Connect with us

አለም አቀፍ

በሰሜናዊ የህንድ ውቅያኖስ ፤በደቡባዊ ኤዢያ ከ22 ሚሊየን በላይ ህዝብ የያዘችው ስሪላንካ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሟ በደግ እየተነሣ አይደለም፡፡

Published

on

pixle

በሰሜናዊ የህንድ ውቅያኖስ ፤በደቡባዊ ኤዢያ ከ22 ሚሊየን በላይ ህዝብ የያዘችው ስሪላንካ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሟ በደግ እየተነሣ አይደለም፡፡በሀገሪቱ በተፈጠረው የኑሮ ውድነት ምክኒያት ዜጎች መንግስትን እያስጨነቁ ነው፡፡ፕሬዚዳንት ጎታባይ ራጃፓክሳ እና ጠቅላይ ሚኒስቴር ራኒል መላ ያሉትን ውሳኔ እያሳለፉ ቢቆዩም ፤የኮሎምቦ ነዋሪዎችን ግን ሊያረጋጋ አልቻለም፡፡ ቀደም ሲል ተረጋግቶ ይመራ የነበረው መንግስት በምዕራባውያን ሴራ መፍረሱ ቢነገርም ፤እነርሱ ግን አሁንም ስሪላንካን ለመታደግ እንሠራለን ፤እናግዛለን እያሉ ይገኛሉ ፡፡በስሪላንካ የምግብ ዋጋ ንረት 75% ደርሷል ፡፡በኬሚካል ማዳበሪያ ላይ የተጣለው ማዕቀብና ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ ዕቃዎች መወደድ በኮሎምቦ ዜጎች ላይ ተደራራቢ ችግር እየሆነባቸው ቀጥሏል ፡፡ የደዜቷ ሀገር መንግስት በተፈጠረው ችግር ምክኒያት የመንግስት ሠራተኞች በሣምንት ለ4 ቀናት ሌላ ሥራ እንዲሠሩ ወስኗል ፡፡በዚህም የነዳጅ እጥረቱን ለማረጋጋት የሚያመጣው ለውጥ አለ የሚለው መንግስት ሠራተኞች በፍጥነት የሚደርሱ የምግብ ዓይነቶችን እንዲያመርቱ ያግዛል ብሏል፡፡ በደሴቷ ሀገር ስሪላንካ 1ሚሊየን የሚደርስ የመንግስት ሠራተኛ አለ፡፡እነዚህ ሠራተኞች በአብዛኛው በከተሞች የሚኖሩ ሲሆን ወደ ገጠራማው ክፍል በመጓዝ አማራጭ የሥራ መስኮች ላይ የሚሠማሩ ከሆነና ምግብ ነክ ምርት ላይ የሚያተኩሩ ከሆነ የሦስት ወር ደመወዛቸው እንደሚከፈላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል ፡፡ በሌላ በኩል ለረጅም ግዜ ያለደመወዝና በግል ሥራቸው በገጠራማው የሀገሪቱ ክፍሎች የሚሣተፉ ካሉም ከአምስት ዓመታት በኋላ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ እስከማድረስ የሚያደርግ ውሳኔ በካቢኔው ተላልፏል፡፡ ይህንን ማድረግ መንግስት ለምግብ ፤ለሀይል እና መድሐኒት ግዚ የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ እንዲቀንስ ያስችለዋል ተብሏል፡፡ የተ.መ.ድ የኮሎምቦ መንግስት የሚያሣልፋቸው ውሳኔዎች በሀገሪቱ ያለውን ቀውስ እያረጋጋ አይደለም ሲል ወቅሷል ፡፡ድርጅቱ በሣምንቱ መጀመሪያ እንዳሣወቀው በከፋ የድህነት ተጋላጭነት ውስጥ ላሉና ከ1 ሚሊየን ለሚበልጡ የሀገሬው ዜጎች በአፋጣኝ የሚደርስ የ47 ሚሊየን ዶላር ዕርዳታ አፅድቋል ፡፡መንግስት ግን እርዳታ ብሎ ያቀረበው የገንዘብ መጠን በጣም ከፍተኛ ነው ፡፡የችግሩ መነሻ በዋናነት የገቢ ዕቃዎች መወደድ በመሆኑ ፤ያንን ክፍተት ሊሸፍን የሚችል የ5 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ እንዲደረግለት ጠይቋል፡፡ስሪላንካን በቻልነው መጠን እናግዛለን ያለችው አሜሪካ በገንዘቡ መብዛት ወደ ኋላ እያለች ነው፡፡ከጠቅላይሚኒስቴሩ ራኒ ጋር በስልክ የተነጋገሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒዮ ብሊንከን አሜሪካ የምታደርገውን እርዳታ በቀጥታ ከመናገር ይልቅ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም/ IMF/ በኩል ስለሚደረገው እገዛ አትኩሮት ሠጥተው ተናግረዋል ፡፡የሀገራቸውን አቋም ግን በደፈናው እገዛ ታደርጋለች ሲሉ ሀሣባቸውን አያይዘው ገልፀዋል ፡፡ስሪላንካ መንግስት ጋር በርቀት ሲነጋገር የነበረው IMF ከ5 ቀናት በኋላ ልዑካኑ ስሪላንካ ኮሎምቦ ይገባሉ ፡፡ በዚህም ስሪላንካ በሚያስፈልጋት እገዛ ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መንግስት በሀገር ውስጥ ፤የውጭ አጋር የሚባሉ አካላትም የየበኩላቸውን ጥረት ቢያደርጉም ፤ኮሎምቦ ግን ልትረጋጋ አልቻለችም፡፡በዋና ከተማዋና በሌሎች ታላላቅ ከተሞች የሚደረጉ የተቃውሞ ሠልፎች አልበረዱም ፡፡አሁን በሚደረጉ ሠልፎች ደግሞ ባለሥልጣናቱ ሥራቸውን በገዛ ፍቃዳቸው እንዲለቁ እየተጠየቀ ነው፡፡ በሌላ በኩል የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከፍተኛ ኃላፊዎች ወደ ስሪላንካ ሊያመሩ መሆኑን ደይሊ ኒውስ ዘግቧል፡፡ስሪላንካ ካለባት ዘርፈ ብዙ ቸግሮች አንዱ የምግብ እጥረት ነው፡፡ከዚህ የወቅቱና የቀጣይ ሥጋት ከሆነው ችግሯ ጋር እየተናነቀች ያለችው ሀገር መፍትሔ ቢገኝ በሚል መሪዎቹ የተ.መ.ድ የምግብ ፕሮግራም ከፍተኛ ኃላፊዎችን ወደ ሐገራቸው ጠርተዋል፡፡ የፕሮግራሙ መሪዎችም የጠቅላይ ሚኒስቴር ራኒልን ጥሪ ተቀብለው ወደ ስሪላንካ እንደሚመጡ ፈጣን ምላሽ ሠተዋል ፡፡የምግብ እጥረቱ የተከሠተው በሀገሪቱ ያጋጠመውን የሩዝ ምርት መቀነስን ተከትሎ ነው ፡፡ለዚህ ምርት መቀነስ ደግሞ ፕሬዚደንት ራጃፓካሳ በኬሚካል ማዳበሪያ ላይ የጣሉት እቀባ መሆኑን ባለሙ ያዎች አስቀምጠው ነበር ፡፡ ታዲያ ጠቅላይሚኒስቴሩ ወደ ተ.መ.ድ ጥሪ ያቀረቡት የባለሙያዎቹን ቅድመ ማስጠንቀቂያ ከሠሙ በኋላ ነው፡፡አስተያየት ሠጪዎች ግን የፕሬዚደንቱ የኬሚካል ማዳበሪያ ማዕቀብ ካልተነሣ የስሪላንካ ችግር በእርዳታ የሚፈታ አይደለም እያሉ ይገኛሉ ፡፡ ትልቅ ለውጥ ያመጣል የተባለው የIMF ልዑክ በዋና ዳይሬክተሩ ዴቪድ ቤዝ ሌይ የሚመራ እንደሆነ ተናግሯል ፡፡ የተ.መ.ድ ለስሪላንካ የምግብ እጥረት በሚል የሚመደበው 47.2 ሚሊየን ዶላር ለህክምና ጉዳይ እንዲውል እየተጠየቀ ነው፡፡በስሪላንካ ከፍተኛ የሆነ የመዳኒት እጥረት ተከስቷል ፡፡በዚህ ምክኒያት የተ.መ.ድ የለቀቀው ገንዘብ ለዚህ ዘርፍ እንዲውል ተጠይቋል፡፡መንግስት ግን በህክምናው ረገድ የተፈጠረው ችግር ሌላ መላ ተበጅቶለታል እያለነው፡፡የህንድ መንግስት ባመቻቸው የመካከለኛ ግዜ የብድር አመላለስ ሥርዓት በስሪላንካ የተፈጠረውን የህክምና ችግር ለማቃለል ይሠራል ብሏል፡፡ በዚህም የተ.መ.ድ እና በሀገሪቱ ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ያስተባበሩት ገንዘብ የ1.7 ሚሊየን ዜጎችን ግዜያዊ ችግር ለመታደግ ይውላል ተብሏል ፡፡የስሪላንካ ችግር ቀደም ሲል የነበረው የሀገሪቱ ተወዳጅ መንግስት ይከተለው የነበረውን ፖሊሲ ሊቀይረው መቃረቡን አስተያየት ሰጪዎች ሠዎችን በማሳመኛነት አቅርበዋል፡፡ ወደ ስሪላንካ የሚመጣው ቡድን በዋናነት በሀገሪቱ ችግር ላይ ይነጋገራል ቢባልም የውስጥ አዋቂ ምንጮችን ጠቅሶ ደይሊ ኒውስ እንደዘገበው የልዑክ ቡድኑ የሀገሪቱ የፋይናንስ ፖሊሲ በሚቀየርበት ሁኔታ ላይ ይነጋገራሉ የሚል መረጃ ወቷል ፡፡ የፖሊሲ መቀየሩ የስሪላንካን መሠረታዊ ችግር ይፈታል ብለው ምዕራባውያኑ የፕሬዚዳንት ራጃፓክሳ መንግስትን አሣምነው እንደጨረሱ ተገልጿል ፡፡የዓለም የገንዘብ ተቋም (IMF)ቃል አቀባዩ ጌሪ ራይስ ይህንን ድብቅ አጀንዳ ቢይዙም ፤በኮሎምቦ ያለው ቀውስ በተለይም ፤የሠብዓዊ ቀውሱ ጉዳይ ያሣሥበናል የሚል አስተያየት ሠተዋል ፡፡ በአስተያየት ሠጪዎቹ ከ(IMF)ድብቅ አጀንዳ አንፃር በርከት ያሉ ተቃራኒ ሀሣቦች ቢሠነዘሩም ድርጅቱ ግን ልዑካን ለመላክ ዝግጅቱን ጨርሷል ፡፡ የህንዱ ዚ ኒውስ ደግሞ የስሪላንካ መንግስት ለህክምና መገልገያነት ከህንድ አገኘዋለሁ ካለው ብድር ባለፈ በዴልሂ መንግስት ተጨማሪ ብድር እንደሚቀርብ ገልጿል፡፡ በዘገባው 55ሚሊየን ዶላር እንደሚቀርብ የተነገረ ሲሆን እቀባ ያልተደረገበትን ማዳበሪያ ለማስገባትና የምግብ ችግርን ለመቀነስ ለሚሠሩ ሥራዎች ይውላልም ተብሏል፡፡
