Connect with us

ሀገር ዉስጥ

በሀገራችን የተቋቋሙ የሲቪክ ማህበራት የሚጠበቅባቸውን ያክል እየሰሩ እንዳልሆነ ተነግሯል ።

Published

on

pixle

በሀገራችን የተቋቋሙ የሲቪክ ማህበራት የሚጠበቅባቸውን ያክል እየሰሩ እንዳልሆነ ተነግሯል ።

ዜጎች የተለያዩ መብቶች እና ነፃነቶች ያሏቸው ሲሆን ከእነዚህ መብቶች መካከል ተደራጅቶ መብትን እና ጥቅማቸውን ማስጠበቅ አንዱ ነው ።
ዜጎች ፖለቲካዊ ፣ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ባህላዊ መብታቸውን በመደራጀት መከወን ይችላሉ ።
በሀገራችን 3800 የሚሆኑ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዳሉም ተገልጿል ።
የኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ለአዋሽ ራዲዮ እንደገለፁት ፦ ችግር ፈች የማህበረሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ፣ የህዝብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚችል ሲቪክ ማህበረሰብ መሬት ላይ ከተንቀሳቀሰ እና የመንግስትም ትብብር ከታከለበት መንግስት ለሚያስተዳድረው ሴክተር መስሪያቤቶች ወጤት ማምጣት እንደሚያስችል ተናግረዋል ።ለሀገራችን ዘላቂ መፍትሔ የሚሆነው ቀጣይነት ያለው ሰላምን ማረጋገጥ ሲቻል ነው ያሉት አቶ ፋሲካዉ፦ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መስራት እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል ።
በዩክሬን እና ራሺያ ጦርነት ጋር ተያይዞ በምእራባውያኑ በኩል ያሉ ለጋሽ አካላት ሙሉ በሙሉ ድጋፋቸውን ወደ ዩክሬን ግጭት በማዞራቸው የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች አሁን ባለው ሁኔታ የገንዘብ እጥረት በስፋት እንደገጠማቸው ተናግረዋል ።
አዋሽ ራዲዮም በዚህ ዙሪያ የተለያዩ አካላትን አነጋግሯል ፦በጉዳዩ ዙሪያ ሃሳብን የሰጠን ጋዜጠኛ ዉብሸት ታየ የሲቪክ ማህበራቱ ዉጤታማ ስራ እየስራን ነው ይበሉ እንጂ ማህበራቱ የሚጠበቅባቸውን ያክል እየሰሩ እንዳልሆነ ነግረውናል ።የሲቪክ ማህበራት ለግል ጥቅማቸው ሳይሆን ለተቋቋሙለት አላማ መስራት እንደሚገባቸውም ተመላክቷል።

በመቅደላዊት ይግዛው

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

ሀገር ዉስጥ

ኢትዮ ቴሌኮም የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል አዲስ አሠራር ይፋ አደረገ።

Published

on

ኢትዮ ቴሌኮም የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል አዲስ አሠራር ይፋ አደረገ።

የአገልግሎት መዘግየትን ለማሻሻልና ተደራሽነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎችን ተግባራዊ ማድረጉን የገለፀው ኢትዮ ቴሌኮም በአዲሱ የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥም ቴሌብርን ተጠቅሞ ፓስፖርትን ማውጣት፣ ማደስ፣ መቀየርና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎት ማግኘት እንደሚቻል ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።

የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩህተስፋ ሙሉጌታ በበኩላቸው ዜጎች የሚገባቸውን አግልግሎት ለማግኘት ቀልጣፋ አሠራር እና ቴክኖሎጂ ወሳኝ ነው ብለዋል። ለዚህም ኢትዮ ቴሌኮም ያስተዋወቀው አዲስ የአገልግሎት አሰጣጥ አጋዥ በመሆኑ ወደ ደንበኞቻችን የበለጠ ለመቅረብ የሚያስችለን ነው ብለዋል።ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ በሁለቱ ተቋማት መካከል በነበረው የስራ ስምምነት ወቅት፤ ሰሞኑን ብሔራዊ ባንክ ካወጣው የዲጂታል ግብይት ክልከላ ጋር በተያያዘ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህም ብሔራዊ ባንክ ክልከላ የጣለባቸው የግብይት ዓይነቶች ከኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል አሠራሮች ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለዋል።

በሌላ በኩል ሰሞኑን የተፈጠረው የቴሌኮም መቆራረጥና የጥራት መጓደል ከኃይል መዘግየት ጋር የተያያዘ በመሆኑ እና በአማራጭ የኃይል አቅርቦት እየተሠራ በመሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል።በዘመድኩን ብሩ

