Connect with us

ጤና

ኦቲዝም በሽታ ወይስ ልዩ ችሎታ?

Published

on

featured
Photo: Awash FM 90.7

ኦቲዝም አንድ በሽታ ነው ማለት አይቻልም። በአጠቃላይ ተመሳሳይ መገለጫ ያላቸው ከአእምሮ እድገት መዛባት (ከአብዛኛዉ ሰዉ መለየት) ጋር የተያያዙ ችግሮች የጋራ ስም ነው። ኦቲዝም የሚለው አጠራር ከግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “አውቶ” ማለትም የአንድ ሰው እኔነት (ራስ) ከሚለው ሲሆን፣ ኦቲዝም የተባለበት ምክንያት ይህ ሁኔታ ያለባቸዉ ሰዎች አብዛኛው ዓለማቸው በራሳቸው ስለሚሽከረከር ነው፤ የፈጠሩት የራሳቸዉ ምናባዊ አለምም ስለምኖራቸዉ ነዉ።
አብዛኛዉ ሰው ውስጣዊውንና ውጫዊውን ማለትም የግሉን አና ከሌሎች ጋር ያለዉን ዓለም አመጣጥኖ ነው የሚኖረው። ኦቲዝም ያለባቸው ግን ልክ ሳጥን ውስጥ እንዳለ ሰው ብዙውን ጊዜ የሚያሳልፉት በራሳቸው ጭንቅላት ውስጥ ነው። ከዚህም የተነሳ ለሰው ግራ የሚያጋባና ለመረዳት አስቸጋሪ የሆነ የባህርይ፣ የቋንቋና የማህበራዊ ግንኙነት ሁኔታዎች ይታዩባቸዋል።

ሁሉም ልጆች በተመሳሳይ ደረጃ ጉድለት ስለማይኖራቸው ኦቲዝም ያለበት እያንዳንዱ ልጅ አንድ አይነት ሊሆን አይችልም። ከ 1994 እስከ ሜይ 2013 ኦቲዝም አምስት የተለያዩ የኦቲዝም መጠሪያ አይነቶች የነበሩት ሲሆን ፤ እነርሱም፡- አስፐርገርስ ሲንድሮም (ሊትል ፕሮፌሰር)፣ በሌላኛው ጫፍ ደግሞ Pervasive Development Disorder, Chilhood Disintegrative Disorder, PDD – NOS, Genetic ASD) ይባሉ ነበር። ነገር ግን ከዚያ በኋላ አምስቱም በአንድነት ኦቲዝም ስፔክትረም ዲኦርደርስ በመባል ይታወቃሉ።
በቁጥር ደረጃ ስናጥ በአሜሪካ በ 1990 ከ 10,000 አንዱ ነበር ዛሬ ግን ከ 44 ሰዎች አንዱ ኦቲዝም አለበት እኛ ሀገር ግን ወደ አንድ ሚልየን አከባቢ የሚጠጉ እንደሚኖሩ ይገመታል። በኦቲዝም የተጠቁ ሰዎች መግባባት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ግንኙነት ለመፍጠርና ለመግባባት ይቸገራሉ፡፡ በተጨማሪም ለተወሰኑ ነገሮች ብቻ ፍላጎት ማሳየት በተደጋጋሚ ባህሪያትን ማሳት ከሚታይባቸዉ ባሀሪዎች መካከል ናቸዉ፡፡
ሁሉም ኦቲዝም ያለባቸዉ ሰዎች ይነስም ይብዛም አብዛኞቹ ላይ ከሚታዩ ችግሮች መካከል፡-

1. ውስን የሆነ ስሜታዊነት፡- የራሳቸዉንም መግለጽ ይሁን የሌሎችን መረዳት ይከብዳቸዋል

2. (ቋንቋ)ግባባት አለመቻል፡- በንግግርሞ ሆነ በምልክት ለመግባባት ይችግራቸዋል፡፡

3. ማህበራዊ ግንኙነት መፍጠር መክበድ ይታይባቸዋል። ኦቲዝም ያለባቸዉ ሰዎች የሎሎችን ሰዎችን ስሜቶች

4. የሚደጋገም ባህሪያት/የተለመዱ ነገሮችንን መዉደድ፤ ለነገሮች ባልተለመደ መልኩ ሲሆኑ ስመሜታዊ መሆን የሆነ ፍላጎት ላይ ከመጠን በላይ ማተኮር እና ጭንቀትን ለማስወገድ አዲስ ነገር እና አከባቢ አይፈልጉም

