Connect with us

ሀገር ዉስጥ

ከውጪ ከሚገቡ ካንፓኒዎች ጋር በጋራ መስራት ቢቻል የኮንስትራክሽን ዘርፉን ማሻደግ ይቻላል …

Published

on

featured
Photo: Social Media

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ከውጪ ከሚገቡ ካንፓኒዎች ጋር በጋራ መስራት ቢቻል የኮንስትራክሽን ዘርፉን ማሻደግ ይቻላል ሲል ለአዋሽ ራድዮ ተናገሩ::
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በዘንድሮዉ የ2014 የበጀት አመት ከ40 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ የኮንስትራክሽን ዉል 50 የግንባታ ፕሮጀክቶችን እያካሄደ እንደሆነ ከዚህ በፊት መግለፁ የሚታወስ ነዉ:: ተቋሙ ከሀገር ዉስጥና ከዉጪ የሚገቡ በዘርፉ የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ጋር ዉልን በመፈራረም በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የኮንስትራክሽን ዘርፉ እንዲያድግ እየሰራ ይገኛል:: ይሁን እንጂ የተጀመሩ የተለያዩ የመሰረተ ልማቶች በወቅቱ ሲጠናቀቁ አይታይም::

በአሁኑወቅት አለም ወደ አንድ መንደር ከመምጣቷጋር ተያይዞ በሀገራችን የተለመደዉን የኮንስትራክሽን የአሰራር ስርአት በማዘመን ከዉጪ ሀገር ከሚገቡ ኢንቨስተሮች ጋር በጋራ በመስራት ከሮቦቲክ ኢንዱስትሪዉ ለመድረስ ዲጂታላይዝድ የሆነ መንገድ መጠቀም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮናስአያሌዉ ለአዋሽ ራድዮ ተናግረዋል:: ሀገራችን አሁን ካለችበት የፀጥታ አለመረጋጋት ተያይዞ ወደሀገር ዉስጥ የሚገቡ ኢንቨስተሮች ስጋት እንዳይኖርባቸዉ ምን አይነት ቅድመ ዝግጅት ተደርጎል ስንል ዋና ስራ አስኪያጁን ጠይቀናቸዋል:: ሀላፊዉም የኛሀገር ኢንቨስተሮች የልምድ ልዉዉጥ በማድረግ አዳዲስ ስረዎችን መስራት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታዎች ይፈጠርላቸዋል ብለዋል::

በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ3 ሚሊዮን ላላነሱ ዜጎች የስራ እድል እንደሚመቻችላቸዉ መረጃዎች ያመላክታሉ:: ይህንን ተከትሎ ከዉጭ የሚገቡ ካንፖኒዎች የራሳቸዉን ባለሙያ ይዘዉ ስለሚመጡ ለሀገርዉስጥ ስራ ፈላጊ ዜጎች እድሉ ጠባብ አይሆንም ወይ ብለን ለአቶ ዮናስ ጥያቄ አንስተናል:: በማከልም ወደሀገር የሚገቡ ኢንቨስተሮች በምን አይነት መንገድ ሊገቡ ታስቧል ሲል አዋሽ ራድዮ ጠይቋል::
ዳይሬክተሩም ለዜጎች ምቹና የተሻለ የስራ እድል ይፈጠርላቸዋል ሲሉ ምላሻቸዉን ሰጥተዋል:: ከዉጪ ሀገራት ገሚገቡ ኢንቨስተሮች ጋር በጋራ ሆኖመስራቱ ለሀገር ዉስጥ ኢንቨስተሮች ምቹ የዉድድር ጊዜ ቢፈጥርም ለረጅም አመታት የተጓተቱ በርካታ ግንባታዎች መኖራቸዉን መረጃዎች ይጠቁማሉ:: ከዚሁጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የተጀመሩ የኮንስትራክሽን ስራዎችን በወቅቱ ባለማጠናቀቁ ከ3.2 ቢሊዮን ብር በላይ የግብር እዳ እነደተሰረዘለት የሚታወስነዉ::
በዳኛቸዉ መላኩ

ሀገር ዉስጥ

የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህጻናት ከመወለዳቸው በፌት የሚከሰት ችግር ሲሆን በእርግዝና ወቅት የህጻኑ/የህጻኗ ከንፈር ወይም ላንቃ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሳይገጥም ሲቀር የሚፈጠር ክፍተት /ስንጥቅ ማለት እንደሆነ የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ ።

