ዓለማችን ከፌብሩዋሪ 24/2022_ማርች 24/2022 በነበሩት ጊዜያት30 ቀናት ከባዱን ጊዜ አልፋለች። ሩሲያ በዩክሬን የጀመረችውን ወታደራዊ ዘመቻ ተከትሎ ከባድ ውሳኔዎች ተላልፈዋል። አብዛኞቹ ውሳኔዎች ሩሲያን በመቃወም፤ ዩክሬን በመደገፍ የተሰጡ ናቸው። በሩሲያ በኩል የተላለፉት ደግሞ በተቀራኒው። ይሁንና እነዚህ የሁለቱ ወገን የፍቃድና ክልከላ እወጃዎች በዓለም ላይ ላሉ፤ ጦርነቱ በምንም መልኩ የማይመለከታቸው ዜጎች አቅም እየፈተነ ነው። በጦርነቱ መጀመሪያ ሰሞን በጉዞ እገዳዎች የጀመረው የማእቀብ እርምጃ እምብዛም ስጋት ያጫረ አልነበረም። ሁኔታው ቀስ በቀስ ወደ ንግድ ነዳጅ ጉዳዮች ሊያመራ ዓለም የገበያ እንቅስቃሴ በፍጥነት አናግቷል።
በዚህ የአንድ ወር ወታደራዊ ዘመቻ በመጀመሪያ ሁሉም ነገር ይመለከተኛል የምትለው አሜሪካ 100 በሚሆኑ የሩሲያ ባለስልጣናትና የቀድሞዋ ሶቬት ቅራት ያለቻችቸው ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ ጣለጭቀጥሎም እንግሊዝንና የአውሮፓ ህብረትን ያስከተለችው ዋሺግተን የጉዞ ታጋቾች ቁጥር ወደ 386 ሰዎች ከፍ አደረጉ። በዚህ እቀባ የቀድሞዎቹ ፕሬዝዳንትና መከላከያ ሚኒስቴር ዪሜትሪ ሜድቬዬቭና ሰርጌ ሸጉ ተጠቃለሉ። ከግለሰብ ወደ ግዢ ልውውጥ ያደረገው ማዕቀብ ብሪታኒያና የአ.ሕ. በጋራ በመሆን ለሩሲያ የሚያቀርቧቸውን ውድ ዕቃዎች አንሸጥም ሲሉ አወጁ። እኛ ያመረትናቸው ተሽከርካሪዎች ሳይቀሩ ሩሲያ ምድር አይሄዱም ሲሉ ወሰኑ።
ካናዳና ጃፓን የማዕቀብ መጣሉን ተግባር ተቀላቀሉ። እንዲህ ከሆነ ያዋጣል ያሉት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከእንግዲህ ከሩሲያ የማስገባው ነዳጅ አልፈልግም ሲሉ ከባድ ውሳኔ አሳልፈዋል። ይህ የሆነው ጦርነቱ ተፋፍሞ በወሩ ወገብ ላይ በነበረበት ጊዜ ነው። ከዚህም በኋላ አሜሪካ ሩሲያን በማዕቀብ የሚጫንና ጦርነቱ የሚያወግዝ አጋር ፍለጋ በወሩ ውስጥ በርካታ ሀገራት አካላለች አላደርስ ያላቸውንም ቦታ ስልክ በመምታት “እህ ምን ትላላችሁ “ስትል በሚስጥርም በግልፅም ጠይቃለች። ከሩሲያ ዩክሬወን ጦርነት በኋላ እንደ አሜሪካ እጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒዮ ብሊንከን ስራ የበዛበት ባለስልጣን የለም።አሜሪካ አውጋዥና አጋዥ ፍለጋ በአፍሪካ ፣በኤዢያና መካከለኛው ምስራቅ ያደረገችውን ጉዞ የመሩት ብሊንከን ናቸው። ይሁናና ጉዞዋቸው ውቴታማ አልነበረም። አንዳንዶቹ “አንደግፍም”ከሚለው አሉታዊ ምላሽ ያለፈ ማብራሪያ መስጠታቸው የአሜሪካ የዲፕሎማሲ ስራ የቁልቁለት መንገድ ጀምራለች እስከማለት አድርሷቸው ዋል።
