Connect with us

አለም አቀፍ

የታይዋን ደሴት የነፃነት ጉደይ በዋዛ የሚያላቅቀን አይደለም :- ቻይና

Published

on

featured
Photo: wilsoncenter

የታይዋን ደሴት የነፃነት ጉደይ በዋዛ የሚያላቅቀን አይደለም ሥትል ቻይና በብርቱ አስጠንቅቃለች፡፡ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት በአሜሪካ የቻይናው አምባሳደር ቂን ጋንግ ናቸው፡፡ ባለፈው ዓርብ ከአሜሪካ ሬድዮ ጋር ቃለ ምልልስ የነበራቸው በአሜሪካ የቻይና አምባሳደር ቂን ጋንግ አሜሪካ የታይዋን ነፃ መውጣት የምታበረታታ ከሆነ የሁለቱ ሀገራት ጉዳይ መጨረሻ ጦርነት ብቻ ይሆናል ያ እንዳይሆን ግን ዋሺንግተን ብትጠነቀቅ ይበጃታል ነው ያሉት፡፡

ቻይና የራሥ ገዟን የታይዋንን ደሴት የራሷ ሉዓላዊ ግዛት አድርጋ ነው የምትቆጥራት፡፡ የቻይና መንግሥት የታይዋንን ደሴት ወደ ዋናው ምድሩ ለመቀላቀል የኃይል ርምጃ መውሰድ አያስፈልግም የሚል አቋም ቢኖረውም ዛሬ ዛሬ ግን የአሜሪካና የታይዋን መወዳጀት እልህ ውስጥ እንደከተተው ይነገራል፡፡

የቻይናውን አምባሣደር የዛቻና የማስጠንቀቂያ ጉዳይ በተመለከተ አስተያየት የተጠየቀው የአሜሪካ መንገሥት የሰጠው ፍንጭ የለም፡፡ የቻይናው አምባሣደር ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ደግሞ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንና የቻይና አቻቸው ዋንግ ዪ በዩክሬን ጉዳይ ከተወያዩ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነው፡፡ የቻይና መንግሥት ከቅርብ ወራት ጀምሮ ቻይናና ታይዋንን በሚለየው የውሃና የአየር ክልል ተደጋጋሚና ከባድ የሚባል የጦር ልምምድ ማድረጉን ተከትሎ በቻይናና በታይዋን ደሴት መካከል ውጥረቱ መጦዙ ይታወቃል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በአንድ ወቅት ከቻይናው አቻቸው ሺ ዢንፒንግ ጋር በስልክ የሁለት ሰዓታት ውይይት ሲያደርጉ አሜሪካ የታይዋን ነፃነት አታበረታታም ከቶም አያገባትም ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

ይሁንና ባይደን የቪዲዮ ኮንፈረሱን ካጠናቀቁ በኋላ ለሀገራቸው የመገናኛ ብዙኃን ማብራሪያ ሲሰጡ ቻይና ታይዋንን የምታጠቃ ከሆነ አንላቀቅም ማለታቸው በቻይና ሹማምንት ዘንድ የ79 ዓመቱን አዛውንት በከሃዲነት አስፈርጇቸዋል፡፡

ባለፈው የአውሮፓውያኑ 2021 ዘመን ለአሜሪካ ኮንግረስ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካ ጥምር ጦር ኃይል ዋና አዛዥ ጀነራል ማርክ ሚሌይ ቻይና በቀጣዮቹ 6 ዓመታት ውስጥ ታይዋንን ለመውረር ተሰናድታለች ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

የአሜሪካ መንግሥት አሁን ከሁለት ኃያላን መካከል የሥንግ መያዙ እየታየበት ነው፡፡ አሜሪካ በታይዋን ደሴት ከቻይና ጋር በዩክሬን ደግሞ ከሩሲያ ጋር የገባችበት አተካሮ በሁለቱም ወገን ቢሆን በሩሲያም ይሁን በቻይና ቤት ከባድ የእሣት አደጋ መጋረጡ ይታያል፡፡

ግንባረ ኮስታራው የሩሲያው ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን በሰጡት ማብራሪያ ጠየቅናቸው አስጠየቅናቸው የአሜሪካና የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ባለስልጣናት እኛ የምንፈልገውን ምላሽ አልሰጡንም፤ ከዚህ በኋላ ደጅ የምንፀናበት ጊዜም ፅናትም አይኖረንም ነው ያሉት፡፡

ፑቲን አሉ ከመከላከያ ሚኒስትራቸው ጋር ቆመው የሀገራቸው የጦር መሣሪያ ጠበብቶች ያወጡትን ግሩም ድንቅ የተባለለት የጦር መሣሪያ አገላብጠው እያዩ ፤ የባይደን አስተዳደር ባለስልጣናት ተጨማሪ ጦራቸውን በዩክሮን ለማስፈር እያጓጓዙ ነው፡ እንግዲህ እዚያው ዐውደ ግንባሩ ላይ እንገናኛለን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከፈረንሣዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በጉዳዩ ዙሪያ በስልክ መክረዋል፡፡ የሩሲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በሰጡት ማብራሪያ ሞስኮ ጦርነት አትፈልግም ማለታቸው ይታወቃል፡፡

የላቭሮቭ አስተያየት የተሰጠው ዓርብ ዕለት ሲሆን ከዚህ በፊት ሐሙስ ዕለት ደግሞ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሩሲያ ዩክሬንን የምትወር ከሆነ የከፋ መቅሰፍት ይወርድባታል ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወቃል፡፡

አሜሪካ በምዕራብ አውሮፓ ቀጣና የሰፈሩ በብዙ አስር ሺ የሚቆጠሩ ወታደሮች እንዳሏት ይነገራል፡፡ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንሥኪ በበኩላቸው ጦርነቱ ተጀምሯል ነው ያሉት፡፡

እንደ ዘለንሥኪ ጥልቅ ማብራሪያ ታዲያ ጦርነቱ ጀምሯል ማለታቸው የምጣኔ-ሐብታቸው መላሸቅን ተከትሎ ነው፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በቅርቡ ለዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንሥኪ ስልክ ደውለው ሩሲያ ድንገቱን ወረራ ልትፈፅም እንደምትችል ነግረዋቸዋል ፤ አስጠንቅቀዋቸዋልም፡፡

ሩሲያ ዩክሬንን ልትወር ነው የሚለው ዜና በድፍን ዓለም ትርምስን ፈጥሯል፡፡ አሁን በምሥራቅ አውሮፓ የተፈጠረው የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት የሚፈነዳ ከሆነ የአውሮፓ አህጉር የማይጠገን ስብራት ይሰጠዋል ነው የሚባለው፡፡