5. ለ አከባቢያቸዉ (ስሜት ህዋሳት (ብርሃን፣ ድምጽ፣ ሽታ፣ ቀለም፣ ይዘት፣ ህመም፣ ባላንስ፣))በጣም ከፍ ያለ ወይም ምንም በቂ የሆነ ምላሽ ያለመስጠት

6. ተደጋጋሚ የሆነ ትርጉም የማይሰጥም ሆነ የማይገባ ቃላት ወይም ድምጽ ወይም እንቅስቃሴ መደጋገም

የኦቲዝም መንስኤው ምንድነው?

ብዙውን ጊዜ ግን የችግሮቹ መንስኤ ይሄ ነዉ ተብሎ በዉል አይታወቅም፡፡ ነገር ግን ለዚህ ችግር አጋላጭ የሚንላቸው ሁኔታዎች አሉ ለምሳሌ፡- ዘረ መል እና አከባቢ (ኬሚካል፣ አና እናቶች በእርግዝና የሚጋለጡባቸዉ ነገሮች)

በእድሜ ከገፉ በኋላ መዉለድ (ይሄኛዉ ከዘረመል መዛባትጋር ለሚገናኙት ሊያጋልጥ ይችላል )

አራርቆ አለመውለድ

የልጆች ያለጊዜያቸው መወለዱ

እንዲሁም በቤተሰብ ውስጥ ተመሳሳይ ችግር ያለበት የቤተሰብ አባል መኖር

ስምምነት ላይ ያልተደረሱ መንስኤዎች አሉ፡- (ክትባት፣ የምግብ አለርጂ፣ የለያዩ መድሃኒቶች፣ የአካባቢ ብክለት)

የኦቲዝም ምርመራ
ምርመራ ማለት የኦቲዝም በሰዎች ላይ መኖር እና አለመኖርን የማረጋገጫ መንገድ ሲሆን፤ የተወሰኑ መስፈርቶችን በመጠቀም የሚካሄድ ነዉ። ብዙ ጊዜ ምርመራውን የሚያካሄደዉ ባለሙያ ስለኦቲዝም የዳበረ ልምድ ያለዉ መሆን ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም ምርመራዉ በተለያዩ ባለሙያዎች ጥምረለኦት ቢደረግ መልካም ነዉ፡፡ በሚቀጥለዉም ጊዜ ሲመረመር በተሻለ ባለሙያ ቢመረመር ይመከራል።

ኦቲዘም ዉስጥ የሚካተቱ ችግሮች እንደ ክብደታቸዉ በ 3 ይከፈላሉ።
ኦቲዝም በማህበራዊ ግንኙነት ላይ፣ በተግባቦት ላይ ከሚያደርሰው ተፅዕኖ አንፃር 3 አይነት ደረጃዎች አሉት
Level 1፡- የምንላቸው መጠነኛ የሆነ የሌላ ሰው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የኦቲዝም ተጠቂ ልጆች ናቸው
Level 2፡- በዚህ ደረጃ ላይ ያሉት የኦቲስቲክ ተጠቂዎች ከሰዎች ጋር ለመግባባት፣ ራሳቸውን ለመጠበቅ ከፍተኛ የሆነ የሌላ ሰው ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል
Level 3፡- በዚህ ደረጃ ላይ ያሉት ደግሞ መጠነኛ የሆኑ ነገሮች ለማድረግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የሌላ ሰው ድጋፍ ይጠይቃሉ

የኦትዚም መፍትሄ ምንድነዉ ?