የፓክስታኑ ፕሬዚዳንት ኢምራን ካሀን የሰጡት ምላሽ በአንድ ወር ውስጥ በጦርነቱ ጡዘለት ልክ ዓልምን ጉድ ያስባለ ነበር።አሜሪካ በተዓ.ኤስ በሳውዲ አረቢያና ህንድ ጠብቀው የነበረ በጎ ምላሽን ሳታገኝ ቀርታለች። በኪሳራ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱትን ብሊንከንናሳርፈው ወደ ኳታር ያቀኑት ፕሬዚዳንቱም ቢሆኑ ከዶሀ መንግስት የተመቸውን ድጋፍ ይዘው አልመጡም። ጦርነቱን ሰእብ አድርጎ ሩሲያን ከዓለም የመነጠሉ ተግባር ብዙ ተደክሞበታል። ሆኖም ውጤቱ አመርቂ አልሆነም ልለዋሺግተን። ዝምታን የመረጡት ሀገራት ከሩሲያ ላለ መቀያየም ነው ቢባልም ነገሩ ግን የዋሽግተን የክሽፈት ጉዞ አድርገው የቆጠሩም ነበሩ። ድሀና ባለ እዳ ሀገራት ባለባቸው ድክመት እየተስፈራሩ በነገሩ ላይ ኧጃቸውን እንዲነከሩ ተጠይቀዋል ፣ተገደዋል። ሆኖም በዝምታ ሽሽታቸው ቀጥለዋል።
በተለይ አፍሪካዊያን የኬቭ ነዋሪዎቻቸው ትኩረት ይሰጣቸው ለሚልለው ጥያቄያቸው መልስ ሳይሰጥ ነገሩን እንዲያወግዙ ሲወተወቱ ሰንብተዋል። በአንድ ወርጦርነት አስገራሚ ተብሎ ከተነሳው ውስጥ ይኸው የአፍሪካዊያን ስደተኞች ጉዳይ ነበር። በጦርነት ውስጥያሉት ዩክሬናዊያን በአፍሪካዊያን ላይ ያደረሱት ግፍ ከአሁግሪቱ የነጠላቸው ይመስላል።በዚህ ረገድ ስኬታማ ተደርጋ የምትወሰደው ዲ.ሪ.ኮንጎ ናት። ብራዚል 223 የኬብ ነዋሪዎች ወደ ፈረንሳይ አሸሽታለች። በማዕቀብ መጣሉ አሜሪካንን የደገፏት የአውሮፓ ሀገራትን ያስደነገተ ውሳኔ ከአውሮፓ ተሰማ። አውሮፓዊያን ከዚህ በኋላ ከሩሲያ አንድ በርሚል አያገኑም ስትል ሩሲያ በግሏ ማዕቀብ ጣለች። ይሄኔ በዓለማችን ከነዳጅ አምራች ሀገራት ቀዳሚ የሆነችው አሜሪካ ሩሲያ በመቃወም የደገፏትን አጋሮች አላየሁም አልሰማሁም በሚመስል ዝም ብሏቸዋል።
የአሜሪካንን ዝምታ ያስተዋሉ ት አውሮፓዊያን ሩሲያ የከለከለቻቸውን የነዳጅ ክፍተር ለመድፈን መካከለኛው ምስራቅ ደጋግመውና ተፈራርቀው ጎበኙት። አፍሪካንም የነዳጅ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ደጋግመው ተማፅነዋታል። የፈረሳዩ ኢማኑኤል ማክሮን ፤የእንግሊዙ ቦሪስ ጆንሰን፤ የጀርመኑ ቻንስለር አለፍ ስሆልዝ አውሮፓን ወክለው ነዳጅ ፍለጋ ቢሮዋቸው ትተው የተንከራተቱ መሪዎች ናቸው። በዚህ ፍለጋቸው ከድርጀት ኦፔከን ፣ከመግስታን አልጄሪያን፣ሞሮኮን፣ ናይጄሪያን፣ከአፍሪካ ይናገሩ ሲሆን ከመካከለኛው ምስራቅ ነዳጅ አምራቾች ደግሞ ኩዌትን፣ ሳውዲ አረቢያ ፣ እና ሌሎችንም አግኝተው የነዳጅ ሽጡልን ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። ሆኖም አረቦች ከድርጅታቸው ኦፔክ መመሪያ አንወጣም በማለት የተናጠል መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል። አፍሪካዊያን ደግሞ የነዳጅ መሰረተ ልማታችን ደካማ ነው፤እሱን የምታለሙ ከሆነ ነዳጅስ ነበረን ሲሉ በቅድመ ሁኔታ ተለያይተዋል።