የባይደን አስተዳደር ባለስልጣናት የሩሲያን ጉዳይ ወደ ሙሉ ጦርነት የማምራቱን ነገር የማይቀር በሚል ይተነብዩታል፡፡ የሩሲያ በዩክሬን ድንበር ግዙፍ የጦር ኃይል የማስፈር ጉዳይ ለምዕራባውያኑ መንግሥታት ከባድ ፈተና ሆኖባቸዋል፡፡ በቀድሞው የብሪታንያ መንግሥት ለቤላሩስ አምባሣደር የነበሩት ኒጌል ጉልድ ዳቪሥ የአሁኑን የአውሮፓ ምድር ፍጥጫ ሲገልፁት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1980ዎቹ ወዲህ አስከፊው ሰቆቃ ነው ብለውታል፡፡

ባለፈው ማክሰኞ ከሲ.ኤን.ኤን ጋር ቃለ ምልልስ የነበራቸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይዳን ሩሲያ በዩክሬን ላይ አንዲት የወረራ ሙከራ ብታደርግ ወዮላት ነው ያሉት፡፡

የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በበኩላቸው ሀገራቸው ለሰሜን ጦር ቃል ኪዳን አጋር የሚሆን ጦሯን ይሁን የትኛውንም አስተዋፅኦ ልታደርግ መዘጋጀቷን ገልፀዋል፡፡ የፈረንሣዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንም ፑቲን ዩክሬንን ለመውረር ውሣኔ ላይ የሚደርሱ ከሆነ ዘግናኝ ዋጋ ይከፍላሉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ሦስት የአሜሪካ ባለስልጣናት በሰጡት ማብራሪያ አሜሪካና የቅርብ አጋሮቿ ተጨማሪ የጦር ኃይልና የጦር ቁሣቁሣቸውን በሮማኒያ በቡልጋሪያና በሀንጋሪ ለማስፈር መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡

የዩክሬን ምጣኔ-ሐብት በወራራው ስጋት እንኳን ክፉኛ መጐዳቱ ይነገራል፡፡ እንደ አብነትእንኳን ዩክሬን በዓለም ላይ ካሉ አራት የጥራጥሬ አምራቾች አንደኛዋ ስትሆን በዚህ ሥጋት የተነሣ በቀጣዮቹ 5 ዓመታት ራሷ በብዙ መጠን ከፍተኛ ምንዛሬ በቆሎ እየገዛች የምታስገባ ሀገር እንደምትሆን ከወዲሁ ተተንብዮላታል፡፡

በአውሮፓ አህጉር የኃይል አቅርቦት የ30 በመቶ የተፈጥሮ ጋዝ አቅራቢዋ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ወደ ጦርነት የምትገባ ከሆነም የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት አፋቸውን ከፍተው ይቀራሉ በነዳጅ እጥረት ነው ሚባለው፡፡

እንግሊዝ የጦር መርከቦቿንና የጦር ጀቶቿን በምሥራቅ አውሮፓ ለሰፈረው የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኃይል ልትልክ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የእንግሊዝ መንግሥት ከዚያ መሰሉ ውሣኔ የደረሰው የአውሮፓ አጋሮቿን ከየትኛውም ጥቃት ለመከላከል ስለ መሆኑ ይነገራል፡፡

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪሥ ጆንሰን ጦራቸውም በተጠንቀቅ ይቆም ዘንድ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ነው የተባለው፡፡ አሁን እንግሊዝ በርካታ የጦር መሣሪያዋን የላከቸው በዩክሬኗ አጐራባች ኤስቶኒያ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

ጆንሰን ከውሣኔው በኋላ ቃል በቃል ሲናገሩ “This package Would Send a Clear message to The Kremlin- We will not tolerate destabilizing activity and we will always stand with our NATO allies in this Russian Hostility” ነው ያሉት፡፡ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪሥ ጆንሰን እንደማስታረቅ ማጣላት፤ ጆንሰን መለስ አድርገውም ቭላድሚር ፑቲን ደም መፋሰሱን ከመረጠና ያንን መንገድ ከተከተለ ለአህጉረ አውሮፓ ትልቅ ሀዘን ኪሣራና ምጥ ነው ሲሉ እጃቸውን አጨብጭበዋል፡፡ ዩክሬንም ብትሆን አሉ ጆንሰን የወደፊቱን ምርጫዋን ማስተካከል አለባት ነው ያሉት፡፡

የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አክለውም የብሪታንያ ጦር በመላው አውሮፓ ይሰፍር ዘንድ በቃ I have Ordered our armed forces to prepare to deploy across Europe next week. ቦሪስ ጆንሰን በዚህ ሣምንት ወደ ዚያው ቀጣናው ተጉዞው የሩሲያውን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ያውያዩአቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከወዲሁ ግን ከዕባብ መርዝ በከፋው ምላሣቸው ወግተዋቸዋል፡፡ ብሪታንያ በኤስቶኒያ ከ900 በላይ ጦር እንዲሁም በዩክሬንም ከ100 በላይ ጦር እንዳላት ይታወቃል፡ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ጦሩን ከዚያ የምሥራቅ አውሮፓ ቃጣና ካላስወጣ በስተቀር ሩሲያና ቻይና በተጣመሩበት ወዲያም ላይፋቱ በተጋመዱበት የቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ውርደት እንደሚገጥመው የሜይል ፕላሥ ዘገባ ያተተው፡፡

ሩሲያ ይግረማችሁ ስትል ከቤላሩስ ጋር ለምታደርገው የጋራ የጦር ልምምድ ጦሯን ወደዚያው መላኳን ያሳያል፡፡ የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው ማብራሪያ በሩሲያና በቤላሩስ ጦር የሚያደርገው የጋራ የጦር ልምምድ የአጋር ሀገራትን ጥምረትና ትብብር ለማሳየት መሆኑን አስምሮበታል፡፡

የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ሩሲያ ወታደሮቿንና ህልቆ መሣፍርት የሌለውን የጦር መሣሪያዋን ለጦር ልምምዱ ወደ ቤላሩስ መላኳን በትኩረት እየተከታተለው መሆኑን ገልጿል፡፡ የአሜሪካ ሹማምንት ቀድሞውንም የሚታወቁበትን የሸፍጥ ግብራቸውን በግልፅ ማሣየት ጀምረዋል፡፡ እነርሱ ጠላታችን ሲሏት የበረችዋን ቻይናን በሩሲያ ላይ ተፅዕኖዋን እንድታበረታ መወትወት ይዘዋል፡፡

በሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊዋ ቪክቶሪያ ኑላንድ ቻይና በሩሲያ ላይ ፊቷን ታዞር ዘንድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ኑላንድ የትዕቢት በመሰለው ንግግራቸው እንዲህ አሉ We are Calling 0n Beijing to use its influence with Moscow to urge diplomacy b/c if there is a conflict in the Ukraine it is not going to be good for china. ሲሉ ዛሬም የማስፈራሪያ መልዕክታቸውን አስይዘው ቻይናን ትዕዛዝ ሰጥተዋታል፡፡

አሜሪካኖቹ ሩሲያ ዩክሬንን ብትወር እንዲች ብለው ቀድመው እሣት ውስጥ አይገቡም ነው የሚባለው፡፡

ያው የሚያሞከሻሹት የሰሜ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /NATO/ እንደፈንጂ መሞከሪያ ይቀድማል ወዲህም የዩክሬን ልጆች የእሣቱን ላንቃ ይጋቱታል እንጂ ሴትየዋ ለንግግራቸው ለከት የላቸውም ይባልላቸዋል፡፡

በቅርቡ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከቻይናው አቻቸው ዋንግ ዪ ጋር ሲነጋገሩ ብሊንከን ይሏቸዋል ምናለ ወዳጃችሁን ሩሲያን አንድ ብትሏት፤ አርፋ ብትቀመጥ፡፡

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ንግግርዎን ጨረሱ ይሏቸውና እንኪያስ እናንተ ምናለ በቻይና የውስጥ ጉዳይ ምላሣችሁም እጃችሁም ቢያድብ ሲሉ ከንፈራቸው እስኪንቀጠቀጥ ብሊንከንነ ከብስጪት አድርሰዋቸዋል፡፡

ንግግሬን ልጨርስሎት ይስሙኝ ይላሉ ዋንግ ዪ ስለምን በሩሲያ የውሰጥ ጉዳይ ያልበላችሁን ታካላችሁ አሁንም አይበቃችሁም፡፡ ብትተው ይበጃችኋል ነው ያሏቸው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ አዲስ የኑክሌር ጦርነት ለመጀመር መሰናዳቷ ተነግሯል፡፡ አሜሪካ በዚህ ዓመት በዚህ ባሳለፍንው ሳምንት ግዙፍ የተባለለት የጦር ልምምድ ማድረጓ ሲነገር በኔብራስካ ኦማሃ ያለው የኑክሌር እዟም በዚያ የጦር ልምምድ ማድረጓ ተነግሯል፡፡

በአሜካ ሳይንቲስቶች ፌዴሬሽን የኑክሌር ጦር መሣሪያ ዋና ዳይሬክተር ሀንስ ከሪሥተንሰን አዲስ የኑክሌር ጦርነት ዕድቅ ሰንደው መላካቸው ተነግሯል፡፡ እኒያ በነሱ አጠራር Great Power ይሏቸው ኃያላኑ መንግሥታት ኃይላቸው የሚሟሽሸው በዚያ የኑክሌር መሣሪያ ከተቀጣቀጡ ብቻ መሆኑ ይነገራል፡፡

ይሄ ፍንጭ አፈትልኮ ይውጣ እንጂ ታዲያ ስለ አዲሱ የኑክሌር ጦር ዕቅድ ብዙም በግልፅ የሚታወቅ ነገር የለውም፡፡ በርግጥም ዓለማችን ለማጥፋት ስለሚጠነሰስ ድግስ ምን ተብሎ ለዓለም ይነገራል፡፡

ወትሮስ ድግሱ ለማን ሆነና የመጨረሻው መጨረሻ ቀን ሲመጣ ጥፋቱን የደገሱትም ራሳቸው ያንን የመርዝ ብጥብጣቸውን ተጐንጭተው የማሸለባቸው ነገር ዛሬ ላይ አልታይ አልሰማ ብሏቸዋል ፤ ነገር ግን የከፋ ዋይታና ሰቆቃ!

ትንታኔ ዘገባውን በዋቢነት ስናዘጋጅ ሬውተርስ፣ ስካይ ኒውስን፣ ዘ-ዊክን፣ ሲ.ኤን.ኤን፣ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን፣ ሜል  ፕላስን፣ ኤል.ቢ.ሲ ኒውስን፣ አልጀዚራን፣ አሪቲ ድረ-ገፅንና ሜትሮ ኒውስን ተጠቅመናል፡፡

የዘገበው፡- ትዕግሥቱ በቀለ

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

ትኩረት

ሩሲያ በዩክሬን የጀመረችውን ወታደራዊ ዘመቻ ተከትሎ የተላለፉ ዉሳኔዎች

Published

on

featured
Photo: Social Media

ዓለማችን ከፌብሩዋሪ 24/2022_ማርች 24/2022 በነበሩት ጊዜያት30 ቀናት ከባዱን ጊዜ አልፋለች። ሩሲያ በዩክሬን የጀመረችውን ወታደራዊ ዘመቻ ተከትሎ ከባድ ውሳኔዎች ተላልፈዋል። አብዛኞቹ ውሳኔዎች ሩሲያን በመቃወም፤ ዩክሬን በመደገፍ የተሰጡ ናቸው። በሩሲያ በኩል የተላለፉት ደግሞ በተቀራኒው። ይሁንና እነዚህ የሁለቱ ወገን የፍቃድና ክልከላ እወጃዎች በዓለም ላይ ላሉ፤ ጦርነቱ በምንም መልኩ የማይመለከታቸው ዜጎች አቅም እየፈተነ ነው። በጦርነቱ መጀመሪያ ሰሞን በጉዞ እገዳዎች የጀመረው የማእቀብ እርምጃ እምብዛም ስጋት ያጫረ አልነበረም። ሁኔታው ቀስ በቀስ ወደ ንግድ ነዳጅ ጉዳዮች ሊያመራ ዓለም የገበያ እንቅስቃሴ በፍጥነት አናግቷል።

በዚህ የአንድ ወር ወታደራዊ ዘመቻ በመጀመሪያ ሁሉም ነገር ይመለከተኛል የምትለው አሜሪካ 100 በሚሆኑ የሩሲያ ባለስልጣናትና የቀድሞዋ ሶቬት ቅራት ያለቻችቸው ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ ጣለጭቀጥሎም እንግሊዝንና የአውሮፓ ህብረትን ያስከተለችው ዋሺግተን የጉዞ ታጋቾች ቁጥር ወደ 386 ሰዎች ከፍ አደረጉ። በዚህ እቀባ የቀድሞዎቹ ፕሬዝዳንትና መከላከያ ሚኒስቴር ዪሜትሪ ሜድቬዬቭና ሰርጌ ሸጉ ተጠቃለሉ። ከግለሰብ ወደ ግዢ ልውውጥ ያደረገው ማዕቀብ ብሪታኒያና የአ.ሕ. በጋራ በመሆን ለሩሲያ የሚያቀርቧቸውን ውድ ዕቃዎች አንሸጥም ሲሉ አወጁ። እኛ ያመረትናቸው ተሽከርካሪዎች ሳይቀሩ ሩሲያ ምድር አይሄዱም ሲሉ ወሰኑ።