ኦቲዝምን በተለያዩ ዘዴዎች መደገፍ ይቻላል፡- ለኦቲዝም ተጠቂወች የሚሰጠው ህክምና አላማው የኦቲዚም ምልክቶችን በመቀነስ ያላቸውን ችሎታ በመደግፍ ልጆች ቢያንስ ራሳቸውን ችለው እንዲንቀሳቀሱ ማሰቻል ነው። ለዚህም የተለያዩ የመግባባት ክህሎትና የባህሪ ለዉጥ ህክምናዎች፡- የልጁን ማህበራዊ፣ ቋንቋና የባህሪ ችግሮች ላይ የሚሰሩ ብዙ ፕሮግራሞች/መርሃግብሮች አሉ፡፡ የተወሰኑት ፕሮግራሞች የልጁን የሚያስቸግሩ ባህሪያቶችን ለመቀነስና አዳዲስ ችሎታዎችን ማስተማር ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ህፃናቱ በማህበራዊ ግንኙነታቸዉ ላይ እንዴት መሆን/ምን መተግበር እንዳለባቸዉ ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር እንዴት መግባባት እንደሚችሉ ትኩረት ያደርጋል፡፡
ትምህርት፡- ኦቲዝም ያለባቸዉ ህፃናት በደንብ ለተቀረጸ የትምህርት መርሃግብር ጥሩ የሆነ አቀባበል አላቸዉ፡፡ የተዋጣላቸዉ ፕሮግራሞች በዉስጣቸዉ ብዙ መርሃግብሮችን የሚይዙ ሲሆን ይህም የልጁን ማህበረዊ፣ የመግባባት ክህሎትና ባህሪዉ ላይ ያተኮሩ ይሆናሉ፡፡
ቤተሰብ ተኮር ህክምና፡- ወላጆችና ሌሎች የቤተሰቡ አባላት የልጁን የመግባባት ክህሎት፣ችግሮችን የመፍታት ችሎታ ለማዳበር እንዲሁም በየቀኑ የሚጠቀምበትን የመግባባት ክህሎቱን ለማሳደግ በሚረዳዉ መልክ እንዴት አብረዉ መጫወትና መግባባት እንደሚችሉ ማስተማር ያፈልጋል፡፡
መድሃኒት፡- ዋናዎቹን የህመም ምልክቶች የሚያሻሽል መድሃኒት እስከአሁን ባይገኝም ምልክቶቹን ለመቆጣጠር የሚረዱ የተወሰኑ መድሃኒቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ አንታይዲፕሬሳንትና አንታይሳይኮቲክ

ስለኦቲዝም መልካም እይታ
አለማችንን እጅግ የቀየሩ አብዛኞቹ ኦቲዝም እንዳለባቸዉ ይነገራል ወይም ባህሪዉ ይታይባቸዋል።
ለምሳሌ፡-

1. የአለማችን ሃብታሙ ሰዉ Elon Musk

2. ሳይንቲስት Nicola Tesla (3000 ግኝቶች በ 986 ምድብ)

3. በአንድ ቀን የታወቀች ድምጻዊ Susan Boyle ለ 10 ዓመታት በከፍተኛ ሽያጭ የተሸጠላት

4. እነዚህ ለምሳሌ ያነሳኋቸዉ ከእጅግ ብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸዉ።

አብዛኞቹ በማህበረሰብ የተሻለ ምግባር ያላቸዉ ሰዎችም ከነዚሁ ሰዎች ናቸዉ
70 በመቶ የሚሆኑ ኦቲዝም ያለባቸው የተወሰነ ስራ ላይ የአዕምሮ አቅማቸዉ ከፍተኛ ከሆኑቱ መካከል ይገኛሉ። በሙዚቃ በሒሳብ በቴክኖሎጂ በስነ-ጥበብ እና በምህንድስና መስኮች ዉስጥ አብዛኞቹ የተዋጣላቸዉ ስራ የሰሩት ከነዚህ ሰዎች ብዞዎቹ ናቸዉ። ማህበረሰቡም ሐቀኞች ናቸው፣ ማጭበርበር፣ ማስመሰል ወይም መዋሸት አይፈልጉም፣ ምን ያመጣብኛል የሚለዉን አይጨነቁበትም።