አውሮፓዊያን ከሩሲያ የሚገኙት የነዳጅ አቅርቦታቸው ተቋርጦባቸዋል። ከዚህ ውጪ ራሳቸው ባስቀመጡት እገዳና ሩሲያ በሰጠችው ምላሽ ውስጥ ሀገራት ብቻ ከ150 ቢሊየን ዶላር በላይ በአንድ ወር ውስጥ አተውታል። ይህንን በፍጥነት የተገነዘቡት የህብረቱ አባል ሀገራት አካሄዳቸውን ቁጥብ አድርገዋል። ነገሩ ከረገበ በሚል ለማደራደር ሙከራ ያደረጉም ነበሩ። በወሩ ማብቂያ በህብረቱ የአባልነት ቦታ አገኛለሁ በሚል ምኞት ከኔቶ ጎን መሆኗን ያወጀችው ሞልዶቫ ስህተት እንደሰራች እየተነገረ ነው። በአንድ ወር የጦርነት ሂደት የአሜሪካና ዩክሬን የህንድን ድጋፍ ያሳጣቸው ተብሎ ከተቀመጠው አንዱ የህንድ ተማሪዎች ጉዳይ ነበር። ተማሪዎቹ የአፍርካዊያንን ያህል ባይሆንም መውጫ አጥተው መቸገራቸው በበርካታ መገናኛ ብዙሃን ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ህንዳዊያኑን መንገድ ለመስጠት በሚል ሩሲያ የወሰደችው መፍትሄ በህንድ በኩል ምስጋና ተችሮታል ።በዚህም ህንድ ለነአሜሪካ ጥያቄ ዝምታን በማድረግ ለሩሲያ ያላት ውግንና በሰምና ወርቅ መልኩ ገልፃች። ወርቁ ገብቶናል ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን “ህንድ ከአሁኑ ወዳጇ አሜሪካ ይልቅ የቀዝቃዛው ጦርነት አጋሯ እንደመረጠች አውቀናል ሲሉ ተደምጠዋል።
ጦርነቱ ከሶስት ሚሊየን በላይ ዜጎች ከቤታቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል። በጎረቤት ሀገራት በርከት ያሉ ዩክሬናዊያን የሞቀ አቀባበል ተደርጎላቸው የሚኖሩ ሲሆን ከኬብ ሳይወጡ በህንፃዎች ምድር ቤት የተጠለሉም ምድር ቤት ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። በ30 ቀናት የስደተኞች ጉዞ በርካታ በረራ የተደረገባት ሀገር ስዊዘርላንድ መሆኗም ታውቋል።የ30 ቀናቱ የዩክሬንና ሩሲያን ጦርነት ለማርገብ በሚል ሁለት ሀገራት ቀዳሚ እርምጃ በተግባር አሳይተዋል። ቤላሩሲና ቱርክ።
ቤላሩስ በዝቅተኛ ዲፕሎማቶች መካከል የተደረጉ ውይይቶች ያስተናገደ ሲሆን ጦርነቱን ለማርገብ ሆነ ለማስቆም ግን አልሆነላትም። ቀጥሎም ቱርክ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ደረጃ ከፍተኛ የውይይት ድግስ አዘጋጅታ ብትጠራም የሚኒስትሮቹ መገናኘት ያመጣው ነገር አልነበረም ።የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ከፕሬዚዳንት ቭላድር ፑቲን ጋር ፊት ለፊት መገናኘት አልፈልግም ያሉትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴቹ ውይይት ፍሬ አልባ መሆናቸው ተከትሎ ነበር።ዘለንስኪ የዘር ሀረጋቸው የሚመዘዝባት እስራኤልን በጦር መሳሪያ አልደገፍሽንም በሚል ቢወቅሱም የድርድርሩ ሁነኛ ቦታ ቴላቪቭ መሆኗን ግን ተናግረዋል። ጦርነቱ ካሳየን ገራሚ ነገር አንዱ አሜሪካና አውሮፓውያን ተረባርበው ስፖርትን ከፖለቲካው ጋር የቀላቀሉበት መንገድ ነው። ሩሲያን ከአለም ዋንጫ ፣ከአውሮፓ ሊጎችና ከማንኛውም የስፖርት ንግግር አግደዋታል። በዚህ ሳያበቃ የሩሲያ ባለ ሀብቶች ሲያስተዳድሩዋቸው የነበሩ ግለቦችም አደጋ ውስጥ እንዲወደቁ ተደርጓል።