በዚህ ወር መጀመሪያ ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት /FAO/ከተ.መ.ድ/UNDP/ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር የተገናኙት ጠቅላይ ሚኒስቴር ራኒል የሀገራቸውን ጭንቅ አብራርተው ነበር፡፡ይህንን ተገንዝቤያለሁ ያለው የህንድ መንግስት የቅርብ አጋርነቱን ለመግለፅ ፈጣን ምላሽ መስጠቱ እያስሞገሰው ነው፡፡ጠቅላይሚኒስቴሩ በወቅቱ የተመራጭ ማዳበሪያዎች እና የነዳጅ እጥረት በሀገሪቱ የግብርና ምርት ላይ እክል የሚፈጥሩ ሁለት ከፍተኛ ችግሮች መሆናቸውን ተናግረው ነበር ፡፡ጠቅላይ ሚኒስቴር ራኒል እነዚህን ሁለት አንኳር ችግሮችንና ሌሎችንም ለመገላገል 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ ባለፈው ማክሠኞ ለሀገራቸው ፓርላማ ባቀረቡት መፍትሔ አመላካች ንግግር ላይ ጠቅሠዋል፡፡ ሀሣባቸውን ለፋይናንሻል ታይምስ የሰጡ ባለሙያዎች እንደሚሉት የስሪላንካ መጥፎ ግዜያቶች ገና ናቸው ብለዋል ፡፡ሀገራት በዚህ ዓይነት ችግር ውስጥ ሲወድቁ መፍትሄ ብለው የወሰዷቸው እርምጃዎች፤ለብተና አልያም ለእርስ በርስ ግጭት ሲዳርጋቸው መታየቱን ጋዜጣው ባለሙያዎችን ጠቅሶ ፅፏል ፡፡ የስሪላንካ የቅርብ ጎረቤት የሆነችው ሕንድ በሁለቱ ሀገራት መካከል በሚደረግ ንግድ ምክኒያት ብዙ እዳ ቆልላባታለች፡፡የናሬንድ ራሞዲ መንግስት ግን አሁንም ለስሪላንካ መንግስት ብድር ለመስጠት ወደ ኋላ አላለም ፡፡የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋምም ቢሆን የሚያስቀምጠው የድጋፍ ዓይነት ሊሆን የሚችለው አብዛኛው ብድር እንደሚሆን ይጠበቃል ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ ፡፡ የኮሎምቦ የውጭ ምንዛሬም ቢሆን ሀገሪቱ ወደ ብድር የምትገባበት ሌላኛው ማስጨነቂያ መሆኑ እየተገለፀ ነው፡፡ በዚህ ምክኒያት የተበደረችውና ባለፈው አፕሪል ወር ላይ ተመልሶ መጠናቀቅ የነበረበት 7 ቢሊየን ዕዳ የመጨረሻ ግዜው ተራዝሞላታል፡፡በንግድና በሌሎች ጉዳዮች የገባችበት እ.አ.አ እስከ 2026 መመለስ ያለበት 25 ቢሊየን ደርሷል፡፡ ስሪላንካ የዕዳ መመለስ አቅሟ በመዳከሙ ፤አንዳንዶች ደግሞ ሀብቷን በቀጣይ ለመቀራመት በማሠብ ከፍተኛ የዕዳ ቁልል ጭነውባታል፡፡አጠቃላይ የሀገሪቱ ዕዳ 51 ቢሊየን መድረሱም ታውቋል ፡፡ይህንን የተመለከቱ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ፤ስሪላንካ በአበዳሪዎቿ ልክ ልትቆራረስ ትችላለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ በተለይም ሕንድ ሀገሪቱን በከባድ ልትመልሰው በማትችለው ዕዳ ውስጥ ለመክተት የምታደርገው መሯሯጥ ቅርበቷን ተጠቅማ በግዛትነት ልትጠቀልል ያሠበች ይመሥላል ሲል ፋይናንሺያል ታይምስ አትቷል፡፡ ስሪላንካ እዚህ ሁሉ ችግር ወስጥ መግባቷ በቀደመው አገዛዝ ላይ የውስጥ አንድነት በማጣታቸው ነው ሲሉ ብዙዎች እየተናገሩ ነው፡፡ይህንን መሠል አደጋ ያንዣበባቸው መንግስታትና ሕዝቦችም ብዙ ሊማሩ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል ፡፡ፋይናንሻል ታይምስ አል-ጀዚራ ፣ዚኒውስ እና ሮይተርስ የዘገባው ምንጮች ናቸው ፡፡
በዚህ ወር መጀመሪያ ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት /FAO/ከተ.መ.ድ/UNDP/ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር የተገናኙት ጠቅላይ ሚኒስቴር ራኒል የሀገራቸውን ጭንቅ አብራርተው ነበር፡፡ይህንን ተገንዝቤያለሁ ያለው የህንድ መንግስት የቅርብ አጋርነቱን ለመግለፅ ፈጣን ምላሽ መስጠቱ እያስሞገሰው ነው፡፡ጠቅላይሚኒስቴሩ በወቅቱ የተመራጭ ማዳበሪያዎች እና የነዳጅ እጥረት በሀገሪቱ የግብርና ምርት ላይ እክል የሚፈጥሩ ሁለት ከፍተኛ ችግሮች መሆናቸውን ተናግረው ነበር ፡፡ጠቅላይ ሚኒስቴር ራኒል እነዚህን ሁለት አንኳር ችግሮችንና ሌሎችንም ለመገላገል 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ ባለፈው ማክሠኞ ለሀገራቸው ፓርላማ ባቀረቡት መፍትሔ አመላካች ንግግር ላይ ጠቅሠዋል፡፡ ሀሣባቸውን ለፋይናንሻል ታይምስ የሰጡ ባለሙያዎች እንደሚሉት የስሪላንካ መጥፎ ግዜያቶች ገና ናቸው ብለዋል ፡፡ሀገራት በዚህ ዓይነት ችግር ውስጥ ሲወድቁ መፍትሄ ብለው የወሰዷቸው እርምጃዎች፤ለብተና አልያም ለእርስ በርስ ግጭት ሲዳርጋቸው መታየቱን ጋዜጣው ባለሙያዎችን ጠቅሶ ፅፏል ፡፡ የስሪላንካ የቅርብ ጎረቤት የሆነችው ሕንድ በሁለቱ ሀገራት መካከል በሚደረግ ንግድ ምክኒያት ብዙ እዳ ቆልላባታለች፡፡የናሬንድ ራሞዲ መንግስት ግን አሁንም ለስሪላንካ መንግስት ብድር ለመስጠት ወደ ኋላ አላለም ፡፡የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋምም ቢሆን የሚያስቀምጠው የድጋፍ ዓይነት ሊሆን የሚችለው አብዛኛው ብድር እንደሚሆን ይጠበቃል ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ ፡፡ የኮሎምቦ የውጭ ምንዛሬም ቢሆን ሀገሪቱ ወደ ብድር የምትገባበት ሌላኛው ማስጨነቂያ መሆኑ እየተገለፀ ነው፡፡ በዚህ ምክኒያት የተበደረችውና ባለፈው አፕሪል ወር ላይ ተመልሶ መጠናቀቅ የነበረበት 7 ቢሊየን ዕዳ የመጨረሻ ግዜው ተራዝሞላታል፡፡በንግድና በሌሎች ጉዳዮች የገባችበት እ.አ.አ እስከ 2026 መመለስ ያለበት 25 ቢሊየን ደርሷል፡፡ ስሪላንካ የዕዳ መመለስ አቅሟ በመዳከሙ ፤አንዳንዶች ደግሞ ሀብቷን በቀጣይ ለመቀራመት በማሠብ ከፍተኛ የዕዳ ቁልል ጭነውባታል፡፡አጠቃላይ የሀገሪቱ ዕዳ 51 ቢሊየን መድረሱም ታውቋል ፡፡ይህንን የተመለከቱ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ፤ስሪላንካ በአበዳሪዎቿ ልክ ልትቆራረስ ትችላለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ በተለይም ሕንድ ሀገሪቱን በከባድ ልትመልሰው በማትችለው ዕዳ ውስጥ ለመክተት የምታደርገው መሯሯጥ ቅርበቷን ተጠቅማ በግዛትነት ልትጠቀልል ያሠበች ይመሥላል ሲል ፋይናንሺያል ታይምስ አትቷል፡፡ ስሪላንካ እዚህ ሁሉ ችግር ወስጥ መግባቷ በቀደመው አገዛዝ ላይ የውስጥ አንድነት በማጣታቸው ነው ሲሉ ብዙዎች እየተናገሩ ነው፡፡ይህንን መሠል አደጋ ያንዣበባቸው መንግስታትና ሕዝቦችም ብዙ ሊማሩ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል ፡፡ፋይናንሻል ታይምስ አል-ጀዚራ ፣ዚኒውስ እና ሮይተርስ የዘገባው ምንጮች ናቸው ፡፡

