መልስ እንድጸጥበት ተሟጋቾቹ ጠይቀዋል።
በአሜሪካ ያለው አሁናዊ የነዳጅ ዋጋ በጋሎን ወይም 3.8 ሊትሮች ላይ የጨመረው 41 ሳንቲም ነው።ሆኖም የሀገሪቱ የጥቅል ገበያ ልውውጥ 1.3 በመቶ መቀነሱ ተረጋግጧል።መጠኑ አይገለፅ እንጂ በአውሮፓም ያለው የጥቅል ገበያ መቀነሱ እየገለፀ ነው።
የነዳጁ ዋጋ መውጣት መውረድ እንደ ጃፓን ያሉ መሰል የሀይል አማራጮችን ሙሉ ከሙሉ ከውጪ ለሚያስገቡ ሀገራት መጥፎ ዜና ቢሆንም አሁንም አማራጮች እየፈለጉ ነው።አሁን ጃፓን ከፍላጎቷ 3.5 በመቶ የቀነሰ ነው ኀይል እያገኘች ያለችው።የሆንግኮንግ አማራጭ ኀይል አቅራቢ ሀንግ ሴንግ እያገኘ ያለው ከሚፈለገው በ4 በመቶ ያሽቆለቆለ ነው።የደቡብ ኮሪያ ኮስፒ ደግሞ 2.5 በመቶ ኡየቀነሰ አቅርቦት ነው ለሀገሩ እያቀረበ ያለው ።የአውስትራሊያ ሼድ 1.2 በመቶ ያህል እያጣ ሲሆን ሻንጋይ ኮምፓዚሽን 0.8 በመቶ ያህሉን አለማግኘቱን ለዜና ወኪሎች ተናግረዋል።በሲንጋፑር IG ዩኒቨርስቲ የዓለም አቀፍ ገበያ ጥናት ባለሙያ የሆኑት ያኘጁን ደንግ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ማስፈሪያ እያደረጉ ነው።
እንደ ባለሙያው ገለፃ ጦርነቱ በዚሁ የሚቀትል ከሆነ የገበያው ሁኔታ መሻሻል አያሳይም ሲሉ ለአሶሼትድ ፕሬስ ገልፀዋል።
ይሁንና ባለሙያው ከማዕቀብ አንጻር ከምዕራባዊያን ጋር በተቃራኒው ቆመዋል።በዚህ ጊዜ ማዕቀቡ የንግዱ ዘርፍ ከእንቅስቃሴ ማገት ሁኔታውን እንደሚያባብሰው የሚገልፁት ያፕጁን ማዕቅቡ በመጣል ላይ ያተኮርነው ያህል በኀይል አማራጭ አቅርቦት ላይ ብናውለው የነዳጁ ዋጋ አሁን ከሚታየው ዋጋ የተሻለ መገበያያ ለአለም እናቀርብ ነበር ብለዋል።
በዚህ ጊዜ ዓለም ላይ የሚታየው የገበያ ምስቅልቅል ከምስራቁ ጦርነት ጋር ብቻ መጋመድ የለበትም ሲሉ ባለሙያው ይሞግታሉ። ምክኒያታቸውም ደግሞ አለም አቀፍ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ የዓለም ገበያ እጎሳቋል ብለዋል።ከዚህ ወረርሽኝ በኋላ የዓለም ምጣኔ ሀብት በዋጋ ግሽበት መጎዳቱን ገልጸው የግሽበቱ ትፅዕኖ እስካሁን ያልተላቀቅነው መሆኑንም ባለሙያው አንስተዋል።
በእርግጥ ግጭቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተፀዕኖ ያሳረፈባቸው ዘርፎች እንዳሉ መካድ አይቻልም።ግጭቱ በተለይ ከምግብ አቅርቦት ጋር ያለውን ስራ ወደ ኋላ እንዲጎተተ አድርጎታል።እጅግ በጣም ለም የሆነና ጥቁር ባህር አከባቢ ያለው ሰፊ መሬት ከፍተኛ የምግብ የምግብ ምርት የሚገኝበት አከባቢ ነው።አሁን ይህ አከባቢ በጦርነት ቀጠና ውስት በመግባት ለአውሮፓ፣ለእስያና አፍሪካ ይቅርብ የነበረው ከፍተኛ የምግብ አቅርቦት ችግር ውስጥ እንዲወድቅ ሆኗል።
ይህ ደግሞ ከነዳጅ አስደንጋጭ የዋጋ ጭማሪ በኋላ በምግብና ምግብ ነክ አቅርቦቶች ላይ ተመሳሳይ የዋጋ መናር ሊያስከትል እንደሚችል ተሰግቷል ይላልየአሶሼትድ ዘገባ።
የባለሙያዎቹ ‘’ሁሉም ችግር ከቶርነት ጋር መያያዝ የለበትም’’የሚለው ዕይታ ሚዛን የሚደፋው የጀርመኑ ስታስቲክስ ቢሮ ያወጣው መረጃ ነው።በጀርመን አሁን ላይ የውጭ ሀገራት ትዕዛዝና ሀገራዊ ምርት ከምን ጊዜውም በላይ መጨመሩ ተነግሯል።ጭማሪውም ከ1.8 በመቶ ወደ 7.3በመቶ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።የጀርመን ምጣኔ ሀብት በችግር ወቅት
