ኦቲዝም አንድ በሽታ ነው ማለት አይቻልም። በአጠቃላይ ተመሳሳይ መገለጫ ያላቸው ከአእምሮ እድገት መዛባት (ከአብዛኛዉ ሰዉ መለየት) ጋር የተያያዙ ችግሮች የጋራ ስም ነው። ኦቲዝም የሚለው አጠራር ከግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “አውቶ” ማለትም የአንድ ሰው እኔነት (ራስ) ከሚለው ሲሆን፣ ኦቲዝም የተባለበት ምክንያት ይህ ሁኔታ ያለባቸዉ ሰዎች አብዛኛው ዓለማቸው በራሳቸው ስለሚሽከረከር ነው፤ የፈጠሩት የራሳቸዉ ምናባዊ አለምም ስለምኖራቸዉ ነዉ።
አብዛኛዉ ሰው ውስጣዊውንና ውጫዊውን ማለትም የግሉን አና ከሌሎች ጋር ያለዉን ዓለም አመጣጥኖ ነው የሚኖረው። ኦቲዝም ያለባቸው ግን ልክ ሳጥን ውስጥ እንዳለ ሰው ብዙውን ጊዜ የሚያሳልፉት በራሳቸው ጭንቅላት ውስጥ ነው። ከዚህም የተነሳ ለሰው ግራ የሚያጋባና ለመረዳት አስቸጋሪ የሆነ የባህርይ፣ የቋንቋና የማህበራዊ ግንኙነት ሁኔታዎች ይታዩባቸዋል።
ሁሉም ልጆች በተመሳሳይ ደረጃ ጉድለት ስለማይኖራቸው ኦቲዝም ያለበት እያንዳንዱ ልጅ አንድ አይነት ሊሆን አይችልም። ከ 1994 እስከ ሜይ 2013 ኦቲዝም አምስት የተለያዩ የኦቲዝም መጠሪያ አይነቶች የነበሩት ሲሆን ፤ እነርሱም፡- አስፐርገርስ ሲንድሮም (ሊትል ፕሮፌሰር)፣ በሌላኛው ጫፍ ደግሞ Pervasive Development Disorder, Chilhood Disintegrative Disorder, PDD – NOS, Genetic ASD) ይባሉ ነበር። ነገር ግን ከዚያ በኋላ አምስቱም በአንድነት ኦቲዝም ስፔክትረም ዲኦርደርስ በመባል ይታወቃሉ።
በቁጥር ደረጃ ስናጥ በአሜሪካ በ 1990 ከ 10,000 አንዱ ነበር ዛሬ ግን ከ 44 ሰዎች አንዱ ኦቲዝም አለበት እኛ ሀገር ግን ወደ አንድ ሚልየን አከባቢ የሚጠጉ እንደሚኖሩ ይገመታል። በኦቲዝም የተጠቁ ሰዎች መግባባት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ግንኙነት ለመፍጠርና ለመግባባት ይቸገራሉ፡፡ በተጨማሪም ለተወሰኑ ነገሮች ብቻ ፍላጎት ማሳየት በተደጋጋሚ ባህሪያትን ማሳት ከሚታይባቸዉ ባሀሪዎች መካከል ናቸዉ፡፡
ሁሉም ኦቲዝም ያለባቸዉ ሰዎች ይነስም ይብዛም አብዛኞቹ ላይ ከሚታዩ ችግሮች መካከል፡-
1. ውስን የሆነ ስሜታዊነት፡- የራሳቸዉንም መግለጽ ይሁን የሌሎችን መረዳት ይከብዳቸዋል
2. (ቋንቋ)ግባባት አለመቻል፡- በንግግርሞ ሆነ በምልክት ለመግባባት ይችግራቸዋል፡፡
3. ማህበራዊ ግንኙነት መፍጠር መክበድ ይታይባቸዋል። ኦቲዝም ያለባቸዉ ሰዎች የሎሎችን ሰዎችን ስሜቶች
4. የሚደጋገም ባህሪያት/የተለመዱ ነገሮችንን መዉደድ፤ ለነገሮች ባልተለመደ መልኩ ሲሆኑ ስመሜታዊ መሆን የሆነ ፍላጎት ላይ ከመጠን በላይ ማተኮር እና ጭንቀትን ለማስወገድ አዲስ ነገር እና አከባቢ አይፈልጉም
5. ለ አከባቢያቸዉ (ስሜት ህዋሳት (ብርሃን፣ ድምጽ፣ ሽታ፣ ቀለም፣ ይዘት፣ ህመም፣ ባላንስ፣))በጣም ከፍ ያለ ወይም ምንም በቂ የሆነ ምላሽ ያለመስጠት
6. ተደጋጋሚ የሆነ ትርጉም የማይሰጥም ሆነ የማይገባ ቃላት ወይም ድምጽ ወይም እንቅስቃሴ መደጋገም
የኦቲዝም መንስኤው ምንድነው?