ካናዳና ጃፓን የማዕቀብ መጣሉን ተግባር ተቀላቀሉ። እንዲህ ከሆነ ያዋጣል ያሉት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከእንግዲህ ከሩሲያ የማስገባው ነዳጅ አልፈልግም ሲሉ ከባድ ውሳኔ አሳልፈዋል። ይህ የሆነው ጦርነቱ ተፋፍሞ በወሩ ወገብ ላይ በነበረበት ጊዜ ነው። ከዚህም በኋላ አሜሪካ ሩሲያን በማዕቀብ የሚጫንና ጦርነቱ የሚያወግዝ አጋር ፍለጋ በወሩ ውስጥ በርካታ ሀገራት አካላለች አላደርስ ያላቸውንም ቦታ ስልክ በመምታት “እህ ምን ትላላችሁ “ስትል በሚስጥርም በግልፅም ጠይቃለች። ከሩሲያ ዩክሬወን ጦርነት በኋላ እንደ አሜሪካ እጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒዮ ብሊንከን ስራ የበዛበት ባለስልጣን የለም።አሜሪካ አውጋዥና አጋዥ ፍለጋ በአፍሪካ ፣በኤዢያና መካከለኛው ምስራቅ ያደረገችውን ጉዞ የመሩት ብሊንከን ናቸው። ይሁናና ጉዞዋቸው ውቴታማ አልነበረም። አንዳንዶቹ “አንደግፍም”ከሚለው አሉታዊ ምላሽ ያለፈ ማብራሪያ መስጠታቸው የአሜሪካ የዲፕሎማሲ ስራ የቁልቁለት መንገድ ጀምራለች እስከማለት አድርሷቸው ዋል።

የፓክስታኑ ፕሬዚዳንት ኢምራን ካሀን የሰጡት ምላሽ በአንድ ወር ውስጥ በጦርነቱ ጡዘለት ልክ ዓልምን ጉድ ያስባለ ነበር።አሜሪካ በተዓ.ኤስ በሳውዲ አረቢያና ህንድ ጠብቀው የነበረ በጎ ምላሽን ሳታገኝ ቀርታለች። በኪሳራ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱትን ብሊንከንናሳርፈው ወደ ኳታር ያቀኑት ፕሬዚዳንቱም ቢሆኑ ከዶሀ መንግስት የተመቸውን ድጋፍ ይዘው አልመጡም። ጦርነቱን ሰእብ አድርጎ ሩሲያን ከዓለም የመነጠሉ ተግባር ብዙ ተደክሞበታል። ሆኖም ውጤቱ አመርቂ አልሆነም ልለዋሺግተን። ዝምታን የመረጡት ሀገራት ከሩሲያ ላለ መቀያየም ነው ቢባልም ነገሩ ግን የዋሽግተን የክሽፈት ጉዞ አድርገው የቆጠሩም ነበሩ። ድሀና ባለ እዳ ሀገራት ባለባቸው ድክመት እየተስፈራሩ በነገሩ ላይ ኧጃቸውን እንዲነከሩ ተጠይቀዋል ፣ተገደዋል። ሆኖም በዝምታ ሽሽታቸው ቀጥለዋል።

በተለይ አፍሪካዊያን የኬቭ ነዋሪዎቻቸው ትኩረት ይሰጣቸው ለሚልለው ጥያቄያቸው መልስ ሳይሰጥ ነገሩን እንዲያወግዙ ሲወተወቱ ሰንብተዋል። በአንድ ወርጦርነት አስገራሚ ተብሎ ከተነሳው ውስጥ ይኸው የአፍሪካዊያን ስደተኞች ጉዳይ ነበር። በጦርነት ውስጥያሉት ዩክሬናዊያን በአፍሪካዊያን ላይ ያደረሱት ግፍ ከአሁግሪቱ የነጠላቸው ይመስላል።በዚህ ረገድ ስኬታማ ተደርጋ የምትወሰደው ዲ.ሪ.ኮንጎ ናት። ብራዚል 223 የኬብ ነዋሪዎች ወደ ፈረንሳይ አሸሽታለች። በማዕቀብ መጣሉ አሜሪካንን የደገፏት የአውሮፓ ሀገራትን ያስደነገተ ውሳኔ ከአውሮፓ ተሰማ። አውሮፓዊያን ከዚህ በኋላ ከሩሲያ አንድ በርሚል አያገኑም ስትል ሩሲያ በግሏ ማዕቀብ ጣለች። ይሄኔ በዓለማችን ከነዳጅ አምራች ሀገራት ቀዳሚ የሆነችው አሜሪካ ሩሲያ በመቃወም የደገፏትን አጋሮች አላየሁም አልሰማሁም በሚመስል ዝም ብሏቸዋል።

የአሜሪካንን ዝምታ ያስተዋሉ ት አውሮፓዊያን ሩሲያ የከለከለቻቸውን የነዳጅ ክፍተር ለመድፈን መካከለኛው ምስራቅ ደጋግመውና ተፈራርቀው ጎበኙት። አፍሪካንም የነዳጅ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ደጋግመው ተማፅነዋታል። የፈረሳዩ ኢማኑኤል ማክሮን ፤የእንግሊዙ ቦሪስ ጆንሰን፤ የጀርመኑ ቻንስለር አለፍ ስሆልዝ አውሮፓን ወክለው ነዳጅ ፍለጋ ቢሮዋቸው ትተው የተንከራተቱ መሪዎች ናቸው። በዚህ ፍለጋቸው ከድርጀት ኦፔከን ፣ከመግስታን አልጄሪያን፣ሞሮኮን፣ ናይጄሪያን፣ከአፍሪካ ይናገሩ ሲሆን ከመካከለኛው ምስራቅ ነዳጅ አምራቾች ደግሞ ኩዌትን፣ ሳውዲ አረቢያ ፣ እና ሌሎችንም አግኝተው የነዳጅ ሽጡልን ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። ሆኖም አረቦች ከድርጅታቸው ኦፔክ መመሪያ አንወጣም በማለት የተናጠል መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል። አፍሪካዊያን ደግሞ የነዳጅ መሰረተ ልማታችን ደካማ ነው፤እሱን የምታለሙ ከሆነ ነዳጅስ ነበረን ሲሉ በቅድመ ሁኔታ ተለያይተዋል።