Published

on

የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህጻናት ከመወለዳቸው በፌት የሚከሰት ችግር ሲሆን በእርግዝና ወቅት የህጻኑ/የህጻኗ ከንፈር ወይም ላንቃ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሳይገጥም ሲቀር የሚፈጠር ክፍተት /ስንጥቅ ማለት እንደሆነ የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ ። በአለማችን ላይ በየአመቱ ከ170.000 በላይ ህጻናት ከከንፈር እና ከላንቃ መሰንጠቅ ጋር ይወለዳሉ ። በአፍሪካ ውስጥም ከ32.000 ህጻናት በላይ በየአመቱ ከዚሁ ችግር ጋር ይወለዳሉ ። እንዲሁም ደግሞ በሃገራችን ኢትዮጵያ በየአመቱ ከ3000 በላይ ህጻናት ከከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ ጋር ይወለዳሉም ተበሏል። ይህም ህጻናቱ ለአመጋገብ ፣ለአተነፋፈስ እንዲሁም ለአነጋገር እክሎች ያጋልጣቸዋል ነው የተባለው ። ስማየል ትሬን በአለማችን የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ጋር ለተወለዱ ህጻናት የማስተካከያ ቀዶ ጥገና በነፃ የሚሰጥ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው ። ስማይል ትሬን ከሰን ኢኮ አርት ፎር ሶሻል ደቨሎፕመንት ጋር በመተባበር “ሙቪንግ ስማይል” የተሰኘ የአስፋልት ላይ ባቡር መሰል መኪና በማዘጋጀት፤ አገር አቀፍ የከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጉዞ በይፉ መጀመሩን የሰን ኢኮ አርት ፎር ሶሻል ደቨሎፕመንት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤፍሬም በቀለ ተናግረዋል። ከ1999 ጀምሮ በአለማችን ላይ የክንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ላጋጠማቸው 1.5 ሚሊየን ህጻናት ቀዶ ጥገና በነጻ አድረገዋል ተብሏል ። በኢትዮጵያም ከ 2007 ዓ.ም ጀምሮ ከ32.000 ህጻናት እና ወጣቶች በላይ የነጻ ቀዶ ጥገና ህክምና እና አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛልም ነው የተባለው ። ስማይል ትሬን በኢትዮጵያ ከ2007 ጀምሮ ከ32 ሺሕ ህጻናት እና ወጣቶች በላይ የነፃ ቀዶ ጥገና ህክምና እና አገልግሎት መስጠቱን የገለጹት በምስራቅ አፍሪካ የስማይል ትሬን ረዳት ፕሮግራም አስተባባሪ ዶ/ር ቤተል ሙሉጌታ ሲሆኑ፤ ከዚህም በተጨማሪም ድርጅቱ ከከንፈር እና ላንቃ ጋር ተያይዞ ነጻ የጥርስ ህክምና፣ የአመጋገብ ምክር፣ የንግግር ህክምና (speech therapy)፣ የማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ድጋፍ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን የያዘ ኹሉን አቀፍ የአገልግሎቶችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ዶ/ር ቤተል አክለውም ስማይል ትሬን በአገር ውስጥ ለሚገኙ የግል እና የመንግስት ሆስፒታሎች እና ሀኪሞች የቀዶ ጥገና ህክምና ስልጠናዎችን በመስጠት ዘላቂ የሆነ መፍትሄዎችን እዚሁ ባሉ የጤና ባለሙያዎች እንዲሰጥ እያደረገ እንደሚገኝም አስረድተዋል። የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ጋር ተያይዞ ችግር ያለባቸው የማህበረሰብ ክፍሎችም፤ ድርጅቱ የነጻ ጥሪ ማዕከል 9889 ላይ በነጻ በመደወል ለህክምናው መመዝገብ፣ መረጃ ማግኘት እና መማር እንደሚችሉ ተገልጿል።
በመቅደላዊት ይግዛው

Continue Reading

ሀገር ዉስጥ

በአዲስ አበባ በክርና ፕላስቲክ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 8 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን እንደተቻለ 2 ሚሊዮን ብር የተገመተ ንብረት መውደሙ ተገለፀ ።

Published

on

በአዲስ አበባ በክርና ፕላስቲክ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 8 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን እንደተቻለ 2 ሚሊዮን ብር የተገመተ ንብረት መውደሙ ተገለፀ ።