ብዙውን ጊዜ ግን የችግሮቹ መንስኤ ይሄ ነዉ ተብሎ በዉል አይታወቅም፡፡ ነገር ግን ለዚህ ችግር አጋላጭ የሚንላቸው ሁኔታዎች አሉ ለምሳሌ፡- ዘረ መል እና አከባቢ (ኬሚካል፣ አና እናቶች በእርግዝና የሚጋለጡባቸዉ ነገሮች)
በእድሜ ከገፉ በኋላ መዉለድ (ይሄኛዉ ከዘረመል መዛባትጋር ለሚገናኙት ሊያጋልጥ ይችላል )
አራርቆ አለመውለድ
የልጆች ያለጊዜያቸው መወለዱ
እንዲሁም በቤተሰብ ውስጥ ተመሳሳይ ችግር ያለበት የቤተሰብ አባል መኖር
ስምምነት ላይ ያልተደረሱ መንስኤዎች አሉ፡- (ክትባት፣ የምግብ አለርጂ፣ የለያዩ መድሃኒቶች፣ የአካባቢ ብክለት)
የኦቲዝም ምርመራ
ምርመራ ማለት የኦቲዝም በሰዎች ላይ መኖር እና አለመኖርን የማረጋገጫ መንገድ ሲሆን፤ የተወሰኑ መስፈርቶችን በመጠቀም የሚካሄድ ነዉ። ብዙ ጊዜ ምርመራውን የሚያካሄደዉ ባለሙያ ስለኦቲዝም የዳበረ ልምድ ያለዉ መሆን ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም ምርመራዉ በተለያዩ ባለሙያዎች ጥምረለኦት ቢደረግ መልካም ነዉ፡፡ በሚቀጥለዉም ጊዜ ሲመረመር በተሻለ ባለሙያ ቢመረመር ይመከራል።
ኦቲዘም ዉስጥ የሚካተቱ ችግሮች እንደ ክብደታቸዉ በ 3 ይከፈላሉ።
ኦቲዝም በማህበራዊ ግንኙነት ላይ፣ በተግባቦት ላይ ከሚያደርሰው ተፅዕኖ አንፃር 3 አይነት ደረጃዎች አሉት
Level 1፡- የምንላቸው መጠነኛ የሆነ የሌላ ሰው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የኦቲዝም ተጠቂ ልጆች ናቸው
Level 2፡- በዚህ ደረጃ ላይ ያሉት የኦቲስቲክ ተጠቂዎች ከሰዎች ጋር ለመግባባት፣ ራሳቸውን ለመጠበቅ ከፍተኛ የሆነ የሌላ ሰው ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል
Level 3፡- በዚህ ደረጃ ላይ ያሉት ደግሞ መጠነኛ የሆኑ ነገሮች ለማድረግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የሌላ ሰው ድጋፍ ይጠይቃሉ
የኦትዚም መፍትሄ ምንድነዉ ?