አውሮፓዊያን ከሩሲያ የሚገኙት የነዳጅ አቅርቦታቸው ተቋርጦባቸዋል። ከዚህ ውጪ ራሳቸው ባስቀመጡት እገዳና ሩሲያ በሰጠችው ምላሽ ውስጥ ሀገራት ብቻ ከ150 ቢሊየን ዶላር በላይ በአንድ ወር ውስጥ አተውታል። ይህንን በፍጥነት የተገነዘቡት የህብረቱ አባል ሀገራት አካሄዳቸውን ቁጥብ አድርገዋል። ነገሩ ከረገበ በሚል ለማደራደር ሙከራ ያደረጉም ነበሩ። በወሩ ማብቂያ በህብረቱ የአባልነት ቦታ አገኛለሁ በሚል ምኞት ከኔቶ ጎን መሆኗን ያወጀችው ሞልዶቫ ስህተት እንደሰራች እየተነገረ ነው። በአንድ ወር የጦርነት ሂደት የአሜሪካና ዩክሬን የህንድን ድጋፍ ያሳጣቸው ተብሎ ከተቀመጠው አንዱ የህንድ ተማሪዎች ጉዳይ ነበር። ተማሪዎቹ የአፍርካዊያንን ያህል ባይሆንም መውጫ አጥተው መቸገራቸው በበርካታ መገናኛ ብዙሃን ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ህንዳዊያኑን መንገድ ለመስጠት በሚል ሩሲያ የወሰደችው መፍትሄ በህንድ በኩል ምስጋና ተችሮታል ።በዚህም ህንድ ለነአሜሪካ ጥያቄ ዝምታን በማድረግ ለሩሲያ ያላት ውግንና በሰምና ወርቅ መልኩ ገልፃች። ወርቁ ገብቶናል ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን “ህንድ ከአሁኑ ወዳጇ አሜሪካ ይልቅ የቀዝቃዛው ጦርነት አጋሯ እንደመረጠች አውቀናል ሲሉ ተደምጠዋል።

ጦርነቱ ከሶስት ሚሊየን በላይ ዜጎች ከቤታቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል። በጎረቤት ሀገራት በርከት ያሉ ዩክሬናዊያን የሞቀ አቀባበል ተደርጎላቸው የሚኖሩ ሲሆን ከኬብ ሳይወጡ በህንፃዎች ምድር ቤት የተጠለሉም ምድር ቤት ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። በ30 ቀናት የስደተኞች ጉዞ በርካታ በረራ የተደረገባት ሀገር ስዊዘርላንድ መሆኗም ታውቋል።የ30 ቀናቱ የዩክሬንና ሩሲያን ጦርነት ለማርገብ በሚል ሁለት ሀገራት ቀዳሚ እርምጃ በተግባር አሳይተዋል። ቤላሩሲና ቱርክ።

ቤላሩስ በዝቅተኛ ዲፕሎማቶች መካከል የተደረጉ ውይይቶች ያስተናገደ ሲሆን ጦርነቱን ለማርገብ ሆነ ለማስቆም ግን አልሆነላትም። ቀጥሎም ቱርክ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ደረጃ ከፍተኛ የውይይት ድግስ አዘጋጅታ ብትጠራም የሚኒስትሮቹ መገናኘት ያመጣው ነገር አልነበረም ።የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ከፕሬዚዳንት ቭላድር ፑቲን ጋር ፊት ለፊት መገናኘት አልፈልግም ያሉትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴቹ ውይይት ፍሬ አልባ መሆናቸው ተከትሎ ነበር።ዘለንስኪ የዘር ሀረጋቸው የሚመዘዝባት እስራኤልን በጦር መሳሪያ አልደገፍሽንም በሚል ቢወቅሱም የድርድርሩ ሁነኛ ቦታ ቴላቪቭ መሆኗን ግን ተናግረዋል። ጦርነቱ ካሳየን ገራሚ ነገር አንዱ አሜሪካና አውሮፓውያን ተረባርበው ስፖርትን ከፖለቲካው ጋር የቀላቀሉበት መንገድ ነው። ሩሲያን ከአለም ዋንጫ ፣ከአውሮፓ ሊጎችና ከማንኛውም የስፖርት ንግግር አግደዋታል። በዚህ ሳያበቃ የሩሲያ ባለ ሀብቶች ሲያስተዳድሩዋቸው የነበሩ ግለቦችም አደጋ ውስጥ እንዲወደቁ ተደርጓል።

አውሮፓዊያኑ እነዚህንና መሰል ጫናዎች በሩሲያ ላይ ቢያሳድሩም ዩክሬንን ኝ በምንም መልኩ የሚጠቅም አይደለም። ዩክሬን በእስካሁኑ ቆይታ ከ245 ቢሊየን በላይ ወይም ከ 75 በመቶ በላይ የሚሆኑ የሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ቆሟል። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጡ የምጣኔ ሀብት ስራዎች በግማሽ ያህል ጠፍተዋል። ሩሲያ በብዙ መንገድ ፈጥነው መጣል ያልቻሉት አካላት ፕሬዚዳንት ቮሎንድሚር ዘላንስኪ ኬቭን ለቀው እንዲወጡ ተጠይቀው ነበር። በሩሲያ ላይ ማዕቀብ የታልለችው ጃፓን ሳትቀር ፕሬዚዳንቱ ከሀገር እንዲወጡ ጠይቃለች። የሩሲያ ወዳጅ ናት የምትባለው ቻይና ጨምሮ የ18 ሀገራት መሪዎች ዘለንስኪ ኬቭን ላቀው በመውጣት የዩክሬንን ህዝብ ይታደጉ የሚል ጥያቄ አቅርበዋል።

