የዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመዲናዋን የትራንስፖርት ችግሮች የሚያቃልሉና የመንገድ መሰረተ ልማትን ይበልጥ ለማዘመን የሚረዱ የ3 የመንገድ ፕሮጀክቶችን የፊርማ ስነ ስርዓት አከናወነ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ የሚደረግባቸዉ በአጠቃላይ ከ10 ኪሎሜትር በላይ ርዝመት እንዲሁም ከ15-30 ሜትር የጎን ስፋት ያላቸዉን 3 የመንገዶችና ድልድይ ፕሮጀክት ግንባታዎችን ሊያከናዉን እንደሆነ አስታወቀ፡፡
ፕሮጀክቶቹ በከተማ አስተዳደሩ በጀትና በአለም ባንክ ብድር የሚከናወኑ መሆናቸዉ ተገልጿል::
የመጀመሪያዉ የአፍሪካ ጎዳና -ኤድናሞል አደባባይ-22ማዞሪያ -እንግሊዝ ኢንባሲ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሰሆን 4.4 ኪሎሜትር እርዝመት እንዳለዉ ተገልጿል፡፡
ከ2.4-4 ሜትር ስፋት ያለዉ የእግረኛ መንገድ ፤2ሜትር ስፋት ያለዉ የብስክሌት ብቻ መሄጃ መንገድ 9የሳይክል ማቆሚያ 3 የሳይክል ማከራያ ቦታዎች እንደሚያካትትና ለከተማዋ የመጀመሪያ የሆነ የመንገድላይ የደህንነት ቁጥጥር ስርአት ያካተተ ዲዛይን መሆኑንም ይፋ ተደርጓል:: ይህንን ስራ የሚሰራዉ ኮንትራክተር የቻይና ሲቪል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እንደሆነ ተገልጿል::
ይህ ፕሮጀክትም ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላየ እንደሚፈጅ ተገልጿል:: ሁለተኛዉ የየአደር ጤና በለቴ-ሱቅ -አለምገና አደባባይ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ነዉ:: አዲስ አበባ ካሏት 5 በሮች መካከል አንዱ እንደመሆኑ መጠን ከተማዋን በዙሪያዋ ካሉት አካባቢዎች በተለይም ከደቡብና ደቡብ ምዕራብ መዉጫ ማለትም ወደአለም ገና ፣ቡታጅራ ፣ሶዶ፣ወልቂጤና ጅማ ለሚደረጉ ጉዞዎች ትልቅ የትራንስፖርት ማሳለጥ እንዲኖር ያደርጋል ተብሏል፡፡
5.6 ኪሎሜትር ርዝመት ያለዉ ሲሆን የእግረኛ መንገድን ጨምሮ 30 ሜትር ስፋት እንደሚኖረዉ ተገልጿል:: ይህንን ስራ የሚሰራዉ ኮንትራክተር ይርጋለም ኮንስትራክሽን ሀ.የተ.የግ.ማ እንደሆነና ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪዉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሚሸፍን ተገልጿል::
ሶስተኛዉ የአቃቂ ዴልድይ ግንባታ ፕሮጀክት ነዉ:: 61.2 ሜትር ርዝመት ያለዉ ሲሆን 140 ሜትር ወደድልድዩ የሚያገናኙ መንገዶችን እንደሚያካትት እና 25 ሜትር የገን ስፋት እንዳለዉ ይፋ ተደርጓል:: ይህንን ስራ የሚሰራዉ ኮንትራክተር ብሪጅ ኮንስትራክሽን ሀ.የተ.የግ. ማ እንደሆነና 447.2 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚፈጅ ተገልጿል፡፡
ሙሉ ወጪዉን የሚሸፍነዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሆነም ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንተባና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ እነዚህ ፕሮጀክቶች በመዲነዋ የሚታየዉን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ አቅም ለመፍጠር የሚያስችሉ ኤንደሆኑና በከተማዉ ሰፊ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ሊሰራ እንደሚገባ በር አፋች መሆናቸዉን ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ሀላፊ ኢንጅነር ሞስ ጥበቡ የሶስቱ መንገዶች ፖሮጀክት ቅድሚያ መሰጠት የማህበረሰቡን ጥያቄ ለመመለስ እንደሆነ ገልፀዉ፠ የዉለታ ፊርማ ስነ-ስርአቱ መከናወኑ የተጀመሩ የመሰረተ ልማቶች በአጭር ጊዜዉስጥ እንደሚጠናቀቁ የክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ አመቺ እንዲሆን የተደረገ መሆኑንጠጠቁመዋል።
ምክትል ከንቲባዉ የከተማ አስተዳደሩ ፕሮጀክቶች ተጀምረዉ እንዲቆሙና እንዲደናቀፉ ስለማይፈልግ በተሰጠዉ ጊዜ ዉስጥ በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ መመሪያ ሰጥተዋል።
በየክፍለከተማዉ ያሉ የስራ አሰፈፃሚዎች በመንገድ ወሰን ምክንያት ለሚፈጠሩ ችግሮች ከአካባቢዉ ነዋሪዎች ጋር በጋራ በመሆን አፋጣኝ የሆነ የመፍትሄ አቅጣጫ እንዲያስቀምጡ ሀላፊነት ሰጥተዋል። እነዚህ ሶስት ፕሮጀክቶች ተጠናቀዉ ለማህበረሰቡ አገልግሎት ለመስጠት የሁለት አመት ጊዜ እንደሚፈጅባቸዉ ተገልጿል።
ከአፍሪካ ጎዳና – እንግሊዝ ኢንባሲ ፕሮጀክት ሁለት ቦታዎች ላይ ዲጅታል የትራፊክ መቆጣጠሪያና ቅፅበታዊ የአዉቶቡስ መረጃ ማግኛ ስርአቶች ዲዛይኑ ላይ እንደሚያካትት ተጠቁሟል።
በዳኛቸዉ መላኩ