በአዲስ አበባ ከተማ ሰኞ ምሽት 1ሰዓት ገደማ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታዉ ቃሊቲ ኢንደስትሪ መንደር ውስጥ በክርና ፕላስቲክ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 2 ሚሊዮን ብር የተገመተ ንብረት መውደሙን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል። የደረሰዉን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ሶስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ሃያ አንድ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች መሰማራታቸውን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለአዋሽ ሬዲዮ ተናግረዋል።

አደጋውን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት መፍጀቱን አስታውቀዋል። የእሳት አደጋዉ ተስፋፍቶ አደጋዉ በደረሰበት ፋብሪካ ከዚህ የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስና በአካባቢዉ ባሉ ፋብሪካዎች እንዳይዛመት ማድረግ ተችሏል ያሉ ሲሆን ። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹ ባደረጉት ርብርብም 8 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን እንደተቻለ እና አደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም። የአደጋው የመነሻ ምክንያት በመጣራት ላይ ይገኛል በለዋል ።

በመጨረሻም ባሳለፈነው ቅዳሜና አሁድ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 እና ወረዳ 12 ክፍቱን በተተወ ዉሀ በአቆረ ጉድጓድ ዉስጥ እድሜያቸዉ 12 እና 25 የሆኑ ታዳጊና ወጣት ህይወታቸዉ ማለፉ ተገልጿል ። በአቃቂ ወረዳ 1 እድሜዉ 25 ዓመት የሆነ ወጣት ወንዝ ዉስጥ ገብቶ ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስከሬኑን አዉጥተዉ ለፖሊሰ አስረክበዋል ነው የተባለው ። ሌላኛዉ አደጋ እለተ እሁድ 10 ሰዓት ገደማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 12 ታዳጊዎች ተቆፍሮ ክፍቱን የተተወና ዉሀ ባቆረ ጉድጓድ ዉስጥ ዋና ለመዋኘት ከሄዱ ሶስት ታዳጊ ተማሪዎች መካከል እድሜዉ 12 ዓመት የሆነው የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ታዳጊ ዋና ለመዋኘት ገብቶ ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።

የዚህ ታዳጊ አስከሬን በፍለጋ የተገኘዉ ሰኞ ማለዳ ነዉ። አስከሬኑንም ፖሊስ ተረክቧል። በአዲስ አበባ የሚገኙ ወንዞችና በተለይም ክፍቱን የተተዉ ዉሀ ያቆሩ ጉድጓዶች እየተበራከቱ በመምጣታቸዉ ወላጆች ታዳጊ ልጆቻቸዉ እንዲሁም ወጣቶች በወንዞችና ዉሀ ያቆሩ ጉድጓዶች አካባቢ የሚኖራቸዉን እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ ማድረግ ያስፈልጋል። በ2014 ዓ.ም ክፍቱን በተተዉና ወሀ ባቆሩ ጉድጓዶች ዉስጥ እድሜያቸዉ 7 እና 15 የሚገመት ታዳጊዎች በእነዚህ ወሀ ባቆሩ ጉድጓዶች ዉስጥ ገብተዉ ህይወታቸዉን ማጣታቸው የሚታወስ ነው ።

በያዝነዉ በ2015 ዓ.ምም መስከረምና ጥቅምት ወር 3 ታዳጊዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል። ችግሩ ረጅም አመታትን ያስቆጠረና እየቀጠለ የመጣ ችግር በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ እሙን ነው ። እንዲህ ባለዉ አደጋም በየአመቱ በአማካይ 12 ታዳጊዎች ህይወታቸዉን ያጣሉም ተብሏል ።

