በኢትዮጵያ በለፈዉ አንድ አመት በተከሰተዉ የሰሜኑ ክፍል ጦርነት ምክንያት በርካታ ነግሮች የሂወት ኡደታቸዉን መቀየራቸዉ ይታወቅ ነዉ ፡፡
በተለይ በኢንቨስት መንት ዘርፍ ተሰማርተዉ የነበሩ አልሚ ባለ ሀብቶች ከፍተኛ ችግር እንደ ገጠማቸዉ የሚታወስ ነዉ ፡፡
ችግሩን የከፋ የያደርገዉ ደግሞ የዜጎችን ሰላም ለማስጠበቅ ተብሎ የተጣለዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተከትሎ እንቅስቃሴዎች መገደባቸዉ የምጣኔ ሀብቱ እንዲዳከም ምክንያት ሆኗል ሲሉ የዘርፋ ባለሙያዎች ይናገራሉ ፡፡
በመሆኑም በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት የዉጭ ባለ ሀብቶችም ወደ ሀገር ቤት ገብተዉ ኢንቨስት እንዳያደርጉ ማነቆ ሆኖባቸዉ ቆይቷል ተብሎል ፡፡
የኢንቨስትመንት መዳከም ደግሞ የሀገርን ምጣኔ ሀብት ከሚያደክሙ ግንባር ቀደም ሁኔታዎች መካከል ቀዳሚዉ ነዉ ቢባል ማጋነን አይሆንም ፡፡
በመሆኑም በሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ቀናት ለስደስት ወራት ታዉጆ የነበረዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በ ሶስት ወራት የአፋፃፀም ቆይታ በኋላ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መነሳቱ ይሚታወስ ነዉ ፡፡
አዋሽ ሬድዮም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱ ለተቀዛቀዘዉ የምጣኔ ሀብት ምን አስተዋፅኦ አለዉ ስንል የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችን አነጋግረን ጉዳዩን ተመልክተነዋል ፡፡
የጦርነቶችም ሆነ የተፈጥሮ አደጋዎች ሲከሰቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊጣል እንደሚችል የተለመደ ነዉ ፡፡
አወጁ ሲጣል የእንቅስቃሴ ገደቦች ስለ ሚኖሩ የምጣኔ ሀብቱን ሊጎዳዉ እንደ ሚችል ይታመናል ይሁን እንጅ መንግስት ከምጣኔ ሀብት በፊት የዜጎች በህይወት መኖርን ቀድሚያ ስለ ሚሰጥ አዋጁ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል ሲሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዉ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርህ ተስፋ ይናገራሉ ፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱ ጥቅሙ በተለይ ወደ ዲፕሎማሲያዊ ጥቅም የሚያመዝን ይሆናል ፡፡
በመሆኑም አወጁ በመጣሉ ሲቃወሙ የነበሩ የተለያዩ ሀገራት አሁን ላይ ጥሩ ጅማሮ መሆኑን አስተያየት እየሰጡ በመሆ ናቸዉ ምጣኔ ሀብቱን የሚደግፋ የተለያዩ ብድሮችን እና ልገሳዎችን ሊያደርጉ የሚችሉበትን እድል ይፋጥራል ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህሩ አቶ መዚድ ናሲር ናቸዉ ፡፡
አወጁ መነሳቱ ለማልማት በዝግጅት ላይ ያሉ የዉጭ ሀገር ባለሀብቶችንም ሆነ የሀገር ዉስጥ ባለሀብቶች ስነልቦና ዳግም መጠገን የሚያስችል እና የደህንነት ምቾት እንዲሰማቸዉ የሚያደርግ ነዉ ሲሉ ዶክተር ቆስጠንጢኒዮስ ጨምረዉ ይናገራሉ ፡፡
አወጁ ተጥሎ መቆየቱ ከደህንነት አንፃር ቢሆንም በኢቨስትመንትም ሆነ ሌሎች የምጣኔሀብቱን የሚደግፋ የነበሩ ስራዎች እንዲቆሙ እና እንዲዳከሙ አድርጎት ቆይቷል ፡፡
አሁን ላይ በመነሳቱ ግን በሁሉም መስክ የተቀዛቀዘዉን ኢኮኖሚ ከፍ ለማድረግ አንድ እርምጃ ጠቀሜታ ይኖረዋል ያሉት ደግሞ ሌላኛዉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አቶ ያሬድ ሀይለመስቀል ናቸዉ ፡፡
አወጁ መነሳቱ ኢንቨስትመንቱን እንዲያገግም ቢረዳዉም በዋናነት ከዚሁ ጋር ተየይዞ ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባዉ ያልተገባ የቢሮክራሲ አስራር አሁንም ለአልሚ ባለሀብቶች ማነቆ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል ሲሉ አቶ ያሬድ ይጨምራሉ ፡፡
የትኛዉም ባለሀብት ለማልማት ሲመጣ ከምንም ነገር በላይ የሚያስቀድመዉ የሚያለማበትን ሀገር የሰላም ሁኔታ በመሆኑ መንግስት አሁንም የሰላም ሁኔታዎች ላይ ሊያስብበት ይገባል በማለት አቶ መዚድ ናሲር ይገልፃሉ ፡፡
አንድ ሀገር በምጣኔ ሀብት የዳበረች እንድትሆን እና እራሷን ከተረጅነት ማእቀፍ ለማዉጣት አስተማማኝ ይምጣኔ ሀብት ሊኖራት እንደሚገባ እሙን ነዉ ፡፡
ይህን ለማድረግ ደግሞ ወጥ የሆነ ዘላቂ የሆነ ሰላም በሀሉም አካባቢዎች ሊረጋገጥ ይገባል ሲሉ ባለሙያዎች አስተያየታቸዉን ሰጠዋል ፡፡