በአዲስ አበባ በክርና ፕላስቲክ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 8 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን እንደተቻለ 2 ሚሊዮን ብር የተገመተ ንብረት መውደሙ ተገለፀ ።
በአዲስ አበባ ከተማ ሰኞ ምሽት 1ሰዓት ገደማ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታዉ ቃሊቲ ኢንደስትሪ መንደር ውስጥ በክርና ፕላስቲክ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 2 ሚሊዮን ብር የተገመተ ንብረት መውደሙን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል። የደረሰዉን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ሶስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ሃያ አንድ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች መሰማራታቸውን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለአዋሽ ሬዲዮ ተናግረዋል።
አደጋውን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት መፍጀቱን አስታውቀዋል። የእሳት አደጋዉ ተስፋፍቶ አደጋዉ በደረሰበት ፋብሪካ ከዚህ የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስና በአካባቢዉ ባሉ ፋብሪካዎች እንዳይዛመት ማድረግ ተችሏል ያሉ ሲሆን ። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹ ባደረጉት ርብርብም 8 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን እንደተቻለ እና አደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም። የአደጋው የመነሻ ምክንያት በመጣራት ላይ ይገኛል በለዋል ።
በመጨረሻም ባሳለፈነው ቅዳሜና አሁድ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 እና ወረዳ 12 ክፍቱን በተተወ ዉሀ በአቆረ ጉድጓድ ዉስጥ እድሜያቸዉ 12 እና 25 የሆኑ ታዳጊና ወጣት ህይወታቸዉ ማለፉ ተገልጿል ። በአቃቂ ወረዳ 1 እድሜዉ 25 ዓመት የሆነ ወጣት ወንዝ ዉስጥ ገብቶ ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስከሬኑን አዉጥተዉ ለፖሊሰ አስረክበዋል ነው የተባለው ። ሌላኛዉ አደጋ እለተ እሁድ 10 ሰዓት ገደማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 12 ታዳጊዎች ተቆፍሮ ክፍቱን የተተወና ዉሀ ባቆረ ጉድጓድ ዉስጥ ዋና ለመዋኘት ከሄዱ ሶስት ታዳጊ ተማሪዎች መካከል እድሜዉ 12 ዓመት የሆነው የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ታዳጊ ዋና ለመዋኘት ገብቶ ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።
የዚህ ታዳጊ አስከሬን በፍለጋ የተገኘዉ ሰኞ ማለዳ ነዉ። አስከሬኑንም ፖሊስ ተረክቧል። በአዲስ አበባ የሚገኙ ወንዞችና በተለይም ክፍቱን የተተዉ ዉሀ ያቆሩ ጉድጓዶች እየተበራከቱ በመምጣታቸዉ ወላጆች ታዳጊ ልጆቻቸዉ እንዲሁም ወጣቶች በወንዞችና ዉሀ ያቆሩ ጉድጓዶች አካባቢ የሚኖራቸዉን እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ ማድረግ ያስፈልጋል። በ2014 ዓ.ም ክፍቱን በተተዉና ወሀ ባቆሩ ጉድጓዶች ዉስጥ እድሜያቸዉ 7 እና 15 የሚገመት ታዳጊዎች በእነዚህ ወሀ ባቆሩ ጉድጓዶች ዉስጥ ገብተዉ ህይወታቸዉን ማጣታቸው የሚታወስ ነው ።
በያዝነዉ በ2015 ዓ.ምም መስከረምና ጥቅምት ወር 3 ታዳጊዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል። ችግሩ ረጅም አመታትን ያስቆጠረና እየቀጠለ የመጣ ችግር በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ እሙን ነው ። እንዲህ ባለዉ አደጋም በየአመቱ በአማካይ 12 ታዳጊዎች ህይወታቸዉን ያጣሉም ተብሏል ።
በመቅደላዊት ይግዛው