ከሀገሬ የትም አልሄድም ብለው የፀኑት ዘላንስኪ የመላው ዓለም ድጋፍ ተማፅነዋል ።በመላው ዓለም ያሉ ሰዎች ሩሲያን የሚቃወም ሰልፍ እንዲያደርጉ ፕሬዚዳንቱ ጠይቀዋል። በአንድ አንድ ሀገራት ከፕሬዝዳንቱ ጥሪ በተቃራኒ “በሀገራችን ያሉ ሩሲያዊያን የጦርነቱ አካል አይደሉም”የሚሉ ሰልፎች ተካሂደዋል። የሩሲያ ባለስልጣናት ባለሀብቶች በውጭ ሀገራት ያስቀመጧቸው ሀብቶች አንዱ የወሩ መነጋገሪያ ነብር። የስዊዝ ባንክና አንድ አንድ ምዕራባዊያን ሀገራት ባንኮች 630 ቢሊዮን ዶላር ወይም 470 ቢሊየን ፓውንድ የሚበልጥ የሩሲያዊያንን ሀብት እንዳይቀንሳቀስ አግደዋል። በጦርነቱ የአንድ ወር ሂደት 5 ጋዜጠኞች ተጋድለዋል። ባውሊና ፣ሰርጌ ቶሚሊንኮ አሌክሲ ኮቫሌቭ ሜዱዛና አናስታሪያ ካሪሞቫ በጦርነቱ መሀል የተገደሉ የዩክሬንና ሩሲያ ዘጋቢዎች ናቸው።ሩሲያ በነዚህ ሁሉ ጫናዎች ውስት ብትሆንም የተበረከከች አትመስልም። ጦርነቱ እየገፋችበት ነው። አፀፋዊ የማዕቀብ ምላሾችንም እያጠናከረች መታለች ከበርካታ ሀገራት ጋር ባልት የንግድ ልውውጥ ዶላርን ከገበያ ውጪ አድርጋ በራሷ የመገበያያ ገንዘብ “ሩብል”ቀይራለች። በዩክሪን የተሰማሩ ወታደሮች በጀግንነት ግዳጃቸውን እንዲወጡ በሚል ልዩ መብቶች ሰጥታለች ። ከተባሉት ነገሮች ሁሉ ግን አሜሪካንን ባለስልጣናትን ያስበረገገው ሩሲያ አንዳች የሚያሰጋ ነገር አለ ቢዬ ከጠረጠርኩ የኒውክለር ጦር መሳሪያዬ ተግባር ላይ ይውላል ስትል ከባዱን ካርዷን በተጠንቀቅ አድርጋለች ። ጦርነቱ ግን ንብረት እያወደመ ፤አካል እያጎደለና የሰውን ህይወት እየቀጠፈ ቀጥሏል።Bloomberg,Anadolu,BBC, አልጀዚራ,Sky News The Gardian የዘገባው ምንጮች ናቸው።
በዘመድኩን ብሩ

Continue Reading

አለም አቀፍ

99 በመቶ ዉጤታማ የሆነዉ የወንዶች ወሊድ መከላከያ እንክብል

Published

on

featured
Photo: Social Media

የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል 99 በመቶ ውጤታማ ሆኗል ተባለ። የወሊድ መከላከያው እርግዝናን በመከላከል ረገድ ውጤታማ ነው ተብሏል በሚዋጥ እንክብል መልክ የተዘጋጀ እንደሆነ ነዉ የተነገረዉ። በሴቶች ላይ ብቻ የነበረውን ጫና ያቃልላል በመባል አዲሱም የወሊድ መከላከያ ተስፋ ተጥሎበታል።  ይሄም የወሊድ መከላከለያ ሴቶች እንደሚወስዱት ወንዶች በአፍ በመዋጥ በእንክብል መልክ ቢሰጣቸዉ እጅግ ዉጤታማ በሆነ መልኩ እርግዝናን ሊከላከል እንደሚችልም ነዉ የተገለጸዉ። ስካይ ኒዉስ እንደዘገበዉ የወሊድ መከላከያ እንክብሉ በአይጥ ላይ በተደረገ ሙከራ እርግዝናን ለመከላከል ውጤታማ ሆኗል።

አዲሱ በወንዶች የሚዋጠዉን የወሊድ መከላከያ እንክብል ግኝት ተመራማሪዎቹ በአሜሪካ ኬሚካል ባለሙያዎች ማህበር ጉባኤ ላይ ነበር ያቀረቡት። አዲሱን ግኝት ያቀረቡት ዶክተር በአብደላ አል-ኖማ፤ ተመራማሪዎች ለአስርት ዓመታት ያክል በአፍ የሚወጥ የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል ለመፍጠር በሙከራ ላይ እንደነበሩም ነዉ የገለጹት፣ ሆኖም ግን እስካሁን እውቅና የተሰጠው መድሃኒት በገበያ ላይ እንደሌሌም ጭምር ነበር የገለጹት።

ከዚህ በፊት ሲሞከርባቸዉ የነበሩት የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብሎች የወንዶች የወሲብ ሆርሞን ቴስቴስትሮንን ኢላማ ያደረጉ እንደነበረ ያነሱት ዶክተር አብደላህ መድሃኒቶቹ አገልግሎት ላይ እንዳይዉሉ ግን ከልክ ያለፈ የሰውነት ውፍረትን፣ ድብርትን እና ሌሎች የጎንዮሽ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ በመሆናቸዉ ጥቅም ላይ ማዋሉ አዳጋች እንደሆነም ጠቁመዋል።  አሁን የተሰራው የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል ግን ከሆርሞን ጋር ግንኙነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ፤ በሰዎች ላይ ሙከራ በቅርቡ ማድረግ እንደሚጀመር አስታውቀዋል።

አዲሱ የወሊድ መከላከያ በሴቶች ላይ ብቻ የነበረውን ጫና ያቃልላል የሚል ተስፋ እንደተጣለበት በሰፊዉ እየተነገረ ይገኛል። ምክንያቱም ሴቶች እርግዝናን ለመከላከል የተለያዩ መድሃቶችን ከመዋጥ ጀምሮ ማህፀን ውስጥ የሚገቡ መሳሪያዎችን በመጠቀም ለተለያዩ ጉዳቶች ሲጋለጡ በመቆየታቸዉ ነዉ።

ከዚህ በፊት የወሊድ መከላከያን መጠቀም የሚፈልጉ ወንዶች ግን ኮኖዶምን የሚጠቀሙ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ “ቫሴክቶሚ” የተባለ እና በቋሚነት እንዳይወልዱ የሚያደርገውን የቀዶ ጥገና አማራጭ ብቻ ነበር የነበራቸዉ።  ይሄም ደግሞ መልሰዉ መዉለድ ቢፈልጉ ሁኔታዉን አስቸጋሪ ሊያደርገዉ የሚችል ነበር። በወንዶች ላይ ለወሊድ መከላከያ የሚደረገው “ቫሴክቶሚ” የተባለው ቀዶ ጥገና ህክምና ከዋጋዉ ውድ መሆን በተጨማሪ፤ ብዙም ስኬታማ እንዳልሆነ ይነገራል። ስለዚህ የሄኛዉም አዲሱ ግኝት ብዙ ችግሩችን እንደሚያቀልም ተስፋ ተጥሎበታል።
ዶ/ር ኤርሚያስ ማሞ