አውሮፓዊያኑ እነዚህንና መሰል ጫናዎች በሩሲያ ላይ ቢያሳድሩም ዩክሬንን ኝ በምንም መልኩ የሚጠቅም አይደለም። ዩክሬን በእስካሁኑ ቆይታ ከ245 ቢሊየን በላይ ወይም ከ 75 በመቶ በላይ የሚሆኑ የሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ቆሟል። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጡ የምጣኔ ሀብት ስራዎች በግማሽ ያህል ጠፍተዋል። ሩሲያ በብዙ መንገድ ፈጥነው መጣል ያልቻሉት አካላት ፕሬዚዳንት ቮሎንድሚር ዘላንስኪ ኬቭን ለቀው እንዲወጡ ተጠይቀው ነበር። በሩሲያ ላይ ማዕቀብ የታልለችው ጃፓን ሳትቀር ፕሬዚዳንቱ ከሀገር እንዲወጡ ጠይቃለች። የሩሲያ ወዳጅ ናት የምትባለው ቻይና ጨምሮ የ18 ሀገራት መሪዎች ዘለንስኪ ኬቭን ላቀው በመውጣት የዩክሬንን ህዝብ ይታደጉ የሚል ጥያቄ አቅርበዋል።
ከሀገሬ የትም አልሄድም ብለው የፀኑት ዘላንስኪ የመላው ዓለም ድጋፍ ተማፅነዋል ።በመላው ዓለም ያሉ ሰዎች ሩሲያን የሚቃወም ሰልፍ እንዲያደርጉ ፕሬዚዳንቱ ጠይቀዋል። በአንድ አንድ ሀገራት ከፕሬዝዳንቱ ጥሪ በተቃራኒ “በሀገራችን ያሉ ሩሲያዊያን የጦርነቱ አካል አይደሉም”የሚሉ ሰልፎች ተካሂደዋል። የሩሲያ ባለስልጣናት ባለሀብቶች በውጭ ሀገራት ያስቀመጧቸው ሀብቶች አንዱ የወሩ መነጋገሪያ ነብር። የስዊዝ ባንክና አንድ አንድ ምዕራባዊያን ሀገራት ባንኮች 630 ቢሊዮን ዶላር ወይም 470 ቢሊየን ፓውንድ የሚበልጥ የሩሲያዊያንን ሀብት እንዳይቀንሳቀስ አግደዋል። በጦርነቱ የአንድ ወር ሂደት 5 ጋዜጠኞች ተጋድለዋል። ባውሊና ፣ሰርጌ ቶሚሊንኮ አሌክሲ ኮቫሌቭ ሜዱዛና አናስታሪያ ካሪሞቫ በጦርነቱ መሀል የተገደሉ የዩክሬንና ሩሲያ ዘጋቢዎች ናቸው።ሩሲያ በነዚህ ሁሉ ጫናዎች ውስት ብትሆንም የተበረከከች አትመስልም። ጦርነቱ እየገፋችበት ነው። አፀፋዊ የማዕቀብ ምላሾችንም እያጠናከረች መታለች ከበርካታ ሀገራት ጋር ባልት የንግድ ልውውጥ ዶላርን ከገበያ ውጪ አድርጋ በራሷ የመገበያያ ገንዘብ “ሩብል”ቀይራለች። በዩክሪን የተሰማሩ ወታደሮች በጀግንነት ግዳጃቸውን እንዲወጡ በሚል ልዩ መብቶች ሰጥታለች ። ከተባሉት ነገሮች ሁሉ ግን አሜሪካንን ባለስልጣናትን ያስበረገገው ሩሲያ አንዳች የሚያሰጋ ነገር አለ ቢዬ ከጠረጠርኩ የኒውክለር ጦር መሳሪያዬ ተግባር ላይ ይውላል ስትል ከባዱን ካርዷን በተጠንቀቅ አድርጋለች ። ጦርነቱ ግን ንብረት እያወደመ ፤አካል እያጎደለና የሰውን ህይወት እየቀጠፈ ቀጥሏል።Bloomberg,Anadolu,BBC, አልጀዚራ,Sky News The Gardian የዘገባው ምንጮች ናቸው።
በዘመድኩን ብሩ