በኢትዮጵያ ባለፈዉ አንድ አመት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከዛቀደም ብሎ እስካሁን ድረስ መቋጫ ያልተገኘለት በኦሮሚያ ክልል የሸኔ ጥቃት እስካሁን ለዜጎች ፈተና እንደሆነ ቀጥሏል ፡፡ በህዉኋትም ሆነ በሸኔ ቡድን በሚደርሱ ጥቃቶች በርካታ ነዋሪዎች ዛሬም ድረስ የችግሩ ገፈት ቀማሽ እንደሆኑ ይገኛሉ ፡፡
የሰሜኑ ክፍል ጦርነት የሸፈነዉ የሸኔ ጥቃት ሰለባ የሆኑ 48 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች አሁን ላይ በሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኝ መጠለያ ጣቢያ ያለበቂ እርዳታ እንደሚገኙ በተደጋጋሚ ይነገራል ፡፡
ባለፉት ሶስት ወራት የሰሜኑ ክፍል ጦርነት ለጊዜዉ ማብቃቱ ቢነገርም የህወኃት የሽብር ቡድን ግን አሁንም በአማራ የተወሰኑ ቦታዎች እና በአፋር ክልል ደግሞ በተደጋጋሚ ጥቃት እየሰነዘረ እንደሆነ ከአፋር ክልላዊ መንግስት የወጡ መግለጫዎች ያመላክታሉ ፡፡ አለፍ ሲል ደግሞ እስከሁን በበርካቶች ዘንድ ሸኔ ማነዉ የሚለዉ ጥያቄ እንቆቅልሽ ከመሆኑም ባለፈ የሚያደርሳቸዉ ጥቃቶች መቀጠላቸዉ ችግሩን የከፋ ያደርገዋል ፡፡ በመሆኑም እየደረሰ ላለዉ ችግር ምን መደረግ አለበት ስንል የሚመለከታቸዉን ባለድርሻ አካላት አነጋግረናል ፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍት ፓርቲ (ኢዜማ) በአሳለፍነዉ አርብ በሰጠዉ መግለጫ እንደ ገለፀዉ ባለፉት ሶስት ወራት ተቀሳቅሸ አጥንቼ ደርሸበታለሁ እንዳለዉ የህዉኋት ቡድን አሁንም በሀሉለቱም ክልሎች ላይ ጥቃት እያድሰ መሆኑን አስታዉቋል ፡፡ ፓርቲዉ አያይዞም በሌላኛዉ የኢትዮጵያ ክልል የሚንቀሳቀሰዉ የሸኔ ቡድንም በበርካታ የኦሮሚያ ቦታዎች ላይ አሁንም ጥቃት እያደረሰ እና እራሱን እያስፋፋነዉ በመሆኑም መንግስት ሊነቃ ይገባል ሲሉ መግለጨዉን የሰጡት የፓርቲዉ ዋና ፀሀፊ አቶ አበበ አካሉ ተናረዋል ፡፡
ዜጎች በሀገር ላይ በሰላም የመኖር መብታቸዉን እንዲያስጠብቅ ሀላፊነት የሰጡት ለመንግስት በመሆኑ እና መንግስት ይህን የማድረግ ሀላፊነት ስላለበት በየትኛዉም ቦታ ለሚደርሱ ችግሮች አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ያሉት ደግሞ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ገልፀዋል ፡፡
በዜጎች ላይ እየደረሰ ላለዉ ችግር ምክንያቱ ባለፉት 30 አመታት የተሰሩ የተሳሳቱ ስራዎች በመሆናቸዉ መንግስት በየጊዜዉ መዉሰድ ካለበት እርምጃ ጎን ለጎን ዘላቂ መፍትሄ የሚሆነዉ ሁሉን ያሳተፈ ሀገራዊ መግባባት ማድረግ ሲቻል ነዉ በማለት የህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አቶ ግርማ በቀለ ሀሳባቸዉን ሰጠዋል ፡፡
በህገ መንግስቱ እንደተቀመጠዉ አንድ ዜጋ በየትኛዉም አካባቢ የመኖር እና የመስራት መብት እንዳለዉ ቢደነግግም ይህ ተግባራዊ እየተደረገ ባለመሆኑ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ፡፡ ይህን ማድረግ የሚችልበት የአቅም ዉስንነት ካለበት ደግሞ አግዙኝ ሊል ይገባል በማለት አቶ ሙላቱ ገመቹ ጨምረዉ ተናግረዋል ፡፡
ሀገር እንድት ረጋጋ ካስፈለገ በየትኛዉም በኩል የሚደረጉ ዉጊያዎችን በሀሉለቱም በኩል የተኩስ አቁም በማድረግ ችግሩን ማረጋጋት ቅድሚያ ሊሰጠዉ የሚገባ ጉዳይ ሊሆን ይገባል በማለት አቶ ግርማ በቀለ ይጨምራሉ፡፡
በአማራ ክልልም ሆነ በኦሮሚያ ክልል ባላሉ ችግሮች ላይ ተወያይተን አብረን መፍትሄ እንፈልግ በማለት ለሁለቱም ክልሎች እርዕሰ መስተዳድር ደብዳቤ ብናስገባም ምላሽማግኘት አልቻልንም ፡፡ ይሁን እንጅ በሁለቱም ክልሎች አሁንም ከፍተኛ የደህንነት ችግር አለ በመሆኑም መንግስት ችግር ከደረሰ በኋላ ሳይሆን ችግር ከመድረሱ በፊት እርምጃ ሊወስድ ይገባል ተብሎል ፡፡
በመንግስት መዋቅር ዉስጥ የሚገኙ የስራ ሀላፊ ዎች ከአጥፊ ቡድኖች ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉ ቢነገርም እርምጃ የሚወሰደዉ ችግሩ ከተከሰተ በኋላ በመሆኑ መንግስት ከዚህ መሰል አሰራር እራሱን ሊያፀዳ ይገባል በማለት የመፍትሄ ሀሳባቸዉን የነሱት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ሊቀመንበር አቶ የሽዋሽ አሰፋ ናቸዉ ፡፡
በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰዉ የሸኔ ቡድን በዚህ ደረጃ ሊገን የቻለዉ በሚንቀሳቀስባቸዉ አካባቢዎች ያሉ የወረዳም ሆነ የቀበሌ አመራሮች መዋቅር የፀዳ በለመሆኑ ችግሩን ግዘፍ የነሳ አድርጎታል ሲሉ ይህግ ባለሙያዉ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ተናግረዋል ፡፡
የህዉኃትም ሆነ የሸኔ ቡድን ላይ እርምጃ ለመዉሰድ በመንግስት በኩል የአቅም ጉዳይ ሳይሆን የቁርጠኝነት ችግሮች አሉ ይህንን ችግር በአፋጣኝ ሊቀርፍ ይገባዋል በተጨማሪም እንደ ሸኔ ያሉ በህዝብ መሀል የሚገኙ ቡድኖችን የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በመስራት ቡድኑን ከማህበረሰቡ የመነጠል ስራዎች መሰራት አለባቸዉ ሲሉ አቶ ጥጋቡ አክለዋል ፡፡
በየትኛዉም አቅጣጫ የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች ላይ አፋጣኝ እርምጃ መዉሰድ ካልተቻለ የዜጎች ተረጋግቶ የመኖር ህልዉና ጥያቄ ምልክት ዉስጥ ስለሚገባ አስፈላጊዉ እርምጃ በተፈላጊዉ ሰአት ላይ ሊወሰድ ይገባል ሲሉ ባለሙያዎች ሀሳባቸዉን አንስተዋል ፡፡
በዮሃንስ አበበ