Continue Reading

አለም አቀፍ

አፍሪካ ትልቁን የአከባቢው አየር መለወጥ የፈጠረው አደጋ ማስተናገድ ጀምራለች…

Published

on

featured
Photo: IUCN

አፍሪካ አሁን ባልሰራችው የመቀጣቷ ትልቅ ማሳያ መከሰት ጀምሯል። ለዛውም ለአፍሪካ ተርፎ ለዓለም መስህብ በሆነው በማዳስካር አረጓንዴ ስጦታ ላይ የዓልም ሳምባ ናችዉ ከተባሉና ከአንድ እስከ አራት ከተቀመጡት ውስጥ ነው። በምድራችን ስርዓት እስትፋንስ ውስጥ ብቻውን ያለው አስተዋፅዎ በራሱ በምንም የሚተካ አይደለም። በብዛት ሳይሆን በዝሪያ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ የትም ዓለም ላይ የማይገኙ ብርቂዬ የእንሣት ዝሪያዎች በምቾት የሚያንፈላንስስ መኖሪያ ነው። የማድስካሩ የኦክሲጂን አምራች ማሶዋላ ብሄራዊ ጥብቅ ደንና ፓርክ።

ፓርኩ 2330 ኪሜ የየብስና 100.30 ኪሜ የውሀ አካል የያዘ ነው። ይህንን ቦታ ማዳካስካራዊያን የደኖች ሁሉ ዓይን ብለው ይጠሩታል። በትሮፒካል ራይንፎረስት የአየር ክልል ውስጥ እንደሚነገረው ማሶዋላ ይህንን ዘመን ሁሉ በብቃት ያገለገለው የተከለለበት የአየር ንብረት መሆኑት የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። አሁን 7 ነጥብ 97 ቢሊየን መድረሱ የሚነገረው የዓለም ህዝብ የመጠቀሚያ ከሆኑት ስፍራዎች አንዱ የሆነው ማሶዋላ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጠፋ ነው። የጥብቅ ደኑ ደቡባዊ ክፍል አረንጓዴ ተፈጥሮውን አጥቶ ወደ አሸዋነት እየተቀረ ነው። በቅርብ ያሉ የሰው ዘሮችና በደኑ ውስጥየሚኖሩ እንሣት በዘመናት ታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በምግብ እጥረት ስማቸው ጠርቷል።

በቴክሳስ ኦስትን ዩኒቨርሲቲ የብዙሀን ህይወት መዕከል መስራችና ተመራማሪ ዶክተር ቶማስ ባይኖሮዊች የማሶዋላ ጥብቅ ደን ሁኔታ እጅጉን አስደንጋጭ መሆኑን ይናገራሉ። በደቡባዊ የፓርኩ ክፍል በደረሰው የምጥፋት አደጋ አሁን የቀሩት ድርቅን መቋቋም የሚችሉ የተለየ የተፈጥሮ ፀጋ የታደሉ ዕፅዋቶች ብቻ ናቸው። የአከባቢው ቀዝቃዛ ውሀ ጠፍቷል፤ቦታውም በአሸዋ ክምር ተተክቷል ያሉት ዶ/ር ቶማስ ንፋሱ የሚያስነሳው የበረሀ አዋራ ምግብ በሚጠብቀው የህፃናት ዓይን ውስጥ ገብቶ ሌላ ችግር እየፈጠረ ነው ብለዋል።

አሁን አፍሪካ ትልቁን የአከባቢው አየር መለወጥ የፈጠረው አደጋ ማስተናገድ ጀምራለች የሚሉት ደግሞ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ተመራማሪ የሆኑት የጎ.ሼና ካሮ ናቸው።

አፍሪካ ለችግሩ መፈጠር እጇ በሌለበት ጉዳይ በችግሩ ውጤት ማሶዋላን የመሰለ አሁጉራዊ አልፎ ዓለምን በኦክሲጂን የሚመግበውን ስፍራ እየተነጠቀች ነው ብሏል። የተ.መ.ድ.የአከባቢው መጎዳት የዓለም አየር ንብረት ለውጥ ብቻ አይደለም እያለ ነው። የችግሩ ፈጣሪዎችም ራሳቸው የሀገሪቱ ነዋሪዎች እንደሆኑ ድርጅቱ ተናግሯል። የነዋሪዎቹ ቁጥር በፍጥነት መጨመር፤አራት አመታትን ያስቆጠረው የአከባቢው ድርቅ፤ ከፍተኛ የደን ጭፍጨፋ፤ የከሰል ፍለጋ በሚል የሚጠፋው የብዙሀን ህይወት መጨመርና ድህነት የማስዋላን ጉዳት ያባባሱ ናቸው ሲል ድርጅቱን ጥቅሶ ዪሮ ኒውስ ዘግቧል።

ለብዙዎች መትረፍ የምትችለው ማዳካስካርአሁን በደኑ አከባቢ የሚኖሩ ከአንድ ሚሊየን የሚበልጡ ዜጎች በዓለም የምግብ ፕሮግራም ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ ተደርገዋል ሲል ዘገባውን ጨምሮ አሳውቋል። የአከባቢው አጠፋፍ እጅግ ፈጣንና ከቁጥጥር እየወጣ ነው ያለ የተ.መ.ድ. ማስታወቂያ ሰቷል። ቦታው በከፍተና ስጋት ውስጥ ያለ መሆኑ በቀጣይ ዓለማችን በክፋቱ ተወዳዳሪ የሌለው ዓይነት ድርቅ አሊኦያም ከዛ የባሰውን እልቂት ልትመለከት እንደምትችል አስጠንቅቋል።

ከዛ በፊት ግን መንግስታት የአከባቢ ጥበቃን ዕውን ለማድረግ የወጡ ህጎች ትኩረት ሰጥተው ሊተገብሩ እንደሚገባጥቆማ ተሰቷል። በተለይ በካይ ሀገራት ተቋሞቻቸው ለአካባቢ ጥበቃ የሚደረገውን ርብርብ በቀዳሚነት ሊደግፉት ይገባል መባሉን በዩሮ ኒውስ ላይ ሰፍሯል። ቴዎዶይ የተባለና በአከባቢው የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስተባባሪ እንዳሉት የጥብቅ ደኑ ደቡባዊ ክፍል የሚስተዋለው የአየር ንብረት ለውጥ በፍፅሙ ተገማች አለመሆኑን ይናገራል።ከቅርብ አመታት በፊት በአከባቢው የሚኖሩ ትልልቅ ሰዎች ዝናብ የሚዘንብበትንና የሚመጣበትን አቅጣጫ ሳይቀር ይናገሩ ነበር። አሁን ላይ ሰዎች ትንቢያ መስጠቱ ይቅርና ከእንግዲህ ለአከባቢው ዝናብ እንደማይዘንብ አምነው ተቀብለዋል።