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

አለም አቀፍ

በኢትዮጵያ የክረምቱን መግባት ተከትሎ እያየለ የመጣው ጎርፍ ዓለም አቀፍ አጀብ አስከትሏል፡፡

Published

on

በኢትዮጵያ የክረምቱን መግባት ተከትሎ እያየለ የመጣው ጎርፍ ዓለም አቀፍ አጀብ አስከትሏል፡፡ከኛው ሀገር ክረምት አስቀድሞ በአብዛኛው ወሮቻቸው ዝናባማ የሆኑ ሀገራት ፤በመልካ ምድራዊ አቀማመጣቸው የተነሣ ከፍተኛ የሚባል የጎርፍ አደጋ ያጋጥማቸዋል፡፡የደቡብና መካከለኛው ኤዥያ ሀገራት ከዝናብ ወቅትና ከዓለም የአየር ንብረት መለወጥ ጋር ተያይዞ በሚመጣ የጎርፍ አደጋ ይጠቃሉ ፡፡ጥቃታቸው ግን መነሻው ምንም ይሁን ምን ምላሽ የሚያገኙበትና ድጋፍ የሚደረግበት መንገድ ከጉዳቱ በላይ በርካቶችን ያሣዘነ ነበር፡፡
የነዚህ አካባቢዎች ጉዳት አሁን እያየለ በመምጣቱና መደረግ ያለበት ድጋፍ ከፍ እያለ በመምጣቱ እነዚህ ተጎጂዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ በቸልታ መታለፍ የለላቸውም መባሉን ዘኒውስ ኔሽን ዘግቧል፡፡

ጎርፉ በቀጠናው ሀገራት በተለይ ሲል ሄትና ሉናምጋንጅ በተባሉ አካባቢው የከፋ ጉልበቱን እያሣረፈ ይገኛል፡፡በነዚህ አካባቢዎች ጎርፉ ከሚያስከትለው ቅፅታዊ አደጋ በተጨማሪ በውጤቱ አካባቢውን ቀድሞ ባልነበረ መልኩ ገደላማና የተበላሸ መልከዓ ምድር ይፈጥራል፡፡
በዚህም የአካባቢው ነዋሪዎች የቀድሞ የህይወት መሥመራቸው በእጅጉ የተቀየረና በአዲስ የሚጀምር እየሆነ ኑሯቸውን ሁሌም የድካም ያደርገዋል፡፡በተደጋጋመና አሠልቺ ፤እንዲሁም የበዛ እገዛ የሚሻው ኑሮአቸው ግን የሚደረግለት እገዛ በእጅጉ ያነሠ ነው፡፡
በደቡብ ኤዢያ ሀገራት 12 የሚደርሱ ግዛቶች መሠረተ ልማቶቻቸውን በአደጋው ምክኒያት ሙሉ ለሙሉ ወድሞባቸዋል፡፡በሀይል አማራጮቻቸው ፤የትራንስፖርት መስጫ መሥመሮቻቸውን ተነጥቀው በከባድ ጨለማና ችግር ውስጥ ለመሆን ተገደዋል፡፡ትምህርት ቤቶች መጠለያዎች ፤የህክምና መስጫ ተቋማት በተጎዱበት በዚህ አካባቢ ነዋሪዎቹ በአደገኛ የባህር ወሽመጥ ሥር በመሆን ቀጣዩን ዘግናኝ እልቂት እየተጠባበቁ መሆናቸውን የዜና ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡

በጥቂቱም ቢሆን የተጀመረው የረድኤት ሥራው ዝናብና ጎርፉ ባስከተለው የመሠረተ ልማት ውድመት ምክኒያት መስተጓጎል ጀምሯል፡፡
በሲልሄት አስማኒ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በኩል ሲደረግ የነበረው የሠብዓዊ እርዳታ መስጠቱ አሁን ተቋርጧል ፡፡ጎርፉ በአየር መንገዱ ማረፊያ መሠረተ ልማት ላይ ያደረሠው ጉዳት ሥራዎች በተፈለገው ልክ እንዳይሠሩ እያስተጓጎለ ነው፡፡
በቅርቡ ያሉ ጎረቤቶቻቸው የሚፈልጉትን ዓይነት ፣መጠንና ቀጣይነት ያለው እገዛ የሚያደርጉላቸው እነዚህ የደቡብ እስያ ሀገራት ዓለም አቀፍ ጥሪን አድርገዋል፡፡በቅርብ ያሉት ጎረቤቶቻቸው እነ ማይናማር ፣ኔፓል ፣ባንግላዲሽና ሌሎች በመሠል ችግር የሚሠቃዩ ሀገራት ናቸው፡፡እነዚህ ሀገራት በውስጣቸው በሚፈጠር ተደጋጋሚ የተፈጥሮ አደጋ በከባዱ የተፈተኑትና ለውጭ ጥሪ የሚተርፍ ሀብት ያላከበቱ ናቸው፡፡ከዛ ፈቅ ሲል በቅርብ ርቀት ያሉት ታይላንድ ፣ህንድና ቻይና ሲሆኑ እነዚህ ሀገራት ለተጎጂዎች እየሠጡት ያለው ምላሽ ያቅማቸውን ያህል አይደለም፡፡
ታይላንድ ለችግሩ ትኩረት ባለመስጠት የደሴት ሀገራቱን ጉዳት የቅርበቷን ያህል አልተከታተለችም ሲል ሳይንቲስትስ አለርት አስነብቧል፡፡
ህንድ ደግሞ ሠሞንኛው የውስጥ አለመረጋጋት ጉዳይዋ መጥሮ ይዟታል፡፡በዚህም ምክኒያት ለውጭ የዕርዳታ ጥሪዎች ምላሽ ለመስጠት አልቻለችም፡፡ከሆነም እያደረገች ያለችው ቀድሞውኑ ጣልቃ እንምትገባበት በምትታማበት የስሪላንካ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡በሌላ በኩል ህንድ በአሣም ግዛቷ በተከሠተው ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ 100 ሺዎችን አፈናቅሏል ፡፡በዚህ ዩ.ኤን ግዛት ከደረሠ አደጋ የሸሹ ሠዎች በአንድ የመቆያ ካምፕ ውስጥ ከ4500 በላይ ሆነው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡ይህም ሌላ ምክኒያት ተደርጎ ተወስዷል፡፡/ቻይናም ላሽ ቢሆን ከአቅም በታች በመሆኑ ሀገራቱ በእርዳታ እጦት ምክኒያት ከፍተኛ እልቂት ሊደርስባቸው እንደሚችል ተሠግቷል፡፡
የቻይና ምላሽ መቀዛቀዝ ግን በሀገሯ ካስተናገደችው ተመሣሣይ አደጋ ጋር የሚዛመድ ነው የሚል በጎ ምክኒያት ተቀምጦላታል፡፡
ቻይና ከነዚህ የአደጋ ጥሪ ካስተላለፉ ሀገራት አቅራቢያ የሚገኘው የጉዋንግ ግዛት ውስጥ ከፍተኛ ቁሣዊ ጉዳት ያደረሠ አደጋ ተከስቶባታል፡፡በዚህ ግዛት ውስጥ በግዙፍነቱ የሚታወቀውና ፒርል ተብሎ የሚጠራው ወንዝ በምዕተ ዓመቱ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሞልቶ አካባቢውን እንዳልነበር አድርጓል፡፡ከዚህ አካባቢ እንደ ህንዱ ግዛት ሁሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠዎች ተፈናቅለዋል፡፡
በዚህ አደጋ እስካሁን ከደረሠው እልቂት በተጨማሪ የግዛቱ ዋና ከተማና የንግድና ባህል መግለጫ በሆነችው ጉዋንግ ዞይ ከተማ ላይ ተጨማሪ ከባድ ኪሣራ ሊያመጣ እንደሚችል ተሠግቷል፡፡በዚህች ግዛት በቁሣቁስና መሠረተ ልማቶች ላይ የደረሠው አደጋ ሳይካተት በጎርፉ ምክኒያት በዚህ በተያዘው ሣምንት ብቻ 1.7 ቢሊየን ዩአን /153 ሚሊየን የምጣሜ ሀብት እንቅስቃሴ ኪሣራ መድረሱን የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡በቻይና ሌሎች ግዛትም የደረሠው ተመሣሣይ አደጋ በርካቶችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል፡፡ህንድ ፣ባንግላዲሽ ፣አሁን ጭንቅ ውስጥ የገቡት የደሴት ሀገራት ሌሎችም የመጣባቸውን የጎርፍ መዓት ከዓለም አየር ንብረት ለውጥ መከሠት ጋር አገናኝተውታል፡፡ቻይና ግን ሁለትና ከዛ በላይ በሆኑ አካባቢዎች የጎርፍ መጥለቅለቅ ቢገጥማትም ነገሩን ከከባቢ አየር ጋር አላገናኘችውም ፡፡
ታዲያ ቻይና በነዚህ አስጨናቂ ጉዳዮች ውስጥ በመሆኗ ነው የነ ሲልሂትን ጥያቄ ትኩረት ያልሠጠችው ሲሉ አስተያየታቸውን ለአል-ጀዚራ የሰጡ አካላት ተናግረዋል፡፡

እንዚህ የድረሱልን ጥሪ ያቀረቡ የደሴት ሀገራት የራሳቸውን እንጥፍጣፊ አቅም እየተጠቀሙ ይገኛሉ ፡፡ሲልሄት ወደ ሦስት ሚሊየን ከሚጠጋው ህዝቧ አብዛኛው በከፍተኛ የእዳ ሥጋት ውስጥ ይገኛል ሲሉ ባለሥልጣናቱ እየተናገሩ ነው፡፡
ስጋቱን ለመቀነስና ተጎጂዎችን ከተጨማሪ አደጋ ለመከላከል የሀገሪቱን የጦር ሀይል፤በሙሉ ንቅናቄ ውስጥ አስገብታለች ፡፡የአደጋ ግዜ ሠራተኞችና በጎ ግቃደኞች ንቅናቄውን በመቀላቀል የበኩላቸውን እየተወጡ ነው፡፡ይሁንና ይህ ሁሉ ተደምሮ ከደረሠው አደጋና ከደቀነው ሥጋት አኳያ በቂ ምላሽ አይሠጥም ሲሉ የሃገሪቱ መሪዎች በተደጋጋሚ እያሣወቁ ነው፡፡
የአደጋ ምላሽ ሰጪው አካል አቅም በተመናመነበት በዚህ ግዜ በደሴት ሀገራቱ የተከሠተው ጎርፍ አድማሱን እያሠፋ ፤ጉልበቱን እየጨመረ መምጣቱ ችግሩን የበለጠ አሳሳቢ አድርጎታል፡፡
እነዚህ ሀገራት ያሉበት አካባቢ ለሠው ልጅ እጅጉን ተስማሚ የሆነ የከርሰ ምድርና ገፀ ምድር የውሃ ሀብት የያዘ ነው፡፡በዚህም ለዘመናት በዚህ ረገድ የሚመጣ ችግር ነክቷቸው አያውቅም፡፡ይሁንና አሁን አደጋው ያስከተለው ጥፋት ምክኒያት የውሃ መሠረተ ልማቶች በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቷል ፡፡በዚህም ምክኒያት ነክቷቸው የማይውቀው የውሃና ውሃ ወለድ በሽታ ሊጎዳቸው እንደሚችል የባለሥልጣናቱን ግምት ያጋራው ዘኒውስ ኔሽን ዘግቧል፡፡

የአካባቢው ባለሥልጣናት ነዋሪዎችን ከአደገኛ ቦታዎች ለማራቅ አነስተኛ ጀልባዎች እየተጠቀመ እየሠራ ይገኛል፡፡ይህ ግን ብዙ ምልልስ የሚጠይቅና የጉዳቱ መጠን ከመስፋቱ ጋር ተያይዞ ውጤታማ ሥራ ያስገኛል የሚል ዕምነት አልተያዘም፡፡
በሀገራቱ ያሉ ምግባረ ሠናይ ድርጅቶች መንግስታቱ የሚያቀርቡት ጥያቄ መልስ ማግኘት አለበት ብለዋል፡፡መንግስታቱም ቀድመው ሽፋን ማግኘት ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት ለነዚሁ ሥፍራ ነዋሪዎች ቅድሚያ መሥጠት አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በዚህ ሁሉ የሀገራቱ ትርምስ ውስጥ ግን የተ.መ.ድ ያሳየው ቸልተኝነት ግን አስገራሚ ሆኗል፡፡አካባቢው ላይ የተፈጥሮ አደጋ ፣የምግብ እጥረት ፣የውሃና ውሃ ወለድ በሽታዎች ስጋት ቢሆኑም ፤የተ.መ.ድ በየትኛዎቹም የድርጅቱ ቅርንጫፎች በኩል የሠጠው ተስፋና ያደረገው እንቅስቃሴ የለም፡፡ይህም ድርጅቱን ትዝብት ውስጥየከተተ ሆኗል፡፡
ዓለም ላይ በርከት ያሉ ችግሮች ተፈጥረው ዓለም አቀፋዊ ጥሪ እየቀረበላቸው ነው፡፡