የማደግ ልምድ ያለው ነው የሚለው የኦናዶሉ ዘገባ የበርሊን ምጣኔ ሀብት በኮሮና ቫይረስ 11.9 በመቶ ጨምሮ ነበር ይላል።
በአሁኑ እድገት የአውሮፓዊያኑ ትዕዛዝ ከፍሎ የታየ ሲሆን አምና ከነበረው 2.6 በመቶ የምርት ትዕዛዝ ዘንድሮ ወደ 8.3 በመቶ ጭማሪ ከፍ ማለቱ በስታስቲክስ ቢሮው መረጃ ላይ ተገልጿል።
የአሜሪካና አጋሮቿ ሁሉንም የገበያ ችግር ወደ ሩሲያ ማላከክ ልክ አለመሆን የሚገልፀው የዓለም ባንክ ያወጣው መረጃ ነው።የባንኩ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ ለ BBC እንደገለጹት የዩክሬን ሩሲያ ግጭት የተጀመረው መጥፎ ሰዓት ነው ።ምክኒያቱ ደግሞ በግሽበት እየዳከረ ያለው የዓለም ምጣኔ ሀብት በርካቶች ባሳተፈው ጦርነት ውስጥ መውደቁ ምጣኔ ሀብቱ ለማገገም የሚወስድበት ጊዜ ሊረዝም ይችላል ብሏል።የጦርንርት ዋናው ችግር የዜጎች ህይወት የሚቀጥፍ ቢሆንም በምጣኔ ሀብት በተለይ ለድሆች በሚቀርበው የምግብ ፍጆታ ላይ የሚኖረ ተፅዕኖ ከባድ መሆኑን ፕሬዝደንቱ ማልፓስ ተናግረዋል።
የነዳጁ ዋጋ መቸመር በኤዥያውያን የአቅርቦት መጠን ላይ ጉድለት ከማስከተሉ ባሻገር የአሁግሩን የጥቅል ገበያ ፍሰት እየቀነሰው ነው።በዛ ሰፊ ገበያ ያላት አሜሪካ የሲያ ገበያ መዳከም አሳስቧታል።የነዳጁ ዋጋ ለማስተካከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቀዳሚ ተሰላፊ እንደ ምትሆን እያስታወቀች ነው።ውጭ ጉዳይ ሚኒቴር አብቶኒዮ ብሊከን እንዳሉት የባይደን አስተዳደር እና አግሮቻቸው የሩሱያ ነዳጅ መቅረት የፈጠረው ቀዳዳ ለመሸፈን እየመከሩ መሆናቸውንለአልጀዚራ ገልፀዋል።
አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በበኩላቸው በሩሲያ ላይ ማዕቀብ የጣለው ኮንግረስ ለመፍትሄውም እየሰራ ነው ብለዋል።ችግሩ የሚጀምረው ከዩክሪን በመሆኑ ኮንግረሱ በቀጣይ ሳምንታት ተግባራዊ የሚሆን የ10 ቢሊየ ዶላር ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል።የነናንሲ ፔሎሲ ጥረት የሩሲያ ነዳጅና ሌሎች ምርቶች በዓለም ላይ ገዢ ማሳጣት ነው።ይህንንም አሜሪካ በኮንግረሷ ጭምር ትኩረት ሰታ እየሰራች መሆኑ በከፍተኛ ባለ ሥልጣናቷ በኩል እየገለጸች ነው።ይሁንና ይህ በቀላሉ ውጤት የሚያመጣ አይደለም ሲሉ የዘርፉ ባለ ሙያዎች ይናገራሉ። ይሁንና ይህ ነገር ዕውን ቢሆን ቀድማ የሩሲያን ገበያ ፈላጊ ራሷ አሜሪካ ስለመሆኗ ተናግረዋል።ዋሽግተን ያላትን አማራች ኀይል ግድ ሆኖባት ብትጠቀም እንኳ በአውሮፓና በሌሎች አከባቢዎች
ያሉትን ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ ወደ ሩሲያ ጥገኝነት መመለሷ አይቀሬ ነው ይላሉ ያፕጁን።መክኒያቱም የነ አፍሪካ አስተማማኝነት በጥቃት የታጀበ በመሆኡ ዘላቂ ጠቃሚነቷ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነው።
አልጀዚራ፣ BBC፣ብሉምበርግ፣አሶሼትድ ፕሬዝና አናዶሉ የዘገባው ምንጮች ነቸው
በ ዘመድኩን ብሩ