Continue Reading

ሀገር ዉስጥ

በመዲናዉ ከጊዜ በመሰረተ ልማት አዉታሮች ላይ የሚፈጸሙ የስርቆት ወንጀሎች አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል ተባለ

Published

on

pixle

በመዲናዉ ከጊዜ በመሰረተ ልማት አዉታሮች ላይ የሚፈጸሙ የስርቆት ወንጀሎች አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል ተባለ። በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ በቴሌኮም፣በመብራት ሃይል እና በቀላል ባቡር መሰረተ ልማት ላይ የሚፈጸሙ የስርቆት ወንጀሎች ደግሞ ቀዳሚዉን ስፍራ ይይዛሉ ተብሉል። በጉዳይዉ ዙርያ ከአዋሽ ራድዮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንደገለጡት ለሀገር እና ለህዝብ ግድ በሌላቸዉ አካላት የስርቆት ወንጀሉ ተባብሷላ ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ በባቡር የመሰርተ ልማት አዉታሮች ላይ የስርቆት ወንጀል የሚፈጽሙ አካላት የባቡር ተራንስፖርትን ተጠቃሚ መሆናቸዉን ዳይሬክተሩ ተናግርዋል። የስርቆት ወንጀሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ በብዛት እንደሚፈጸም ያነሱት ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ይህም ተገላጋይዉን ለከፍተኛ ችግር ዳርጓል ብለዋል። ወንጀሉ የሚፈጸመዉ በምሽት ጨለማን ተገን ተደርጎ ሰለሆነ ለመከታተል አዳጋች አድርጎታል ብለዋል። ይህን ህገወጥ ድርጊት በጸጥታ ሀይል ብቻ መከላከል የሚቻል ሰላልሆነ ሁሉ የህብረተሰብ ክፍል የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ጥሪ አስተላልፈዋል። በያሬድ እንዳሻዉ

 

Continue Reading

ሀገር ዉስጥ

ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ባሏቸው ግለሰቦችና አስመራቂ ተቋማት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እየተሰራ ነው ።

Published

on

featured
Photo: Social Media

በኢትዮጵያ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ባሏቸው ግለሰቦችና አስመራቂ የትምህርት ተቋማት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እየተሰራ መሆኑን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ገለጸ። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን የትምህርት ጥራትን ከመቆጣጠር ባሻገር የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነትን የማረጋገጥ ሥራን ያከናውናል። በዚህም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸውን ዝርዝር መረጃና የትምህርት ማስረጃ ከምዝገባ እስከ ምረቃ ድረስ ለባለሥልጣኑ የመላክ ግዴታ አለባቸው።

ይህንንም ተከትሎ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ከ1995 ጀምሮ እስከ 2014 ዓ.ም መረጃቸውን ለተቋሙ ካስገቡ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ክትትል አድርጓል። በእነዚህ ተቋማት እስካሁን ከተመረቁ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ተማሪዎች መካከል ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የያዙ መሆኑን ነው የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ እንደገለፁት ።

ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃውን የያዙት ግለሰቦች የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው፤ በ10+1 እና በ10+2 የዲግሪ የምስክር ወረቀት ከማግኘት እስከ እውቅና በሌለው የትምህርት መስክ እስከተመረቁ ይገኙበታል ነው ያሉት። እርምጃ መውሰድ ቢጀመር አንዳንድ ክልሎች ቢሮዎቻቸው ሊዘጉ ይችላሉ ያሉት ዶክተር አንዱዓለም፤ በአስመራቂ ተቋማትና የሐሰተኛ ትምህርት ማስረጃው ባለቤቶች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዝርዝር ማጣራት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በዚህም የወንጀል ጉዳዮችን በሚመለከት ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ባለሥልጣኑ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሰጡ ተቋማትን በሕገ-ወጥ መንገድ ዲግሪ ያገኙ ተመራቂዎችን ለማጋለጥ ወደ ኋላ እንደማይልም ነው የተናገሩት። እንደ አገር መወሰድ በሚገባቸው እርምጃዎች ላይ መንግሥት አቅጣጫ እንዲያስቀምጥ የተለያዩ የውሳኔ ሐሳቦችን በማካተት እንደሚቀርብ ተናግረዋል።

ለ20 ዓመታት የተንከባለሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማስተካከል እየሞከርን ነው” ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በቀጣይም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የተመራቂዎቻቸውን ሙሉ መረጃ እንዲልኩ የማድረግ ሥራ ይከናወናል ብለዋል። በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በርካታ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ129 ከተሞች ከ2 ሺህ 500 በላይ ቅርንጫፎችን ከፍተው ከ3 ሺህ 315 በላይ የትምህርት መርሃ-ግብሮችን በማስተማር ላይ ናቸው።

Continue Reading

በብዛት የተነበቡ