በመቅደላዊት ይግዛው

Continue Reading

ሀገር ዉስጥ

ኢትዮጵያ ለአለም ገበያ ከምታቀርበው የቡና ምርት ዉስጥ 55 በመቶ የሚሆነዉ ከደረጃ በታች መሆኑ ተገለፀ።

Published

on

ኢትዮጵያ ለአለም ገበያ ከምታቀርበው የቡና ምርት ዉስጥ 55 በመቶ የሚሆነዉ ከደረጃ በታች መሆኑ ተገለፀ።
ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት የጀርባ አጥነት ሆኖ እያገለገለ ያለዉ የቡና ምርት ለሀገሪቱ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ከማስከገኘቱ በተጨማሪ ሩብ ለሚሆነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መተዳደሪያ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ።
ከስድት ሺህ በላይ የቡና ዝርያ እንዳላት የሚነገርላት ኢትዮጵያ እስካሁን እየተጠቀመችዉ ያለዉ የቡና ዝርያ በጣት የሚቆጠር ብቻ ነዉ ተብሏል ።
ሀገሪቱ ለቆላዉም ለደጋዉም ለወይናደጋዉም ለሶስቱም አይነት የአየር ንብረት ተሰማሚ የሆነ የቡና ዝርያ ቢኖራትም ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም በተለያዩ ምክንያቶች እያገኘች እንደልሆነ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ በለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ አንስተዋል።
ለዚህም ማሳይ ደግሞ በዝንድሮው አማት ከተለያዩ አለም ሀገራት ለአለም ገበያ ከቀረበዉ 174 ሚሊዮን በላይ ኬሻ ቡና ኢትዮጵያ ማቀረብ የቻለችዉ 5 ሚሊዮን ብቻ ነዉ ያሉት ዳይሬክተሩ ይህም ካለን የቡና ሀብት እና ተስማሚ የአየር ንብረት አንጻር ሲታይ በእጅጉ የወረደ ነዉ ብለዋል።
ይህም ሀገሪቱ ያላትን ሀብት በአግባቡ አለመጠቀሟ በምጣኔ ሃብቷ ላይ እና በዘርፉ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተነግሯል።
ኢትዮጵያ በያመቱ ለአለም ገበያ የምታቀርበዉ ቡና መጠኑ እየጨመረ ቢመጣም ከዉጪ ንግዱ የምናገኘዉ የገቢ መጠን ግን በእጅጉ ወርዷል ብለዋል፡፡
የአለም የቡና ገበያ እና የኢትዮጵያ ቡና ገበያ በምንያክል መልኩ ነዉ እየሄደ ያለዉ ስንል ላደረግነዉ ጥናት የኢትዮጵያ ቡና ተስፋ ሰጪ አይደለም የሚል ግኝት ላይ መድረሳቸዉን ዳይሬክተሩ ተናግራዋል ፡፡
ለዚህም ምክኒያት ደግሞ ኢትዮጵያ በብዛት የምታመርተዉ ቡና ደረጃ አምስት ወይም ሂዉጅ የሚባሉ ቡናዎች በጨረታ እና በኒዎርክ ገበያዎች ላይ የሚሸጡ መሆናቸዉን ተናግረዋል ፡፡
እነዚህ ቡናዎች ደረጃቸዉም እጅግ የወረደ በጫራታ የማይሸጡ ተደራድረን እንኳን ለመሸጥ የማይሆኑ ናቸዉ ሲሉም አከለዋል ፡፡ እነዚህ ቡናዎች በአለም ገብያ ከሚቀርቡ የኢትዮጵያ ቡናዎች 55 በመቶዉ ድርሻ የሚዙ እንደሆኑም ተነግሯል፡፡
ኢትዮጵያ በአለም ገበያ በሰፔሻለለቲ ደረጃ የምትሸጠዉ 15 በመቶ ብቻ ነዉ፡፡ ይህን ችግር ቀርፈን የቡናዎቻችንን ደረጃዎች ማሻሻል ካልቻልን በሚጠበቀዉ ልክ ከዘርፉ የሚገኘዉን የዉጭ ምንዛሬ ማሳደግ ያዳግታል ብላዋል።
የኢትዮጵያ ቡና አሁን ላይ በሶስት የተለያዩ የሰዉ ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮች እንደተደቀኑበትም ባለስጣኑ አመላክቷል ፡፡
በዚህም አንደኛ የአለም የቡና ዋጋ መዋዠቅ ሲሆን ይህም አረሶ አደሩ የቡና ዋጋ በቀነሰ ቁጥር ከቡና ምርት ወደ ሌላ ምርቶች ለመግባት ይገደዳል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ የአየር ንብረት ለዉጥን እንደችግር ያነሱት ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያ በብዛት የምታመርተዉ የአረቢካ ቡና ስለሆነ ይህም የቡና ዝርያ በሙቀት ሰለሚጠቃ የአለም ሙቀት በአንድ ዲግሪ በጨመረ ቁጥር የቡና ምርት ተፈላጊነት በእጅጉ እንደሚቀንስ አመላክተዋል፡፡
በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ የሃገሪቱ የደንን መመናመን ለዘርፉ ከፍተኛ ስጋቶች መሆናቸዉ በተግዳሮትነት ተወስቷል፡፡
ያሬድ እንዳሻዉ

Continue Reading

በብዛት የተነበቡ