ኦቲዝምን በተለያዩ ዘዴዎች መደገፍ ይቻላል፡- ለኦቲዝም ተጠቂወች የሚሰጠው ህክምና አላማው የኦቲዚም ምልክቶችን በመቀነስ ያላቸውን ችሎታ በመደግፍ ልጆች ቢያንስ ራሳቸውን ችለው እንዲንቀሳቀሱ ማሰቻል ነው። ለዚህም የተለያዩ የመግባባት ክህሎትና የባህሪ ለዉጥ ህክምናዎች፡- የልጁን ማህበራዊ፣ ቋንቋና የባህሪ ችግሮች ላይ የሚሰሩ ብዙ ፕሮግራሞች/መርሃግብሮች አሉ፡፡ የተወሰኑት ፕሮግራሞች የልጁን የሚያስቸግሩ ባህሪያቶችን ለመቀነስና አዳዲስ ችሎታዎችን ማስተማር ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ህፃናቱ በማህበራዊ ግንኙነታቸዉ ላይ እንዴት መሆን/ምን መተግበር እንዳለባቸዉ ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር እንዴት መግባባት እንደሚችሉ ትኩረት ያደርጋል፡፡
ትምህርት፡- ኦቲዝም ያለባቸዉ ህፃናት በደንብ ለተቀረጸ የትምህርት መርሃግብር ጥሩ የሆነ አቀባበል አላቸዉ፡፡ የተዋጣላቸዉ ፕሮግራሞች በዉስጣቸዉ ብዙ መርሃግብሮችን የሚይዙ ሲሆን ይህም የልጁን ማህበረዊ፣ የመግባባት ክህሎትና ባህሪዉ ላይ ያተኮሩ ይሆናሉ፡፡
ቤተሰብ ተኮር ህክምና፡- ወላጆችና ሌሎች የቤተሰቡ አባላት የልጁን የመግባባት ክህሎት፣ችግሮችን የመፍታት ችሎታ ለማዳበር እንዲሁም በየቀኑ የሚጠቀምበትን የመግባባት ክህሎቱን ለማሳደግ በሚረዳዉ መልክ እንዴት አብረዉ መጫወትና መግባባት እንደሚችሉ ማስተማር ያፈልጋል፡፡
መድሃኒት፡- ዋናዎቹን የህመም ምልክቶች የሚያሻሽል መድሃኒት እስከአሁን ባይገኝም ምልክቶቹን ለመቆጣጠር የሚረዱ የተወሰኑ መድሃኒቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ አንታይዲፕሬሳንትና አንታይሳይኮቲክ
ስለኦቲዝም መልካም እይታ
አለማችንን እጅግ የቀየሩ አብዛኞቹ ኦቲዝም እንዳለባቸዉ ይነገራል ወይም ባህሪዉ ይታይባቸዋል።
ለምሳሌ፡-
1. የአለማችን ሃብታሙ ሰዉ Elon Musk
2. ሳይንቲስት Nicola Tesla (3000 ግኝቶች በ 986 ምድብ)
3. በአንድ ቀን የታወቀች ድምጻዊ Susan Boyle ለ 10 ዓመታት በከፍተኛ ሽያጭ የተሸጠላት
4. እነዚህ ለምሳሌ ያነሳኋቸዉ ከእጅግ ብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸዉ።
አብዛኞቹ በማህበረሰብ የተሻለ ምግባር ያላቸዉ ሰዎችም ከነዚሁ ሰዎች ናቸዉ
70 በመቶ የሚሆኑ ኦቲዝም ያለባቸው የተወሰነ ስራ ላይ የአዕምሮ አቅማቸዉ ከፍተኛ ከሆኑቱ መካከል ይገኛሉ። በሙዚቃ በሒሳብ በቴክኖሎጂ በስነ-ጥበብ እና በምህንድስና መስኮች ዉስጥ አብዛኞቹ የተዋጣላቸዉ ስራ የሰሩት ከነዚህ ሰዎች ብዞዎቹ ናቸዉ። ማህበረሰቡም ሐቀኞች ናቸው፣ ማጭበርበር፣ ማስመሰል ወይም መዋሸት አይፈልጉም፣ ምን ያመጣብኛል የሚለዉን አይጨነቁበትም።
ማጠቃለያ ምክር
ከ10 ልጆች 7 ወይ እይታዉ፣ ምናቡ፣ ማስተዋል አቅሙ ወይም ድምጽ ወይም ጥቃቅን ነገሮችን መለየት አቅም ወይም ረጅም ጊዜ ማተኮራቸዉ አንድ ነገር እንዲሰሩ ስለሚያስችላቸዉ ጊዜ ወስዶ ልጆቻቸዉን ማወቅ እጅግጉን ለልጆችም ሆነ ለቤተሰብ ይረዳል፣ ልጆቹም በልዩ ችሎታቸዉ አንድ ነገር ላይ ዉጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል።
መልካም ጤና!
ዶ/ር ተመስገን እንዳለዉ
Getachw Girma
June 5, 2022 at 2:02 pm
Good