ነዋሪዎቹ አሁን ላይ ትንቢያዎቹን ያቁሙ እንጂ እንዲህ በፍጥነት እንደሚሆን ባይጠብቁም ከአየር ንብረት መለወጥ ጋር በተያያዘ በአከባቢው ችግር ሊፈጠር እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር። በተ.መ.ድ. የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አብድሮይና አኖዚ እንደሚሉት የፓርኩ መራቆትና የአከባቢው በድርቅ መጠቃት የሚቀጥሉ ክስተቶች እንደሚሆኑ “Scientists Alert”ለተባለ ድህረገፅ ተናግረዋል። የአከባቢው ስር የሰደዱ ድህነት ለነዚህ ክስተቶች መቀጠል ዋነኛ ምክኒያት መሆኑንም ባለሞያዎቹ ይገልፃሉ። “ሰዎች ህይወታቸውን ለማቆየት አከባቢያቸው ላይ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት ከህግ ውጪም ቢሆን ይጠቀማሉ። በደቡባዊ ማዳካስካር ፤በደቡባዊ ማስካላ ያለው ትልቁ ሀብት ደን መሆኑ መዘንጋት የለበትም”ይላሉ ባለሙያዎቹስለዚህ ዜጎች በህይወት ለመኖር ዳኞቱ ባልተገባ መንገድ ጭምር እያወደሙ ለችግራቸው መውጫ ያደርጉታል ተብሏል። አንድሮይና ኦኖዚ እንደሚሉት ትልቁ መፍትሄ አሁንም በካይሮ ለጋሽ ሀገራት ጋር ነው።እነዚህ አካላት በማሳዋም ሆነ ሌሎች ስጋት ባንዣበባቸው የምድራችን እስትንፋሶች ዙሪያ እጅ አጠር ዜጎች ከድህነት የመውጫ መንገዶች ሊያመቻቹ ይገባል ብሏል።

ችግሩ ፈር ሊይዝ የሚችለው የነዚህን ነዋሪዎች የገቢ ምንጭ ከዳኞቹ አላቆ ወደ ሌሎች ዘፎች ማዞር ሲቻል መሆኑን ባለሙያዎች ያምናሉ። በሌላ በኩል አሁን በማዳካስካር ይህ አይነቱ ክስተት የተለመደ መሆኑን ለማስረዳት ሞክረዋል። ህርግርሪቱ ብርከት ላሉ ጊዜያት መሰል ችግር ውስጥ እየገባች በትግል ታልፋለች ያሉት እነዚህ ተመራማሪዎች የአሁኑን በልዩነት ወስዶ ወደ አየር ንብረት ለውጥ ማስጠጋት ተገቢ አይደለም ብለዋል።

በዳክ ዩኒቨርሲቲ Conservation Biologist የሆኑት ስቱርት ፒም የተ.መ.ድ. ም ሆነ የማዳካስካር ድርቅ “የተለመደ ነው”ያሉትን ተመራማሪዎች ተቃውመዋል።ማዳካስካር ተለምዶዋዊ ድርቅ የላትም።በደቡብ የማሳዋላ ክፍል የተስተዋለው ችግርም በቀጥታ ከአለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዘ መሆኑን ተናግረዋል። የአከባቢው ድሀ ነዋሪዎች በደቡብ ሰሜን ዋልታዎች እየተፈጠሩ ያሉ ከፍተኛ የዕሳተ ጎሞራ ፍንዳታዎችን ከተፈጥሮዋዊ ኡደት አውጥቶ ለሆነ አካል ሊሰጥ የታሰበ ይመስላል በማለት ሁሉም ከሀላፊነት ሳይሸሽ ዓለም ለማዳን የሚጠበቅበትን አስተዋፅዎ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። The Traveler በሁለቱም ዋልታዎች እጅግ ሰፊ የሆነና ከ2500 አመታት ወዲህ ተፈጥሮ የማያውቅ የእሳተ ጎሞራ ፍንዳታ እየተፈጠረ መሆኖን አስነብቧል።

ዓለም ያላትን የተፈጥሮ ፀጋ በአግባቡ ባልያዘችበት በዚህ ወቅት በአንታርቲካ 737 ፍንዳታዎች ፤በግሪንላንድ አካባቢ 1113 ፍንዳታዎች ተከስተዋል።ፍንዳታዎቹ መጠናታቸው በውል ያልተመዘገበ ከፍተኛ ሰልፈሪክ አሲድ በምድር ላይ እንዲገኝ አድጓል። ቀደም ሲል የተፈጠሩ የእሳተ ጎሞራ ፍንዳታዎች የከፍታቸው መጠን የሚለካው በወቅቱ በሚያደርሱት ጉዳት ነበር ይላሉ በዴንማርክ ኮፐንሀገፍ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ባለሙያ Anders svensson.የአሁኑ ኝ ከፍንዳታው ብኋላ በሚተወው ቅሪት የወደፊቱን አለም ሊጎዳ የሚችል ጭምር በመሆኑ አደገኛ ነው ይላሉ። ታዲያ ይህ የተፈጥሮ አደጋ የተሰጡንን ፀጋዎች ካለመንከባከባችን ጋር ሲደምወር የዜጎችን ጉዳት ከፍ ስለሚያደርገው በእጃችን ያለውን ተፈጥሮን የመታደግ ዕድል ልናባክነው አይገባምበማለት የፊዚክስ ባለሙያ ይናገራሉ።ተመራማዎቹ የእሳተጎሞራ ፍንዳታ ናሙና በመውሰድ ሰፊ ምርመራ አድርገዋል።ይህም ከ1ኛ ዝቅተኛ ደረጃ እስክ 8ኛው ከፍተኛ ደረጃ የሚደርስ ነው።

የምርምር ቡድኑ በነዚህ ላይ ባደረገው ዳሰሳ 69 ጊዜ የተደረገው 18185 ቶሞባራ ተብለው የሚጠሩ ፍንዳታዎችን መዝግቧል።ይህንን መሰል ክስተቶች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተደጋግሞ የሚከሰት ከሆነ የፀሀይን ሀይል የመጋረድ አቅም ያለው ክስተት እንደሚፈጠር ተሰግቷል። ይህ ክሆነ ደግሞ ምድር በቅዝቃዜ መድረቋ ሩቅ አይሆንም ሲሉ ዘርፉን ቅርብ ሆነው የሚከታተሉ ባለሙያዎች አስጠንቅቋል።
የሰው ልጅ ግን ስጋቱን ለቀነስ መፍትሄ ለማምጣት አሁን ላይ የተቆጣጠረችው የተፈጥሮ ሀብቶች በአግባቡ መጠቀም የመጀመሪያም የመጨረሻም አማራጮቹ ናቸው። Euro news፣ ሳይንቲስቲስ አለርት ድህረ ገፅ፤ The Traveler ምንጮች ናቸው።
በዘመድኩን ብሩ

Continue Reading

በብዛት የተነበቡ