ማጠቃለያ ምክር
ከ10 ልጆች 7 ወይ እይታዉ፣ ምናቡ፣ ማስተዋል አቅሙ ወይም ድምጽ ወይም ጥቃቅን ነገሮችን መለየት አቅም ወይም ረጅም ጊዜ ማተኮራቸዉ አንድ ነገር እንዲሰሩ ስለሚያስችላቸዉ ጊዜ ወስዶ ልጆቻቸዉን ማወቅ  እጅግጉን ለልጆችም ሆነ ለቤተሰብ ይረዳል፣ ልጆቹም በልዩ ችሎታቸዉ አንድ ነገር ላይ ዉጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል።
መልካም ጤና!
ዶ/ር ተመስገን እንዳለዉ

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ሀገር ዉስጥ

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የክትባት ዘመቻ ከአርባ ሁለት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን የክተባቱ ተጠቃሚ እንደሆኑ ተገለፀ።

Published

on

featured
Photo: Social Media

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የክትባት ዘመቻ ከአርባ ሁለት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን የክተባቱ ተጠቃሚ እንደሆኑ ተገለፀ። በመዲናዋም ሁለት መቶ አሰር ሺህ ሰዎች ደግሞ የሶስተኛው ዙር ክትባት እንደወሰዱም ነው የተነገረው ። በአለም አቀፍ ደርጃ የተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አለምን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ ጥሏት ቆይቷል ። ወረርሽኙ ያስከተለው ምጣኔ ሃብታዊም ሆነ የጤና ተግዳሮቶች በዘላቂነት ሳይፈቱ አሁንም ድረስ ቀጥለዋል ።

ለችግሩ እንደ ጊዜአዊ መፍትሔ እየተወሰደ የሚገኘው በዙር የሚሰጠው ክትባት በቻ መሆኑ ይታወቃል ። በኢትዮጵያም 3ኛው ዙር የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ክትባት መሰጠት መጀመሩን በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ 19 ጉዳዮች አሰተባባሪ የሆኑት ዶክተር መብራቱ ማሴቦ ከአዋሽ ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስታወቀዋል ። የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከዚህ በኃላም ላልተወሰነ ጊዜ አብሮን የሚቀጥል ወረርሽኝ መሆነኑን በመገንዘብ ማህበረሰቡ የተለመዱ ጥንቃቄዎችን በማድረግ እራስን በመጠበቅ ህይወትን ማስቀጠል እንደሚገባም ነው የገለፁት ። በክትባት ዘመቻውም ከ አርባ ሁለት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ከተባቱን የተከተቡ ሰለመሆናቸውም ነግረውናል። ከዚህ ቀደምም ክትባቱን ወስደው ስድስት ወር ያለፋቸው ሰዎችም እንደገና የመያዝ እድላቸው ስፊ ስለሆነ በየ ስድሰት ወሩ የሚሰጠውን የማጠናከሪያ ክትባት በድጋሚ መወሰድ እንዳለባቸውም አሳስበዋል ።

በሁሉም ወረዳዎች ኮቪድን ከሌላ በሽታ ጋር አጣምሮ ህክምና መስጠት የሚቻልበትን ሁኔታም ለማመቻቸት እየሰራን እንገኛለንም ነው ያሉት ። የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የእናቶች እና ህፃናት ዳይሬክቱሬት ዳይሬክተር ወይዘሪት ስንዱ መኩሪያ ለአዋሽ ራዲዮ እንደገለፁት ክትባቱ መሰጠት ከጀመረበት ከሰኔ አስራ ሶስት ጀምሮ ሁለት መቶ አስር ሺህ ስዎች የሶስተኛው ዙር ክትባት ተጠቃሚ እንደሆኑ ተናግረዋል ይህም የዕቅዱን 82በመቶ ማሳካት እንደተቻለ አሰረድተዋል ።