አፍጋኒስታን ከፍተኛ ና አንድ ሺ ገደማ ዜጎቿን ያሳጣ የመሬት መንቀጥቀጥ አናውጧታል ፡፡የታሊባን መንግስትም የደረሠበትን ችግር ለመቋቋምና ተጎጂዎችን ለመረዳት ሁሉም እንዲያግዘው ጠይቋል፡፡
በዩክሬን ጦርነት የተፈናቀሉ ዜጎችም ተደጋጋሚ ጥሪ እያስተላለፉ ነው፡፡ስፔን ለ5 ተከታታይ ቀናት በቆየ ሙቀት ተጨናንቃለች፡፡ሌሎችም በርከት ያሉ ሀገራት በደረሰባቸው ችግር ምክኒያት ዓለም አቀፋዊ ትብብር እየጠየቁ ነው፡፡የተ.መ.ድ ግን በዝምታ ያለፈው የደቡብ እስያ ሀገራትን ጥሪ ነው፡፡
ለእርዳታ ሀገር ፣አካባቢና ሁኔታ እንዲሁም የደጓሚዎቹን ይሁንታ ይጣባበቃል የሚባለው የተ.መ.ድ በዚህ ጥሪ ላይ ያሣየው ቸልተኝነት አጋልጦታል፡፡
አል-ጀዚራ ኒውስ ኔሽን የዘገባው ምንጮች ናቸው

 

Continue Reading

አለም አቀፍ

አውሮፓ የተጀመረው ጦርነት ረጅም ግዜ የሚወስድ መሆኑ መነገሩ መላው የአውሮፓ ሀገራትን በፍርሃት ቆፈን አስሯቸዋል፡፡

Published

on

pixel

በአውሮፓ የተጀመረው ጦርነት ረጅም ግዜ የሚወስድ መሆኑ መነገሩ መላው የአውሮፓ ሀገራትን በፍርሃት ቆፈን አስሯቸዋል፡፡
ፍርሃቱ ግን የመነጨው ከጦርነቱ መራዘም ጋር ብቻ በተያያዘ አይደለም ፡፡አውሮፓውያን ያዝ ለቀቅ በሚያደርጉት ማዕቀባቸው ቅድሚያ ተጎጂ የሆኑት ራሳቸው ናቸው፡፡የአውሮፓ ህብረት ከዱሲያ ጋር ምግብ ፣ማዳበሪያና ሌሎች ተያያዥ ግብዓቶችን መግዛት የሚችሉ ሀገራት መገበያየት ይችላሉ የሚል መግለጫ ሠቷል ፡፡ይሁንና የአካባቢው ሁኔታ ይህንን ለማድረግ የሚያመች አልሆነም ፡፡የሩሲያን ምርቶች በመግዛት ለዓለም የሚያቀርቡ ኩባንያዎቹና መንግስታት ሩሲያን እየሸሹ ፊታቸውን ወደ ሌላ አማራጭ እያዞሩ ነው፡፡ ኩባንያዎቹና መንግስታት በሞስኮ ላይ እየተደጋገመ የመጣው ማዕቀብ ስላሰጋቸው አማራጭ ወዳሉት ቀጠና እየሄዱ ነው፡፡ በተለይ የስዊዘርላንድ አሻሻጭ ኩባንያዎችና ራሱ መንግስት ለአስርት ዓመታት የሩሲያን ምርቶች ለመላው ዓለም ለማድረስ በሚደረገው ጥረት ውጤታማ ድልድይ ሆነው ሠንብተዋል፡፡ ይሁንና አሜሪካ ፣ኔቶ የአውሮፓ አባል ሀገራትና አንዳንዶች ዘላቂ ሆኖ የማይፀና ቢሆንም በሩሲያ ላይ የሚጥሉት ማዕቀብ እየተደጋገመ መቷል ፡፡

በዚህም የሩሲያ ምርት ገዢዎች የንግድ አቅጣጫቸውን መሪ እያዞሩ ይገኛሉ ፡፡ስዊዘርላንድ ከነ ድርጅቱ ቀዳሚ ስትሆን ወደ ሩሲያ የምታደርገውን የንግድ መሥመር ወደ ገልፍ ሃገራት በተለይም ወደ ተ.ዓ.ኤ በማዞር ቀዳሚ ሆናለች ፡፡ ነገር ግን ሩሲያ ይህ አካሄድ ይከሰታል በማለት ቀድማ በወሠደችው እርምጃ የሩሲያ ገበያ አፈላላጊዎች ከስዊዘርላንዳውያን ቀድመው ዱባይ ተገኝተዋል፡፡ ከሩሲያ ነዳጅ አምራች ኩባንያዎች መካከል በቀዳሚነት የሚቀመጡ ሦስት ድርጅቶች የዓለም የገበያ አማራጭ እየሆነች ላለችው ዱባይ ቅድሚያ መስጠታቸው በሌሎች አውሮፓውያን ሊወሠድባቸው የሚችለውን የንግድ የበላይነት አስከብረዋል፡፡ የተ.ዐ.ኤ የገበያ አማራጭ ከመሆን ባለፈ በዓለም አቀፍ ገበያው ሠንሠለት ውስጥ አሻሻጭ በመሆንና የንግድ ሥራዎችን በማቀላጠፍ የተዋጣለቸው ኩባንያዎች አሏት፡፡ የስዊዘርላንድ ድርጅቶች ከሞስኮ ጋር ያለው ገበያ ይቀዛቀዛል ብለው በማሠብ የተ.ዐ.ኤ.ን ከሁሉ አስበልጠው ወደ ዱባይ ቢያቀኑም ከሞስኮ የንግድ ዲፕሎማቶች ጋር ተፋጠዋል፡፡ አሁን የተፈጠረው የገበያ ፍለጋ መሯሯጥ የአውሮፓ ህብረት ለሚጥላቸው ማዕቀቦች በኋላ ይፈጥራል በሚል ሲጠበቅ ነበር ፡፡

የሩሲያውያን በዱባይ ቀድሞ መገኘት ለአውሮፓውያን የገበያ አማራጫቸውን እንደሚያጠበው ባለሙያዎች ገልፀዋል፡፡በሮተርዳም ዩኒቨርሲቲ የንግድ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ዎተር ጃኮብስ እንደሚሉት ሩሲያ በየተኛውም አካሄድ ውስጥ ብትሣተፍ የቀሪው አውሮፓ ክፍል ንግድ መቀጠሉ አይቀሬ ነው፡፡ በስካሁኑ የንግድ ሂደት የማዕከላዊ አውሮፓ የንግድ ሥርዓት የደረሠበት ከፍተኛ ጫና የለም፣አስጊው የወደፊቱ ጉዳይ ነው የሚለው የአውሮፓ ሕብረት በቀጣይ በሚደረግ የአውሮፓ የንግድ ውድድር የገልፍ ሀገራት ያለቸው ዘመናዊ የትራንስፖርት አቅርቦትና የገበያ ሠንሠለት ጥንካሬ አሁን በመጣላቸው ዕድል ተጠቅመው ከፍተኛ ጥረት ያካብቱበታል የሚል ስተያየት እየተሠጠ ነው፡፡ ከሩሲያ ወደ አውሮፓ ሸቀጦችን የሚያመላልሱ የትራንስፓርት ኩባንያዎች በስጋት እና በቅድመ ትንበያ ብቻ አንዳንዶቹ አገልግሎት በማቆም ሂደት ላይ ሲሆኑ የአብዛኛዎቹ አካሄድም ወደዛ ያጋደለ እንደሆነ ተነግሯል ፡፡ የበርካታ የዘርፉ ድርጅቶች ፍርሃት ወደ ፊት የሚገጥማቸው የፋይናንስ ዕጥረት ሥጋት ነው፡፡ይህንን ሥጋት ለመቅረፍ ይመስላል አንዳንድ የአውሮፓ መንግስታት ባንኮቻቸው መሠል አገልግሎት ለሚሠጡ ኩባንያዎች የብድር አቅርቦት እንዲያመቻቹ ጫና እያሣደሩ ነው፡፡
መንግስታቱ በዚህ በኩል ጥረት ቢያደርጉም በግሉ ዘርፍ የመርከብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪዎች ከሩሲያ ወደ አውሮፓ ለማድረግ የንግድ እንቅስቃሴ የዋስትና አቅርቦት የሚያመቻቹ የኢንሹራንስ ድርጅቶች አገልግሎታቸውን ማቆም ጀምረዋል፡፡የነዚህ ደግሞ ድርብ ችግር የሚሆነው አዲስ በሚመሠረተው የንግድ ቀጠና ላይ አስተማማኝ እምነት የለንም በሚል በሩሲያ በኩል ያቆሙትን አገልግሎት በገልፍ ሀገራቱ በኩል ማስቀጠል አለመፈለጋቸው ነው፡፡ የሩሲያን ምርቶች ወደ ተቀረው የአውሮፓ ክፍል በማድረስ የስዊዘርላንድ ኩባንያዎችን የሚወዳደር አይገኝም ፡፡የስዊዘርላንድ መንግስት በአውሮፓውያን ግፊት ወደ ማዕቀብ መጣል ውስጥ ሲገባ ይኸው አሁን ያሣሰበው ችግር እንደሚከሠት በተገቢው አልታየም ነበር ሲሉ አንዳንድ የሀገሪቱ ድርጅቶች ቅሬታ አቅርበዋል፡፡አሁን በዓለም ላይ የገበያ እጥረት ማጋጠሙም የአውሮፓ ማዕቀብ መጣል ብቻ ሣይሆን ከፍተኛ ድርሻ ያላት ስዊዘርላንድ በዚህ ክፉ ተግባር ውስጥ መሣተፏ ነው፡፡ ስዊዘርላንድ በማዕቀቡ ላይ ቶሎ ላለመቀላቀል ከፍተኛ ጥረት አድርጋለች ፡፡በዚህም በርካታ ወቀሳዎችን አስተናግዳለች፡፡የስዊዘርላንድ ባንኮችን ግለሠብ ባለሀብቶች ከክሬሞሊን መንግስት ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላቸው፡፡
የዚህን ግንኙነት ላለማበላሸት ነበር የሀገሪቱ መንግስት ዳር ዳር ሲል የነበረው ፡፡በመጨረሻም የአውሮፓ ህብረት በፈረንጆቹአቆጣጠር በ2022 መጨረሻ የአውሮፓ የኢንሹራንስና የባንክ ተቋማት የአገልግሎት ትስስራቸው ይቋረጣል በሚለው ውሳኔ ላይ ስዊዘርላንድም እኔም የዚህ ሃሣብ ተጋሪ ነኝ በማለት የህብረቱን ውሳኔ ተቀላቅላለች ፡፡