አያይዘውም ከመጀመሪያው ዙር የክትባት ዘመቻ ጀመሮ እንደ ትልቅ ተግዳሮት ያነሱት በማህበረሰቡ ዘንድ ሰለ ክትባቱ የተሳሳተ አመለካከት ስላለ ግንዛቤ ለመፍጠር ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየሰራን እንገኛለን በለዋል ። በመጨረሻም ማህበረሰቡ በዙር እየተሰጠ ያለውን ክትባት በመውሰድ እና እራሱ በመጠበቅ ወረርሽኙን መከላከል እንደሚገባም ተመላክቷል ።
በመቅደላዊት ይግዛው

Continue Reading

ጤና

የራምዜ ሀንት ሲንድረም ምንነት እና መፍትሄ

Published

on

featured
Photo: Social Media

ባለፈው ሳምንት ሊያካሂድ የነበረውን ኮንሰርት የሰረዘው የ28 ዓመቱ ድምጻዊ ጀስቲን ቢበር፣ ከፊል ፊቱ ፓራላይዝድ እንደሆነ ተናግሯል። ኢንስታግራም ላይ በለቀቀው ቪድዮ በአንደኛዉ የፊቱ ገጽ ላይ የደረሰዉን ጉዳት ለተከታዮቹ ሲያስረዳ ነበር። አንደኛዉም የፊቱ ክፍል ሙሉ በሙሉ ፓራላይዝድ እንደሆነ ያስረዳል። ጀስቲን ቢበርን የገጠመው ራምዜ ሀንት ሲንድረም ወይም ሄርፐስ ዞስተር ኦቲከስ የተሰኘ ህመም ነዉ። (Ramsey Hunt Syndrome) የሚባለዉ ህመም የሚከሰተዉ ፊታችንን ገጽ ላይ የሚያገለግለዉ ነርቭ በሻይረስ ሲጠቃ ነዉ። ይሄም ህመም የተጠቃዉን ፊት ፓራላይዝ ማድረግ እና በዚያም ጆሮ መስማት ያለመቻልን ሊያስከትል ይችላል።

ህመሙን የሚያስከትለዉ ቫይረስ ቫሪሴላ ዞስተር ቫይረስ ሲሆን በራምዜ ሀንት ሲንድረም ጊዜ የሚጠቃዉ ነርቭ ደግሞ ፋሻል ነርቭ የተሰኘዉ የፊታችን ነርቭ ነዉ። ይሄ ህመም የሚከሰተዉም ሁኔታ መጀመሪያ በቫይረሱ ተጠቅቶ በነበረ ሰዉ አካል ዉስጥ በአንዱ ነርቭ ዉስጥ ተደብቆ የነበረዉ ቫይረስ መልሶ መራባት ሲጀምር ነዉ። ስለዚህ ራምሴ ሀንት ሲንድረም ህመም ከሰዉ ወደ ሰዉ የሚተላለፍ አይደለም። የሄንን ህመም የሚያመጣዉ ቫይረስ ቺከን ፖክስን እና ሺንግልስ የተሰኙ ህመሞችንን የሚያመጣዉ ቫይረስ ነዉ። የበሽታ መከላከል አቅማቸዉ ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎች፣ ሰዉነታቸዉ በቂ እረፍት በማያገኙ ሰዎች ላይ እና በእድሜያቸዉ ገፋ ያሉ ሰዎች ላይ ህመሙ ሊጸና ይችላል። ቫይረሱን በድጋሚ እንዲራባ የሚያሰደረጉ ነገሮች በግልጽ ባይታወቁም በዋናነት የሰዉነት እረፍት ማጣት እና የበሽታ መከላከል አቅም በተለያዩ ሁኔታዎች መቀነስ ይጠቀሱበታል።

የህመሙ ምልክቶች:- ሁለት ዋና ዋና የሆኑ የህመሙ ምልክቶች መካከል ቀላ ያሉ እና ሲነኩ የሚያሙ የጆሮ አከባቢ ቆዳ ዉሃ መቋጠር እና በታመመዉ ፊት ፓራላይዝ መሆን ናቸዉ። እነዚህ ምልክቶች አብዛኛዉን ጊዜ አብረዉ ቢከሰቱም ብቻቸዉን ሊታዩ ይችላሉ። በተጨማሪም ከታዩ ምልክቶች መካከል፤ የጆሮ ህመም፣ መስማት ያለመቻል፣ ጆሮ ዉስጥ መጮህ፣ አንደ አይንን መክደን ያለመቻል፣ ማዞር፣ የመቅመስ ችግር፣ የአፍ እና አይን መድረቅ ሊከሰቱ ይችላሉ።
መፍትሄ:- አብዛኛዉን ጊዜ ህመሙ ታካሚዉ በሚሰጠዉ ታሪክ ላይ በመመስረት የሚታወቅ ነዉ። ይሄ ህመም በተወሰኑ ሰዎች በራሱ ጊዜ በጥቂት ሳምንታት ዉስጥ ሊሻል የሚችል ቢሆንም በአንዳንዶቹ ላይ ለዘላቂ ችግር ሊዳርግ ይችላል። ስለዚህ በህክምናዉ ከሚመከሩ መፍትሄዎች መካከል የሰዉነት ብግነትን የሚቀንሱ ከስቴሮይድ ዝርያ የሚመደቡ መድሃኒቶች እና የጸረ ቫይረሽ መድሃኒቶች ይገኙበታል። ለህመሙም ማስታገሻ እና እንደየ ታዩ ምልክቶች እርዳታ ሊያስፈልግ ይችላል። መከላከያ መንገዱም የቺከን ፖክስ ክትባት በህጻንነት መዉሰድም እንደሆነ ህክምናዉ ሳይንስ ይጠቁማል። በተጨማሪም ከ50 ዓመት እድሜ በላይ ላሉትም የሺንግልስን ህመም ክትባት እንዲወሰድ ይመክራል።
ሰላማችሁ ይብዛ!
ዶ/ር ተመስገን እንዳለዉ

Continue Reading

ጤና

የወር አበባ ህመም 5 የቤት ዉስጥ መፍትሄዎች

Published

on

featured
Photo: Awash FM 90.7

የወር አበባ የሚከሰተዉ በየወሩ ለጽንስ ዝግጁ የነበረዉ የማህጸን ግድግዳ ጽንስ ባለመካሄዱ የተነሳ በመርገፉ ነዉ። በዚህ ጊዜ የተለያዩ ከፍተኛ የሆኑ የሆርሞን (በሰዉነት ዉስጥ ያሉ መግባቢያ ንጥረ ኬሚካሎች) ለዉጦች ይስተናገዳሉ። በነዚህም ሁኔታ ከፍተኛ የሆኑ የሚመረቱ ፕሮስታግላንዲን የተሰኙ ሆርሞኖች መንስኤነት ህመም በማህጸን ግድግዳ ላይ ሊሰማ ይችላል። ሆርሞኖቹ የሚመረቱት ከማህጸን ግድግዳ ላይ የነበረዉ እድገት እንዲወገድ ነዉ። ይሄም ደግሞ ከወትሮዉ የተለየ የማህጸን ጡንቻዎች መኮማተርን ያስከስታል። በማህጸን መኮማተሩም የተነሳ የተፈረካከሰዉ የማህጸን ግድግዳ በደም መልክ ከማህጸን እንዲወገድ ያስችላል።

ከባድ የሆነ የወር አበባ ህመም ሊጋለጡ ከሚችሉት ሴቶች መካከል በዕድሜ ወጣትነት ከ 30ዓመት በታች መሆን፣ ከባድ ደም የሚፈሳቸዉ ሴቶች፣ የወር አበባ የተለያየ ጊዜ የሚመጣባቸዉ ሴቶች፣ በቤተሰብ ከባድ የወር አበባ ህመም ያላቸዉ ሴቶች፣ በወጣትነት እድሜ የወር አበባ ማየት የጀመሩ ሴቶች ማለትም ከ 11 ዓመት በፊት እና የሚያጨሱ ሴቶች ይገኙበታል።
የወር አበባ በየጊዜዉ የሚከሰት ጤናማ የተፈጥሮ ሂደት በመሆኑ በተለያዩ የህመም ደረጃም ቢሆን እየተቸገሩ ያሉ ሴት እህቶቻችን ከስር የተዘረዘሩትን መፍትሄዎች በማድረግ ህመሙን ማቅለል ይችላሉ። ህመሙ ከባድ ከሆነ ግን ባለፈዉ ክፍል ባስቀመጥነዉ ጽሁፍ ላይ መኖራቸዉ መለየት ያለባቸዉን ችግሮች መለየቱ ይመከራል። እነዛ ችግሮች ያለመኖራቸዉ ከተረጋገጠ በኋላ ግን ህመሙን ለመቀነስ ከስር የተዘረዘሩትን መፍትሄዎች በቤት ዉስጥ ማድረግ ይቻላል።