የአውሮፓ መንግስታትን የሚያተኩሩ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች እንደሚሉት የሚጣሉት ማዕቀቦች በሙሉ ተግባራዊ የሚደረጉ ከሆነ በግፊት የተቀላቀለችው ስዊዘርላንድን ጨምሮ ፣እንግሊዝ ፣ፈረንሳይና ሌሎች ሀገራት ንብረቶች በሩሲያ ምድር ቀልጠው እንሚቀሩ አስጠንቅቀዋል፡፡ እነግሊዝም ከአውሮፓ ህብረት ጋር የነበረው አብሮነቷ በመፍረሱ በተናጠል ከሩሲያ የምታገኛቸው ጥቅሞች ይቀሩባታል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡ይህም ለንደንን ከሁለት ያጣ በማድረግ ዜጎቿን ችግር ላይ ይጥላታል የሚል ስጋት በባለሙያዎቹ ተጠቁሟል ፡፡
ስዊዘርላንድም ሆነች ሌሎች አውሮፓውያን ከሩሲያ ጋር የነበራቸው ጥብቅ ትሥሥር ባስቀመጡት ግዜ ውስጥ ከሌሎች ጋር በሚደረግ አዲስ ስምምነት ዕውን ሊሆን አይችልም፡፡ይህም ዞሮ ዞሮ ራሣቸውን መጉዳቱ አይቀሬ ነው፡፡በውሳኔዎቹ ሩሲያ ተጎጂ ብትሆንም የንግድ ሸሪክነታችንን እናቆማለን የሚሉት ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከእግሯ እንደማይወጡ የታመነ ነው፡፡የአውሮፓ ህብረት የነዳጅ ምርቱን በዓመቱ መጨረሻ አቆማለሁ ባለው አንደበቱ የምግብ፣የማዳበሪያና መሠል ግብዓቶች ላይ ግን ክልከላ አላደረኩም ሲል ማዕቀቡን የሻረ የሚያስመስል መግለጫ በሣምንቱ መጀመሪያ ላይ ሰቷል፡፡

ሩሲያ ግን የአውሮፓውያኑ መሯሯጥ አላስደሰተኝም በሚል የወሠደችው እርምጃ አሁንም ቀዳሚ አድርጓታል ፡፡በዱባይ የወሠደችው የንግድ ዲፕሎማሲ ሥራ በተጨማሪ ማንም የማይጋራት ተጨማሪ የገበያ ድርሻ አላት፡፡ይህም ከቻይና ጋር የምታደርገው የንግድ ትስስር ሲሆን ቤጂንግ በአውሮፓውያኑ በፒን በመዘጋቷ በሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ ጎምዥቶ ከመቅረት ይልቅ የሚቀይሩት አካሄድ አይኖርም ፡፡ ይህ የሞስኮና ቤጂንግ የቀደመ የንግድ ጉዞ አሁን ተጠናክሮ ቀጥሏል ፡፡ይህንን ያዩት አውሮፓውያን ሩሲያ ለቻይና በርካሽ ዋጋ የነዳጅ አቅርቦት እየሰጠች ነው ሲሉ ከሠዋል፡፡በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እድገት በማፋጠኑ በኩል የስዊዘርላንድ ኩባንያዎችና በለንደን ያሉ የፋይናንስ ተቋማት ድጋፍ ማድረጋቸው ነገሩን አስገራሚ አድርጓታል፡፡
የሩሲያ የንግድ ዲፕሎማቶች ከአውሮፓውያን ቀድመው በዱባይ ላይ ያለውን መስመር መያዛቸው ለሌሎች የሞስኮ ኩባንያዎች መነቃቃትን ፈጥሯል ሲሉ የብሉምበርግ ፀሐፊዎቹ አርቼ ሀንተር እና አልሲስ አልሜዳ አስነብበዋል ፡፡ ከፍተኛ ነዳጅ አምራቹ ጋዝሮፕ ,ሮዝኔፍትና ሌሎች ታላላቅ የሞስኮ ድርጅቶች ከአውሮፓ ውጪ ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የገበያ ሠዎቻቸውን አሠማርተዋል ፡፡የአውሮፓ ህብረት ከብራስልስ በሠጠው ተጨማሪ መግለጫ የዓለም ሀገራት ገበያ ፍለጋ መሯሯጥና መሽቀዳደም አያስፈልጋቸውም ብሏል፡፡በዓለም ላይ ያለው ህዝብ ሀገራት የሚያመርቱት ምርት ተሣትፎ ራሱን ማግለሉ አሥደንግጦታል፡፡ በእነዚህ ሁለት አካላት መካከል የሚደረገው አብዛኛው የንግድ ልውውጥ የግብርና ምርት ውጤት ነው ፡፡ህብረቱ ደግሞ የዘርፉን እንቅስቃሴ በእገዳዬ አላካተትኩም ቢልም የስዊዝ ባንክ ግን ራሱን ከትስስሩ ውጪ አድርጓል በዚህ መሀል የዱባይ የቢዝነስ ሠዎች ያጠመዱት ወጥመድ ግቡን መቷል ሲሉ ዘርፉን የሚተነትኑ አካላት እየተናገሩ ነው፡፡

ዱባይ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሠድ ከጀመረች ግዜ አንስቶ ያላቸውን የገበያ ትስስር እና የፈጠሩትን የንግድ ሠንሠለት ጥንካሬ ለዓለም ሲያስተዋውቁ ቆይተዋል ፡፡ይህ ሥራቸውም አሁን ፍሬ አፍርቷል፡፡ የዱባይ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር ናጂብ አልቀለሚ እንደሚሉት ሀገራችን አሁን ዓለም አቀፍ ምርቶችን በማቅረብ አዲስ አማራጭ ሆናለች ሲሉ ተናግረዋል ፡፡ እኛ ጋር አስተማማኝ መሠረተ ልማት፣ተደራሽ የትራንስፖርት አቅርቦት እና በተሻለ የሠው ሀይል የተደገፈ አገልግሎት አለ ሲሉ አሁንም ማስተዋወቃቸውን ቀጥለዋል ብሉምበርግ ፣አል-ጀዚራ፣እና ሮያተርስ የዘገባው ምንጮች ናቸው፡፡

Continue Reading

አለም አቀፍ

የፍትህ መዛባት በማንም ይፈፀም በማን ሥርዓቱን እስካጣ ድረስ እለታዊ ውጤት ማምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡

Published

on

pixel

የፍትህ መዛባት በማንም ይፈፀም በማን ሥርዓቱን እስካጣ ድረስ እለታዊ ውጤት ማምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡ይሁንና መዛባቱ በሀያላኑና ጀሌዎቻቸው ሲፈፀም ፤ስህተቱም ትክክል ፤በዳይም ተበዳይ ይሆናል፡፡ ምዕራባውያንና አጋሮቻቸው በሚፈፅሙት ከባባድ ወንጀል ሳይጠየቁ ፣ራሳቸው በዳይ ፣ራሳቸው ከሣሽ ፣ራሣቸው ዳኛ ሆነው ሳያገኙ ፤ብዙ ብርሃኖች ታፍነው ቀርተዋል ፡፡ የኢራን የኒውክለር ተመራማሪዎች ያደባባይ ግድያ ፣የፍልስጤም ህፃናት ሞት ፣የየመን ፣የሶሪያ ና ሌሎችም ሀገር ዜጎች በዓለም አደባባይ ከፍተኛ በደል ሲፈፀምባቸው ማንም አልተጠየቀም ፡፡ የሳኡዲ መንግስት በጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ዘግናኝ ሞት ሳይጠየቅ የነአሜሪካ ወዳጅ በመሆኑ ብቻ ሳይጠየቅ ታልፏል ፡፡ሌሎችም በየመሀሉ የተፈፀሙ ወንጀሎች አጥፊ ሳይጠየቅ ፤ተበዳይም ሳይከስ በዝምታ ተሸኝተዋል፡፡የዛሬ ወር ገደማ የተወራሪዎቹ ፍልስጤማውያን ድምፅ የ ነበረችው ሽሪን አቡ አቅሌ በሥራ ላይ እያለች በእስራኤል ወታደሮች በግፍ በጥይት ተመታ ተገደለች ፡፡ ስለሷ ፍትህን የሚሹ በዓለም ዙሪያ ያሉ ቤተሰቦች ፤የሥራ አጋሮች ፤አድናቂዎችና ድምፅ አልባዎች ቢኖሩም /ቢጠይቁም መልስ ግን የሚሠጣቸው አላገኙም ፡፡ የብዙዎችን በደል ይፋ በማውጣት የምትታወቀው ሽሪን ከሞተች አንድ ወር አለፋት፡፡ ይሁንና በግድያ ህግ ፊት እናደርሣለን ያለው የፍልስጤም መንግስት መንገዱ ተዘግቶበት ይሁን በሌላ ምክኒያት እስካሁን ምንም ያደረገው ነገር የለም ፡፡ የወንጀሉ ፈፃሚ እስራኤል ፤በዚህም እንዳትጠየቅ የሚተባበሩት እነ አሜሪካ በነገሩ ምርመራ እየተጨቃጨቁ ግዜ እየፈጁ ይገኛሉ፡፡ የፎረንሲክና ባለስቲክ ባለሙያዎች በጋዜጠኛ ሽሪን አቡ አቅሌ ላይ ተተኩሶ ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ጥይት ስሪቱ ፣አይነቱና በማን ጥቅም ላይ እንደሚውል ይፋ አድርገዋል ፡፡ጥይቱ ከባለ5.56 ሚ.ሜ የአፈሙዝ ስፋት ያለው መሣሪያ የሚወረወርና ባለ 3Dሞዴል ተብሎ የሚጠራ መሆኑን ባለሙያዎች በምርመራቸው አረጋግጠዋል፡፡ የጥይቱ ሞዴልም በአሜሪካ የተሠራና ምርቱም በዛው ሀገር ብቻ የሚመረት ስለመሆኑ ተነግሯል ፡፡ይህ የመሣሪያ ዓይነት ደግሞ አሁን ላይ ለእስራኤል ሀይሎች እጅ እንደሚገኝ የቀድሞው ጆርዳናዊ የጦር ሠው ሜጀር ጀነራል ፋኢዝ አል-ድዋሪ ለአል-ጀዚራ ተናግረዋል፡፡በዚህና በሌሎች ብዙ አሣማኝ ምክኒያቶች ጋዜጠኛ ሽሪን በእስራኤል ሀይሎች መገደሏ ግልፅ ነው ሲሉም ጀነራሉ ጨምረው ተናግረዋል፡፡ ይህ አሣማኝ መረጃ ከመምጣቱ በፊት የእስራኤል ባለሥልጣናት ግድያው የተፈፀመው በራሣቸው በፍልስጤም ታጣቂዎች ነው ሲሉ ሲሟገቱ ቆይተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስቴር ናፍታሊን ቤኔትም ይህንኑ ዕውነት ሲሉ ለመገናኛ ብዙሃን ጭምር መግለጫ ሲሰጡ ነበር፡፡ኋላ ላይም ማስረጃ ነው ብለው ጋዜጠኛዋ ተተኩሶባት ስትሞትና የተኩሱን አቅጣጫ የሚያመለክት ነው የተባለ ተንቀሳቃሽ ምሥል አቅርበው ነበር፡፡ ይሁንና ይህ በራሳቸው በእስራኤላውያን የተቋቋመ የሠብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ቡድን ማስረጃ ተብሎ ያቀረበው ምስል የተቀናበረና በትክክል የጋዜጠኛዋን ገዳይ የሚያረጋግጥ ስለመሆኑ መስክሯል ፡፡Bሰለም የተባለው የዚህ ቡድን መሪ የሆነው ኦማር ሻኪ እንዳለው የጋዜጠኛዋ ገዳይ ጥይት በእርግጠኝነት የተተኮሰው ከእስራሴል ወታደሮች ነው ሲል ለአል-ጀዚራ ተናግሯል፡፡አሁን የተገኘውና ምርመራ የተደረገበት ጥይት በመንግስት እጅ እንዲቀመጥ የተደረገ ሲሆን ቀጣይ በሚኖር ምርመራ ሂደትም እንደሚጠቅም ተናግሯል ፡፡ቢ-ሰላም የተሠኘው የሠብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን በፍልስጤምና እስራኤል ዜጎች ጭምር ሀይል የሚሠራ ነው ፡፡ቡድኑ እ.አ.አ ከ2012 ጀምሮ እስራኤልና የተገደሉ ጋዜጠኞችን ዝርዝር የያዘ ሲሆን በስካሁን ምዝገባው 19 የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ሞት መዝግቧል ፡፡ከዚህ ውስጥ ሽሪንን ጨምሮ 12 ቱ የአል-ጀዚራ ጋዜጠኞች መሆናቸውም ታውቋል፡፡ የሽሪን አቡ አቅሌ የግድያ ምርመራ ከብዙ ልፋት በኋላ ዓለም አቀፉ የወንጀል /ችሎት /ICC/እንዲይዘው ተደርጓል ፡፡በዚህ የምርመራ ሂደት ውስጥ አሜሪካና እስራኤል ካልገባንበት ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ አሁን በ/ICC/ በኩል የሚስተዋለው ግልፅ ያልሆነው አሠራርም እነዚህ ሀገራት በምርመራው ሂደት አሉበት ወይ የሚል ጥያቄን አጭሯል፡፡ አሁን ከዚህ የግድያ ምርመራ በተጨማሪ ፍልስጤማውያን እንዲታይላቸው የሚፈልጉት ጉዳይ አለ፡፡በጋዜጠኛዋ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ድብደባ የፈፀሙ ፖሊሶች እንዲጠየቁላቸው ይፈልጋሉ ፡፡ነገር ግን ጉዳዩ ከአንድ ወር በላይ ቢያስቆጥርም ምንም ዓይነት ፍትህ ማግኘት አልተቻለም ፡፡ በዱድ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና የፖለቲካ ተመራማሪ የሆኑት ጀላል አቡካተር እንደሚሉት ከሽሪን ዕለተሞት ጀምሮ ፍትህ ለማሠጠት የተደረገው ጥረት ውጤት አላመጣም ፡፡ ከአንድ ወር በላይ ለተወዳጇ ጋዜጠኛችን ሽሪን አቡ አቅሌ ግድያ ፍትህ ፍለጋ በየአቅጣጫው ተነቃንቀናል ፡፡ነገር ግን ገና ከጅምሩ እስራኤልም ሆነች የርሷን መከሰስ የማይፈልጉ አካላት ነገሩን ከእስራኤል አውርደው ከፍልስጤማውያን ለማዞር በመጣራቸውና ለዕውነተኛ ፍትህ ትብብር ባለማድረጋቸው ጉዳዩ መጓተቱን ተመራማሪው ይናገራሉ ፡፡ በሽሪን ጉዳይ ማንም አይተኛም ለበርካታ ዓመታት በኢ-ፍትሃዊነት ሥር ኖረናል ፡፡የብዙ ዜጎቻችንን ሞት አልፈናል፡፡ይሁንና በሽሪን ጉዳይ ግን ትግላችን ይቀጥላል ያሉት ተመራማሪው ጀላል ፤”ለአል-ጀዚራ ዘገባ ሽሪን አቡ አቅሌ ነኝ”የሚለው ድምጿ የትግላችን አንድ አጋር ነው፡፡ ጉዳዩን የያዘው የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ቢሆንም መጓተቱና ግዜ መውሠዱ አይቀርም ፤ነገር ግን የቱንም ያህል ግዜ ቢወስድ ድምፃችን ለነበረችው ሽሪን ግን እንታገላለን በማለት ጉዳዩን የሚከታተሉት ፍልስጤማውያን ለአል-ጀዚራ ተናግረዋል፡፡ የስካሁኑ የተደነቃቀፈ ጉዞም ቢሆን በነገሩ ላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ መሆኑ ለመቀጠላቸው ተስፋ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡ የሽሪን ግድያ ለፍልስጤማውያን በቀላሉ የሚተው ጉዳይ አይሆንም፡፡በቅርብ ግዜ ታሪካቸው የሽሪን ዓይነት በሕይወቱም በሞቱም ታግሎ ያታገለ ፤በአንድነት ያሠባሰባቸው የለም፡፡ለ3 ቀናት በቆየው የሀዘን ሥነ-ሥርዓት ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የተውጣጡ የሀዘን ተሣታፊዎች ያሳዩት አንድነትና ጥንካሬ ለአንዳንዶቹ በፍልስጤም ትግል ውስጥ ለመሣተፍ ዕድል የፈጠረላቸው በመሆኑ የራሷን ፍትህ ለማሰጠት ለሚደረገው ትግል ሌላ ጉልበት ሆኗል፡፡ ሽሪን ከሞተችበት ጄኒን መንደር ጀምሮ ናብሉስ በሚገኘው አል ነጃህ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ድረስ የነበረው ሥነ-ሥርዓት በራሱ ለዓለም ያደረሰው መልዕክት ነበረው ፡፡ በእየሩሳሌም ጎዳናዎች በሺዎች የሚቆጠሩና ሠንደቅ ዓላማቸውን የያዙ ፍልስጤማውያን ከወትሮው በተለየ መልኩ መታየታቸው አስደንጋጭ ነበር፡፡ይህ በተለይ ለእስራኤል መንግስት በእጅጉ አስፈሪ ነበር፡፡ይህንን ጥንካሬ ከጅምሩ ለመቅጨትም በጋዜጠኛ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ጉዞ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፣ወከባና እሥራት ሲፈፀም ነበር፡፡ይህ ስብስባችን ያስፈራው እስራኤል መንግስት ኃላፊነት የጎደለው ተግባር እንደሚኖር እንጠብቀው ነበር ሲሉ የናብሉስና ራማላህ ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን የጋዛ ፍልስጤማውያን ደግሞ ይህ የለመድነው ተግባር ነው፤አሁን ግን የመጡብን በሽሪን በመሆኑ ትግሉ ይጨምራል ሲሉ ሀሣባቸውን ለአልጀዚራ ገልፀዋል፡፡
ሽሪን የየሩሳሌም ልጅ ናት ፣ሽሪን የፍልስጤም ልጅ ናት ፣እራሷ ህይወቷን በሙሉ ዕውነታችንን ለዓለም ስትነግርልን የቆየች ፤ህይወቷንም ለኛ ትግል ፍሬያማነት የሰጠች በመሆኗ ፤የነፃነት ፍለጋ ትግላችን እንዲቀጥልና እንዲጠነክር በሞቷ ነግራናለች ያሉት ፍልስጤማውያን ገዳዮቿን ለማጋለጥ ያሉትን ግድግዳዎች በሙሉ አልፈን እንከሣታለን ሲሉ ተናግረዋል ፡፡ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ፈተና አሁን ሣይሆን አይቀርም እየተባለ ነው፡፡የሽሪን ሞት በእስራኤል የፀጥታ ኃይሎች ስለመፈፀሙ በርካታ ማስረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ጋዜጠኛዋ በተገደለችበት ሠሞን ዝምታን መርጠው የነበሩት የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን አሁን መረጃዎችን ተንተርሠው እስራኤልን እየወቀሱ ይገኛሉ ፡፡ CNN አሁን በአል-ጀዚራና በሠብዓዊ መብት ተሟጋቾች በተገኘው ማስረጃ ላይ በመመርኮዝ የራሱን ተጨማሪ ምርመራ ሠርቶ ነበር፡፡ በዚህም ያሠባሠባቸውን መረጃዎች ትንተና ካጠናከረ በኋላ በሠራው ዘገባ ሽሪን በእስራኤላውያን ጥይትና ወታደር መገደሏን ይፋ አድርጓል፡፡ይህ ከምዕራቡ ዓለም የመጣ የመጀመሪያ ዘገባ ሆኗል፡፡ አሁን እየቀረቡ ያሉ ማስረጃዎች እስራኤልን በተለያዩ ጉዳዮች ለመከሰስ በቂ ናቸው ፡፡ሆኖም የICC መንቀርፈፍ ፣የCPJ ዝምታና በሌላ ጉዳይ ፍትህ አስከባሪ ነን የሚሉ ለዘብተኝነት መፈተኛቸውን ያቀረበው ፡፡ ከሽሪን የጀኒን መሞት በኋላ እስራኤል 12 ፍልስጤማውያንን ገድላለች ተብሏል፡፡የፍልስጤማውያን ትኩረት ግን አሁንም ሽሪን ላይ ነው፡፡ ትኩረትና ጫናው እየበረታ ሲመጣ የተ.መ.ድ ፤የዓለም ቀይ መስቀል ማህበር ፣እና የአውሮፓ ሕብረት ሀሣባቸውን ገልፀዋል፡፡ይሁንና የሁሉም ትኩረት የቅዱስ ዮሴፍ ሆስፒታል ግቢ የተፈፀመው ድብደባ ላይ አተኩሯል ፡፡የእስራኤል ወታደሮች አስክሬን በያዙ ሠዎች ላይ ያደረሱት ድብደባ ፍፁም ተቀባይነት የለውም ብሏል የተ.መ.ድ የአንድ ወር ሙሉ ዝምታን ሲሠብር ፡፡የአንቶንዮ ጉተሬዝ ቃል አቀባይ እንዳለው የእስራኤል ፖሊሶች የፈፀሙት ተግባር ፤ያደረሱት ጉዳት ነውጠኝነት የተመራበት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡የአውሮፓ ህብረትም ድርጊቱን በተመሣሣይ አባባል ሲገልፀው ፤ስለሽሪን የፍርድ ሂደት ግን ያሉት የለም ፡፡ የእየሩስ አሌም ጉዳይ የቀይ መስቀል ማህበር እንዳለው በፖሊሶቹ ድብደባ 33 ሠዎች ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደዋል ፡፡ከአንድ ወር በላይ ባስቆጠረው በዚህ አስከፊ ድብደባ ግን አንድም የእስራኤል ፖሊስ አለመጠየቁ ተናግሯል፡፡ እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች የብዙዎችን ዝምታ ሠብረዋል ቢባልም ፡፡በሽሪን አቡ አቅሌ ግድያ ላይ ምንም ሣይሉ ማለፋቸው አስገርሟል ፡፡ፍልስጤማውያን ግን የአካል ጉዳትና ሞት ያስተናገዱ ዜጎቻችንን ፍትህ አጥብቀን የምንፈልገው ቢሆንም ፤የሽሪን ጉዳይ ግን የምንሞትላት የፍልስጤም ጉዳይ ነው ሲሉ የፍትህ ጥያቄያቸው አንደማይቆም አጥብቀው ተናግረዋል፡፡ነገሩ አንድ ወር ማስቆጠሩን ተከትሎ ከፍተኛ ንቅናቄ እያደረጉ ይገኛሉ ፡፡ አል-ጀዚራ ፣ሲ.ኤን .ኤን ፣ሮይተርስ እና አናዳሉ የዘገባው ምንጮ

Continue Reading

በብዛት የተነበቡ