  1. በቂ ዉሃ መጠጣት፡ በሆርሞኖቹ ከመጠን በላይ መመረት የተነሳ የሚካሄደዉን ከፍተኛ የሜታቦሊክ ስርዓት እና ተረፈ ምርት ከሰዉነት ለማስወገድ በዊ ዉሃ መጠጣት ይመከራል። በቂ ዉሃ ማለት ቢያንስ በቀን ከሁለት እስከ ሶስት ጊዜ እንዲሸኑ የሚያስችል ያህል ነዉ።
  2. ሞቅ ባለ ዉሃ የተሞላ የዉሃ መያዣዎችን በሆድ ላይ ማድረግ፡- ሞቅ ያለ ዉሃ የያዙ የዉሃ መያዣዎችን በሆድ ላይ በማድረግ መያዝ፣ ከሙቀተ የተነሳ የማህጸን ጡንቻዎችን ለቀቅ ስለሚያደርግ፣ ህመሙን ሊቀንስ ይችላል።
  3. እንቅስቃሴ ማድረግ፡ ጥናቶች አንደሚያሳዩት በሳምንት 3 ቀን ቢያንስ ለ 30 ደቂቃ መካከለኛ የሚባል ደረጃ ድረስ የሚደርስ ኤሮቢክ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሴቶች ላይ ህመሙ እጅጉን እንደቀነሰ ያሳያሉ። በህሙ ሰዓትም ዎክ ወይም ዮጋ መስራቱ የተዋሰነ ህመሙን ይቀንሳል።
  4. ቡና፣ ሻይ እና የጨዉ መጠን መቀነስ፡ እነዚህ ሁሉ ከሰዉነት ላይ ዉሃን በማስወገድ ህመሙን ሊያባብሱ ስለሚችሉ አይመከሩም። ዉሃን ከማስወገድም በተጨማሪ የጡንቻዎችን መኮማተር ስለሚጨምሩ ህመሙን ሊያብሱ ይችላሉ። በሻይ ቅጠል ከሚፈሉ ሻይ ይልቅ የዝንጅብል ቅሽር ሻይ መጠጣቱ የተወሰነ ህመሙን ይቀንሳል።
  5. ሞቅ ባለ የዉሃ ገንዳ ዉስጥ መቀመጥ፡ ከላይ ሞቅ ያለ ዉሃን ሆድ ላይ እንደመያዙ ይሄም ከሙቀት የተነሳ የማኅጸን ግድግዳ ጡንቻዎችን ለቀቅ በማድረግ ህመም ሊያስታግሸኝ ይጭለል።
    በነዚህ ቀላል እና ቤት ዉስጥ ሊደረጉ በሚችሉ መፍትሄዎች የማይሻል ከሆነ ሌሎች ችግሮችን መኖር ያለመኖራቸዉን ማረጋገጡ ይመከራል። እስኪረጋገጡ ድረስ እና ህመሙ ከአቅም በላይ ከሆነ የህመም ማስታገሻዎችን ለአጭር ጊዜ ብቻ ግዴታ ከሆነ መጠቀሙ ይመከር ይሆናል። ሁል ጊዜ መዉሰዱ ግን በረጅም ጊዜ ሌሎች የሰዉነት ክፍላችን ላይ ጉዳት ስለሚያመጣ እነሱን ማቖየቱ ይመከራል።

መልካም ጤና!
በዶ/ር ተመስገን እንዳለዉ

Continue Reading

በብዛት የተነበቡ